ไม่สามารถเล่นวิดีโอนี้
ขออภัยในความไม่สะดวก

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 16 มิ.ย. 2024
  • ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ያቀረቡት ሶስት ጋዜጠኞች ከእስር ተፈቱ። ዛሬ እና ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞች በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ፣ ቴዎድሮስ ዘርፉ ናቸው።
    ሶስቱ ጋዜጠኞች የፌደራል ፖሊስ “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር እንዲቆዩ” ማድረጉን በመጥቀስ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት ባለፈው ሳምንት ነበር። ከአቤቱታ አቅራቢዎች አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ በላይ ከእስር የተፈታው፤ ዛሬ ሰኞ ሰኔ 10፤ 2016 ከሰዓት መሆኑን ባለቤቱ በላይነሽ ንጋቱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግራለች።
    “ኢትዮ ኒውስ” የተሰኘው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ በላይ፤ በህዳር 2016 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለው በኋላ ለሰባት ወራት በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ በእስር ላይ ቆይቷል። ጋዜጠኛው ባለፈው ግንቦት ወር አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መዘዋወሩ ይታወሳል።
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น •