የመለኮታዊ ምሕረት የፋሲካ ዕለት የአምስተኛ ቀን ታስዕት(ኖቬና) የጸሎት ሐሳብ ስቅለተ አርብ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 14 ม.ค. 2025
  • አምስተኛ ቀን
    ኢየሱስ፦ ዛሬ ራሳቸውን ከቤተክርስቲያን የለዩ (መናፍቃንና ከቤተክርስቲያን የተለዩ ክርስቲያኖች) ነፍሳትን አቅርቡልኝ በምሕረቴ ውቅያኖስም እንዲሰጥሙ አድርጓቸው በመሪር ሕማሜ ወቅት ልቤን እና አካሌን ቀደውት ነበር ያም ቤተክርስቲያኔ ነች ። ወደ ቤተክርስቲያኔ አንድነት ሲመለሱ ቁስሎቼን በሕማሜ ወቅት ስቃዬን እንዳበዙት በዛው መልኩ ቁስሎቼ ይፈወሳሉ።
    ቅድስት ፋውስቲና፦ እጅግ መሐሪው ኢየሱስ ሆይ አንተ መልካምነት ራሱ ነህ ከአንተ ብርሀንን ለሚሹ አትከለክልምና እጅግ ሩሕሩህ በሆነው የልብህ መኖሪያ የተለዩንን ወንድሞቻችንን (መናፍቃንና ከቤተክርስቲያን የተለዩ ክርስቲያኖችን)ነፍሳት ተቀበል። በብርሀንህ ወደ ቤተክርስቲያን ሕብረት ምራቸው እጅግ ሩሕሩህ ከሆነው የልብህ መኖሪያም እንዳይጠፉ ነገር ግን ወደ ደግነትህ ምሕረት እነሱም እንዲመጡ አድርጋቸው።
    ከአንተ የሚለያቸው መጋረጃ ቢቀደድ እንኳን በአንድነት
    ይፈሳል ከልብሕ ፏፏቴ ምሕረት
    የምሕረትህ ሁሉን ቻይነት
    እነዚህ ነፍሳትን ከስህተት ውጭ ይመራቸዋል
    ዘልዓለማዊ አባት ሆይ የምሕረት ፊትህን ወደ ተለዩን ወንድሞቻችን (መናፍቃንና ከቤተክርስቲያን የተለዩ ክርስቲያኖችን) በተለይም ባርኮትህን ባባከኑ እና ጸጋህን ያለ አግባብ በተጠቀሙ በእልከኝነታቸውም በስህተታቸው በጸኑ ላይ መልስ ስህተቶቻቸውን አትመልከት ነገር ግን የአንተን ልጅ ፍቅር እና ስለእነሱ ያለፈበትን እጅግ መሪር ሕማሙን ተመልከት እነርሱም በእርሱ እጅግ ሩህሩህ በሆነው ልብ የተሸፈኑ ናቸውና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እነርሱም ማብቂያ የሌለውን እጅግ ታላቅ ምሕረትህን ለዘልዓለም እንዲያከብሩ አድርጋቸው አሜን።
    የቅድስት ፋውስቲና ማስታወሻ 1218 -1219
    እንኳን ወደዚህ የዩትዩብ ገፅ በደህና መጣችሁ በዚህ ገፅ የሚከተለውን የቤተክርስቲያን ሐሳብ እናገለግላለን እንጋራለን "ቅዱስ ዜማ በቅዱስ መጽሐፍ ተመስግኗል(ኤፌሶን 5:19 ቆላስያስ3:16) ...ቅዱስ ዜማ ከሊጡርጊያ ተግባር ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ካለው በቅድስና ያድጋል፤ በውበት ጸሎትን ይገልጻል ፤ አንድነትን ያስፋፋል ፤ ከፍ ባለ ሥነ-ስርዓትም ቅዱሳት ስርዓቶችን ያበለጽጋል። ቤተክርስቲያንም በእውነት ኪነ ጥበብ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ትቀበላለች ፤ በጥራታቸው ተስማሚና ተገቢ ከሆኑም በመለኮታዊ አገልግሎት ላይ ታውላቸዋለች።" የሁለተኛው ቫቲካን ጉባኤ ስለ ስርዓተ አምልኮ ምዕራፍ 6 ቁጥር 112
    Join this channel to get access to perks:
    / @ethiopiancatholic
    Social Media
    Facebook / 478539786435992
    Telegram t.me/Catholicsong
    TH-cam / @ethiopiancatholic
    #EthiopianCatholicSong #HawassaCatholicSong #EthiopianCatholicMezmur​#EthiopianCatholicChurch​​ #Catholic​​ #EthiopianCatholic​​ #CatholicMezimurLyrics​​
    #LyricsVideos​​ #Mezmur​​ #ካቶሊክ​​ #ካቶሊክመዝሙር​​
    Rosery, ሮዛሪ, ሮዘሪ, መቁጠርያ, መቁጸርያ, VoiceOfRosary, Rosary
    hymns for mass, catholic hymns of praise, church songs catholic,holy rosary monday, virtual rosary, catholic diocese,thursday holy rosary,mass times online,livestream mass,daily mass,the daily mass,the daily mass,rosary for sunday,catholic church near me,spiritual praise songs,music for body and spirit

ความคิดเห็น •