የአርብ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ || Airb || Friday || Wudase Mariam Tirgume

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 10 ก.ย. 2024
  • የዓርብ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
    ይህ ዕለት ለምስጋና አምስተኛ ለፍጥረት ስድስተኛ ቀን,ነው፡፡ በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኹናም ሊቁን ባርካው ምስጋናዉን ጀምሯል፡፡ ከወትሮ ይልቅም ደናግልን አስከትላ መጥታለች፡፡
    ፩. ከሴቶች ተለይተሸ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን እያማለድሽ የምታሰጭ ነሽ /ሉቃ.፩፡፳፰/፡፡ ቤዴ የተባለ ተርጓሜ መጻሕፍት ይህን አንቀጽ ሲተረጉመው፡-
    “የመጀመርያው የሰው ልጆች ስሕተት ከዲያብሎስ በእባብ አማካኝነት ወደ ሴት ተላከ፡፡ ሴቲቱም በትዕቢት መንፈስ ወደቀች፡፡ ዲያብሎስ በእባብ ገላ ተሰውሮ መጣና የመጀመርያዎቹ ወላጆቻችንን አታለላቸው፡፡ ኢመዋቲው ጸጋቸውን ገፈፈው፡፡
    ስለኾነም ሞት በሴት ምክንያት ገብቷልና መድኃኒትም በሴት ምክንያት ይገባ ዘንድ ይገባው ነበር፡፡ ቀዳማይቱ ሔዋን ዲያብሎስ በእባብ ገላ ተሰውሮ አታለላት፡፡ ለሰውም ኹሉ የሞትን ጣዕም አቀመሰችው፡፡ ሌላይቱ ሔዋን ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ በተላከ መልአክ የዓለም መድኃኒት የኾነው ክርስቶስን አስገኘች” በማለት እመቤታችን ከሴቶች ኹሉ የመለየቷን ምሥጢር በጥልቀት አስተምሯል፡፡
    የማኅፀንሽም ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍሰ የሌለበት በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚያድል የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ የሚላን ሊቀ ጳጳስ የነበረውና አምብሮስ የተባለው ሊቅ ይህን አንቀጽ ሲተረጕም፡- “እመቤታችን አመነች እንጂ አልተጠራጠረችም፤ በመኾኑም የእምነቷን ፍሬ አገኘች፡፡ “ወብጽዕት አንቲ እንተ ተአምኒ ከመ ይከውን ቃለ ዘነገሩኪ እም ኀበ እግዚአብሔር - ከእግዚአብሔር አግኝተው የነገሩሽን ነገር እንዲደረግ የምታምኚ አንቺ ንዕድ ክብርት ነሽ” እንዲል /ሉቃ.፩፡፵፭/፡፡ እናንተ ከእግዚአብሔር አግኝተው የነገርዋችሁን ነገር እንዲደረግ የምታምኑም ንዑዳን ክቡራን ናችሁ፡፡ የሚያምኑ ነፍሳት አካላዊ ቃልን ይፀንሱታል፤ በግብራቸውም ይወልዱታል (ይገልጡታል)፡፡ እንግዲያውስ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ታደርጉት ዘንድ እመቤታችንን ምሰልዋት፡፡
    በፈጣሪያችሁ በመድኃኒታችሁ አምናችሁ ደስ ይላችሁ ዘንድ የእመቤታችንን ልቡና ገንዘብ አድርጉ /ሉቃ.፩፡፵፮-፵፯/፡፡ ምንም እንኳን ጌታችንን በሰውነቱ የምትወልደው (የወለደችው) እመቤታችን ብቻ ብትኾንም በእምነት በኵል ግን የኹሉም አማንያን ፍሬ ነውና” በማለት ይመክረናል፡፡
    አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ! የጽድቅ ፀሐይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካንቺ ተወልዶም /ሚል.፬፡፪/ በክንፈ ረድኤቱ (በሥልጣኑ) አቀረበን፡፡
    በሐዲስ ተፈጥሮ፣ በጥንተ ተፈጥሮ ፈጥሮናልና፡፡
    ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንዲህ ይላል፡-
    “በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከግብርናተ ዲያብሎስ ነጻ ወጣን፡፡ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ውሉደ እግዚአብሔር ተባልን፡፡ ከምንም በላይ ግን ከኀጢአት ቀንበር ተላቅቀን በሐዲስ ተፈጥሮ ተፈጠርን፡፡ ሥርየተ ኀጢአትን ሰጠን፡፡ ከርኩሰት ኹሉ አነጻን፡፡ ከጸጋው የተነሣ ደቂቀ አዳም የነበርን መላእክት አደረገን፡፡
    መላእክቱም ለእኛ በተደረገው ነገር ሐሴት አደረጉ፡፡
    ወዮ! ገና ሰዎች ሳለን መላእክት መኾናችን እንደምን ይረቃል እንደምን ይደንቃል? ይህ ኹሉ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው” /Fr. Tadros Malaty, On the Book of Isaiah 40:31/፡፡
    በሐዲስ ተፈጥሮ፣ በጥንተ ተፈጥሮ ከፈጠረን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
    ፪. አምላክን የወልድሽ እመቤታችን ሆይ! ፀሐይ ዘኢየዐርብ (የማይጠልቅ ፀሐይ) የተባለው የብርሃን ክርስቶስ እናቱ ነሽና በአፍኣ በውሰጥ በሥጋ በነፍስ አንቺን ብቻሽን እናከብርሻለን፤ እናገንሻለንም፡፡ ልዑላን ከሚባሉ መላእክት አንቺ ትበልጫለሽ፤ ትሑታን ከሚባሉ ከደቂቀ አዳምም አንቺ ትበልጫለሽ፡፡
    ከኀሊናት ኹሉ በላይ ነሽ (ኅሊና የአንቺን ክብር ተናግሮ መጨረስ አይቻለውም)፡፡ ክብርሽን ገናንነትሽን መናገር የሚቻለው ማነው? አንቺንስ የሚመስል ማነው? ሊቁ አባ ሕርያቆስም፡- “ይህንም ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ የልጅሽን የባሕሩ ጥልቅነት ይዋኝ ዘንድ ይወዳል፤ የወዳጅሽ የመሠወሪያው ማዕበልም ያማታዋል” ይላል /ቅዳ.ማር.ቁ.፹፬/፡፡
    መላእክት ያከብሩሻል፤ ያገኑሻልም፡፡ ሱራፌልም ያመሰግኑሻል፡፡ በኪሩቤል በሱራፌል አድሮ የሚኖረው እርሱ ሰው ኹኖ በማኅፀንሽ አድሯልና፡፡ ክብር የክብር ክብር ያለው እርሱ፤ ሰውን የሚወድ ሰውም የሚወደው እርሱ የእኛን ሞት ነሥቶ የእርሱን ሕይወት ለኛ ሰጥቶ ካባቱ ጋራ አስታረቀን፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በ “በእንተ ልደት” ድርሳኑ ላይ፡- “ስለዚህ ሥጋዬን ተዋሐደ! ወንጌልን ሲያስተምር እሰማው
    ዘንድ ሥጋዬን በተዋሕዶ ገንዘቡ አደረገው! ሥጋዬን ወስዶም መንፈሱን ሰጠኝ፡፡ ሰጠሁ፤ ተቀበልኩም፡፡ የእኔን ወስዶ የራሱን ስለ ሰጠኝም ሕይወትን ገንዘብ አደረግሁ፡፡ እኔን ለመቀደስ ሥጋዬን ተዋሐደ፤ የሚያድነኝ መንፈስ ቅዱስንም ሰጠኝ” ብሏል፡፡ ክብር የክብር ክብር ካለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋዉን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

