Withholding part 2/ቅድመ ግብር ክፍል 2/ ግብር ቀንሰው የሚያስቀሩ ሰዎች/ቅድመ ግብር የቅጣት አይነቶች

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 24 เม.ย. 2024
  • Withholding part 2/ቅድመ ግብር ክፍል 2/ ግብር ቀንሰው የሚያስቀሩ ሰዎች/ቅድመ ግብር የቅጣት አይነቶች
    የንግድ ትርፍ/ የቤት ኪራይ ገቢ ግብረ አካል ነው
    በገዢው የሚሰበሰብ የግብር አይነት ነው
    ከውጭ የሚገቡ እቃዎች Withholding የሚያደርገው ጉምሩክ ነው
    ምጣኔው 2%፣30% እና 3%
    ከ1000 በላይ የእቃ ግብይት
    ከ3000 በላይ የአገልግሎት አቅርቦት
    ከውጭ የጉምሩክ ዋጋ፣ የኢንሹራንስና የትራንስፖርት ዋጋ 3%
    አላማው
    ገቢው በተገኘበት ወቅት ግብርን መሰብሰብ (time value of money)
    የግብር ስወራን ለመቀነስ
    ግብር ቀንሰው የሚያስቀሩ ሰዎች
    1. በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች፡- የአክሲዮን ማህበር፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ የሽርክና ማህበር፣ የህብረት ስራ ማህበር…..ወዘተ፣
    2. የመንግስት መ/ቤቶች፡- የፌደራል እና የክልል የመንግስት መ/ቤቶች፣የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣
    3. ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች፡- ማህበራትና የሃይማት ድርጅቶች
    4. መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፡- ‹‹የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች›› ወይም ‹‹የኢትዮጵያ ማህበሮች›› ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ በውጭ አገር የተቋቋሙ ተመሳሳይ ድርጅቶች፣
    5. የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በምርት ገበያው አማካኝት ከሚከናወን ግብይት ጋር በተያያዘ ገዥውን በመወከል የሚፈፅመው ግብይት
    6. የደረጃ “ሀ” ግለሰብ ግብር ከፋዮች
    የደረጃ “ሀ” ግለሰብ ግብር ከፋዮች
    ባለፉት 3 ተከታታይ አመታት በአማካኝ 10 ሚሊዮንና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ገቢ ያስመዘገቡ
    ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢያቸው ከግምት ውስጥ ሳይገባ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ቀንሰው የማስቀረት ግዴታ ያለባቸው የደረጃ “ሀ” ታክስ ከፋዮች፡-
    ማንኛውም ባለ ኮከብ ሆቴል ወይም ማንኛውም ሪዞርት፣
    ግብሩን ቀንሶ እንዲያስቀር ግዴታ የተጣለበት ሰው ተግባርና ኃላፊነት
    በአገር ውስጥ ከሚፈጸሙ ክፍያዎች ላይ በወሩ ውስጥ ቀንሶ ቀሪ ያደረገውን
    አጠቃላይ ግብር ከወሩ የመጨረሻ ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ለባለስልጣኑ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
    በእየንዳንዱ የግብር ዘመን የተፈፀሙ ክፍያዎችና ከክፍያዎቹ ተቀንሶ የቀረውን ግብር የሚያሳይ የሂሳብ ሰነዶችን መያዝና ለምርመራ ሲጠየቅ ማቅረብ
    እነዚህን ሰነዶች ቢያንስ ለ5 አመታት ማቆየት(በንግድ ህጉ መሰረት10አመታት)
    ግብር ለተቀነሰበት ሰው ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ መስጠት፡፡
    ከሚፈጸሙ ክፍያዎች ላይ ቀንሶ ያስቀረውን ግብር ገቢ በሚያደርግበት ጊዜ ክፍያ የተፈፀመለትን እና ግብር የተቀነሰበትን፡-
    የእያንዳንዱን ሰው /ድርጅት ስም፤
    የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/፤
    በወሩ ውስጥ ለተጠቀሰው ሰው የተከፈለውን ገንዘብ አጠቃላይ ድምር፣
    ተቀናሽ ተደርጎ የቀረውን ግብር በእያንዳንዱ ሰው ስም ለባለስልጣኑ ገቢ የተደረገውን ሂሳብ የሚያሳይ ዝርዝር ባለስልጣኑ በሚያዘጋጀው ቅጽ መሰረት ማቅረብ አለበት፣
    ከ1-4 ደረጃ ያላቸው ስራ ተቋራጮች፣
    ማንኛውም የሪል እስቴት አልሚ፣
    የምግብ አምራች እንዱስትሪዎች፣
    በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ግዥ የሚፈፅም ማንኛውም ግለሰብ ግብር ከፋይ በምርት ገበያው በኩል ላደረገው ግብይት ብቻ፣
    ሆስፒታሎች እና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስፈርት መሠረት ከፍተኛ እና ከዚያ በላይ ደረጃ ያላቸው ክሊኒኮች፣
    ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች፣
    ከአምራች እንዱስትሪዎች ምርት በመረከብ የሚያከፋፍል ማንኛውም ግለሰብ ግብር ከፋይ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ቅድመ ግብር በመቀነስ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡
    ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ታክስ ቀንሶ ማስተላለፍ ያለበት ሰው ሳይቀንስ የቀረውን /ቀንሶ ለባለስልጣኑ ያላስተላለፈውን ታክስ 10% ቅጣት ይከፍላል፡፡
    ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008
    የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008
    የቅድመ ግብር ክፍያ ሥርዓት አፈጻጸም ቁጥር 2/2011
    ከተከፋይ ሂሳብ ላይ የንግድ ትርፍ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው ግለሰብ ታክስ ከፋዮችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 145/2011
    በጊዜው ባለማሳወቅ ለዘገየበት ለእያዳንዱ የታክስ ጊዜ ያልተከፈለውን ታክስ 5% የሚከፍል ሲሆን ይህ የቅጣት ክፍያ የሚከፈለው 25% እሰከሚሆን ድረስ ይሆናል::
    በጊዜው ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ
    ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5%
    ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% ቅጣት ይከፍላል
    ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ታክስ ቀንሶ የመያዝ ግዴታ ያለበት ሰው ቀንሶ ያላስቀረ እንደሆነ ወለድ እና ቅጣትን ሳይጨምር ሳይቀንስ የቀረውን ታክስ ከአቅራቢው የማስመለስ መብት አለው፡፡
    ለድርጅት በሚሆንበት ጊዜ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ፣ ዋና የሂሳብ ሹም ወይም ታክስ ተቀንሶ መያዝ እንዳለበትና የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት ማንኛውም ሌላ የድርጅቱ ሰራተኛ እያንዳንዳቸው ብር 2,000 ቅጣት ይከፍላሉ፡፡
    ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰብ ግብር ከፋዮች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ካልተወጡ አቅራቢውና ገዥው እያንዳንዳቸው 20,000 ብር ቅጣት ይከፍላሉ፡፡
    ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የሚከፈልን ታክስ ለማሰቀረት በማሰብ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ታክስ ቀንሶ የመክፈል ግዴታ ላለበት ሰው እቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው 10,000 ብር ቅጣት ይከፍላል፡:

ความคิดเห็น •