አዲስ አበባ ሰበካ | የጎፋ መዘምራን | Apostolic Church song
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 8 ก.พ. 2025
- ከግንቦት 12-14/2014 በአዲስ አበባ ሰበካ በጎፋ አጥቢያ በተደረገው ታላቅ ጉባዔ የጎፋ ጥምር መዘምራን ያቀረቡት መዝሙር
ግጥም/Lyrics
በውበትህ በግርማህ በመገኘትህ እንኑር
ስጋ ለባሽ ክብርህን አይቶ ይውደቅ ከእግሮችህ ስር
በቃን አንልም አይተን ይበልጥ እንሻለን ገና
ይቆጣጠረን በኃይል ይውረድልን ያ ደመና
ያ ክብርህ ይገለጥልን ያ ክብርህ
ያ ክብርህ ዛሬ ይምጣልን ያ ክብርህ
1. እንደአባቶቻችን የእኛም ልመና ነው
አናርፍም በጭራሽ ሆኖ እስክናየው
በግልጥ እስክትሰራ እጅህ እስክታገኘኝ
በኃይልህ ደመና እስክትጎበኘኝ
ሌዋዊም በፊትህ መቆም እስኪያቅተው
ኢየሱስ ሆይ በክብርህ እባክህ ቤትህን ሙላው
ያ ክብርህ...
2. ከምድር ስበት በላይ አድርጎ ሚያንሳፍፍ
ከአለንበት ልማድ አላቅቆ ሚያሳልፍ
ይውረድ ሠማያትን ቀድዶ ይምጣልን
የሰማነውን ያንን ክብር አሳየን
ይብቃን ደግሞ በቃ ዛሬ ላንመለስ
አልፈን በተራራው ላይ እንመላለስ
ያጠግበናል ክብርህን ማየት ጌታ
ይከፈቱ ሠማያት ለአንድ አፍታ
ሳይዳስሰን አይለፍ በላያችን
ሌላው ቀርቶ ይህ ነው ልመናችን
ይከፈት(2x) ሠማይ
ናፍቀናል ክብርህን ልናይ
3. መስዋዕታችን ቢያገኝ በፊትህ ሞገስ
ጥሶ ሠማያትን ወደአንተ መቅደስ
ሚደርስ ይሁንልን አንተን የሚያወርድ
የሚያንቀሳቅሰው የኃይልህን ክንድ
ትነዋወጥ ምድር በክብርህ ተሞልታ
ድና ትቅር ኢየሱስ ነፍስ ሁሉ አንተን አይታ
ያጠግበናል...