ความคิดเห็น • 15

  • @Yalemwoerkeyayu
    @Yalemwoerkeyayu 26 วันที่ผ่านมา +3

    አሜን አሜን አሜን ቃለህ ህይወት ያሰማልን

  • @asegedechligaba1137
    @asegedechligaba1137 26 วันที่ผ่านมา

    አሜን አሜን አሜን ቃል ሂወት ያሰማልን አባታችን አሜን አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @GffDgb
    @GffDgb 26 วันที่ผ่านมา +1

    አሜን አሜን አሜን🤲🤲🤲🤲❤❤❤

  • @tymordoha
    @tymordoha 26 วันที่ผ่านมา +1

    አሜን አሜን አሜን ❤❤❤🙏🙏🙏ቃለ ህይወት ያሰማልን መምሀራችን ❤❤❤🙏🙏🙏

  • @AbebaMail
    @AbebaMail 26 วันที่ผ่านมา +1

    Amen amen amen 🙏 🙏 🙏 🙏 ❤❤❤❤

  • @FekerteBeshada-yk1bx
    @FekerteBeshada-yk1bx 25 วันที่ผ่านมา

    Amen አሜን አሜን ❤❤🌹🌹🌹🌹

  • @mulureta8500
    @mulureta8500 26 วันที่ผ่านมา +1

    አሜን አሜን አሜን

  • @user-jd6ry7lh7c
    @user-jd6ry7lh7c 25 วันที่ผ่านมา

    አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏

  • @Yesewulij
    @Yesewulij 26 วันที่ผ่านมา +1

    ❤❤❤Amen❤❤❤
    ❤❤❤Amen❤❤❤
    ❤❤❤Amen❤❤❤

  • @biizee2684
    @biizee2684 26 วันที่ผ่านมา

    Amen Amen Amen Amen ❤❤❤

  • @fantofanto5737
    @fantofanto5737 25 วันที่ผ่านมา

    Ameen Ameen Ameen nuf haa Haatuu Waqayyoo Saagalee jireenyaa isiin haa dhaageesiisuu ❤❤❤❤❤

  • @KhanKhan-lv6ys
    @KhanKhan-lv6ys 26 วันที่ผ่านมา +1

    🙏🙏🙏🙇🙇

  • @MuluMulu-x2h
    @MuluMulu-x2h 26 วันที่ผ่านมา +1

    Aman,aman

  • @biizee2684
    @biizee2684 26 วันที่ผ่านมา

    ❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉

  • @MaskaramMaskara
    @MaskaramMaskara 26 วันที่ผ่านมา +1

    Ameeen Ameeen Ameeen Ameeen Ameeen Ameeen Ameeen Ameeen Ameeen ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