ለተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ድጋፍና ዕርዳታ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 11 ม.ค. 2025
  • አገራችን ኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል ጁንታው በከፈተብን መጠነ ሰፊ ጦርነት ምክንያት በርካታ መሠረተ ልማቶች ከጥቅም ዉጪ ከሆኑባቸው ክልሎች በዋናነት ከሚጠቀሱት አማራ እና አፋር ክልሎች መሆናቸው ይታወሳል፡፡
    በዚሁ መጠነ ሰፊ ጦርነት ምክንያት ከወደሙት መሠረተ ልማቶች መካከል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ትምህርት ቤቶች፣ የአስተዳደርና የጤና ተቋማት በጢቂቱ የሚጠቀሱ ሲሆን፤ ከነዚህም መካከል ደግሞ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠሽ ነው፡፡
    በዚሁ መሠረት የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የአገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የእያንዳንዱ ዜጋ ልጆች የሚማሩበት ተቋም እንደመሆኑ መጠን፤ የተለያዩ ግምታዊ ዋጋቸው 400,000 ብር በላይ የሚሆን ያገለገሉ የኃላፊ ወንበሮች፣ የቢሮ መቀመጫ ሶፋዎችን፣ ወንበሮች፣ ጠረቤዛዎች፣ መደርደሪያዎች እና መጋረጃዎች እንዲሁም ግምታዊ ዋጋው 350,000 ብር በላይ ዋጋ ያላቸው 70 ኩንታል የስንዴ ዱቄት ለደሴና አካባቢው ተፈናቃዮች እንዱሁም ለሰመራና አካባቢው ተፈናቃዮች ደግሞ የ250,000 ብር የስንዴ ዱቄት ባአጠቃላይ ወደ አንድ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ በማድረግ ለወሎ እና ለሰመራና አካባቢ በጦርነቱ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ድጋፍና ዕርዳታ አድርጓል፡፡

ความคิดเห็น •