ኤፍሬም ታምሩ | ጎጆሽ ይሻላል | Ephrem Tamiru | MUZIKA | Gojosh yshalal | ሙዚቃ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 4 ก.พ. 2025

ความคิดเห็น • 4

  • @Interstellar-uj3ie
    @Interstellar-uj3ie ปีที่แล้ว +4

    ❤ኤፍሬም ታምሩ ላይ ኣሳርጎቷል ኣበበ መለሰ
    . "ለውብዓለም"
    .
    በዘመኑ የነበሩ ድምፃዊያን ከዜማ ና ግጥም ደራሲያን እንዲሁም ከኣሳታሚና ሰው ጋር በመሆን የከተማ ግርግር ሸሽተው ኣልበማቸውን በትኩረት ለመስራት ከከተማ ይወጡ ነበር ፤እናም ድሬዳዋ ና ኣዳማ በብዛት ይመረጡ ነበር
    .
    .
    በእንደዚህ ዓይነት ወቅት ታዲያ አበበ መለሰና ቴዎድሮስ ታደሰ ናዝሬት ላይ ከትመዋል፤አንድ ቀን ታዲያ ለምሳ ኣንድ ሆቴል ሲገቡ አበበ አንድ ሰው ያገኛል ፤በድንጋጤ ብዙ ነገር ኣሰበ ( ያየው ኣያ ትርፌ ነበር ፤ኣያ ትርፌ ማለት አበበ መለሰ ለዘመቻ ለደጀን ቅርብ የሆነች ከተማ ተመድቦ በሰራበት ወቅት የዛች መንደር ኗሪ የነበረ ገበሬ ነበሩ ፤እዛ በነበሩበት ወቅት ባይተዋርነት ሳይሰማቸው ቤታቸው በመጋበዝ በማሳደር ብዙ ነገር ከሚስታቸው ጋር ያረጉላቸው ነበር ፤) እና ተጎሳቁሎ የተመለከተው አቤ ምን እንደሆን ሲጠይቀው .....
    "የሀገሩ ሰው አአ ሄዶ ገንዘብ ኣግኝቶ ሲለወጥ ኣይታ እኛም ያልፍልና ብላ ይኸ ወጣች እርሷን ፍለጋ እየኳተንኩ ነው ፤ እስኳሁን ኣላገኝዋትም ሀረር ናት፤ ናዝሬት ናት እያሉ እየፈለኳት ነው ውብዓለሜን" ይለዋል .......
    .
    .
    ኣቤ በወቅት የሚችለው ኣርጎ ሀገሩ የሚገባበትን የትራንፖርት ሰጥቶ ከሸኝው በኋላ ግን ሃሳቡ ኣላረፍ ኣጠገቡ ለነበረው ቴዲ ታደሰ ግጥሙ ሰርቶ እንዲዘፍን ሰጠው ....1979 በወጣው ኣልበም ላይ ውብ ዓለሜን ዘፈነው
    .
    .
    . አለም ነይ ገብል አለም አለም
    አለም ነይ እንድታግዥኝ
    ውብዓለሜ መጥተሽ እይኝ
    ውብዓለሜ ድረሽልኝ
    .
    .
    ዓመታት ቢያልፉም አቤ ግን ኣሁንም ስሜቱ ከትርፌና ከውብዓለም ኣልጠፋ አለው ፤ሌላ የሙዚቃ ድርሰት ሰራ "ጎጆ ይሻላል ተመለሺ "አለ
    እናም ጎጆሽ ይሻላል ለኤፍሬም ታምሩ ሰጥቶት በ1985 ዓም ባወጣው ድንቅ ኣልበም ላይ ተጫወተው ....
    ተመለሺልኝ እንደ ምንም ባጀሽ
    ከተማ ኑሮ እንዴት አረገሽ
    ሁሉንም ትተሽ ተመለሽ
    ውብ ዓለም እባክሽ
    ጎጆሽ ይሻላል ንብረትሽ
    የደሃው ትዳርሽ❤

    • @johnnybelay9198
      @johnnybelay9198 6 หลายเดือนก่อน

      እኔ አልቻልኩም በጣም ነው ሚያሳዝነው ድንግል😢

    • @BamlakuMeseret-o1w
      @BamlakuMeseret-o1w 5 วันที่ผ่านมา

      የምር ኤፊ ሲዘፍነው ሰውየውን ነው የሳልሁት ....አንጀቴን በላኝ!!!!

  • @eyerusalemmola2364
    @eyerusalemmola2364 2 ปีที่แล้ว +1

    ኤፍ ሰወድህ ግርማሞገሰነህኮ