Ethiopia: ይህን ገዳም የረገጠ የሲዖልን ደጅ አያይም የማትማር ነፍስ ደጁም አይረግጥም።

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 5 พ.ค. 2022
  • #Ethiopia #7Tube ይህ ገዳም በሰሜን ሸዋ በሚንዳ ወረዳ ቤተክህነት ስር የሚገኝ ከመልኬ ፄዲቅ ገዳም በጀርባው ከ1 ሰዓት የእግር መንገድ የሚያስኬድ ድንቅ ገዳም ነው።
    ገዳሙ በ1500 ዓ ም የተመሰረተ ሲሆን መስራቹም ታላቁ ፃድቅ ገቢረ ተአምረኛው ገድሉ በወርቅ ልባድ የተለመደው አባ በረደድ የሚባሉ ደገኛ መነኩሴ ነው የዓለማት ጌታ ስሉስ ቅዱስ ተብለው የሚመሰገኑ ቅድስት ስላሴ ለእኚ ታላቅ አባት ተገልጠው በአንድ ትልቅ ዋሻ ሶስት ቤተመቅደስ እንዲሰሩላቸው በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ወደ እዚህ ቦታ ላይ ተላኩ።
    ወደ እዚህ ስፍራ ሲመጡ ደብረ መዳኒት አቡነ መልኬ ፀዴቅ ገዳም ሲደርሱ ይህ ቦታ ተሰወራቸው ክቡር አባታችንም ሰይጣን ገዳሙን ሰወረብኝ ብለው ስቅስቅ ብለው አለቀሱ በእዚህ ጊዜም መላዕክት ተገለጠላቸውን ገና ቦታው ላይ እንዳልደረሱ ነግሯቸው ቦታውን ይመሯቸው ዘንድ ነብርና ጉሬዛ ታዞላቸው በእነርሱ እየተመሩ ነጎድጓድ ስላሴ ዋሻ ገዳም ደረሱ።
    ይህም ገዳም ብዙ ዛፎች የበዙበት የአራዊት መኖሪያ እንደነበር ፃድቁ ከሁኔታው ተረድተው በትልቁ ዋሻ ውስጥ በአንድነት በሶስትነት የሚመሰል ቤተመቅደስ ሰርተው ባለ አምስት ቆጥም አበጃጅተው ገዳሙ ገደሙት በእዚህም ብዙ ተጋድሉ።
    በተጋድሏቸው በእጃቸው ላይ አቦ የሚል ቃል ተፃፈባቸው ቦረናም በሚባል ሀገር ሄደው 5 ገዳማትን መስርተው አንፀው ተመልሰው በእዚህ ገዳም ወደ በዓታቸው ገቡ ፃድቁ ተክለሃይማኖት ፤አቡነ መልኬ ፄዲቅ ፤ቦታው ድረስ በመሄድ ባርከው ፀልየውበታል።
    የብዙ ቅዱሳን የብዙ ስውራን አባቶቻችን በዓት ሆነ ከቦታው ቅድስና ክብር የተነሳ ያልረገጠው ፃድቅ እንደሌለ የገዳሙ ድርሳን ያስረዳል የቦታው ቃል ኪዳን እንደ መልኬ ፄዴቅ ነው ይህ ገዳም የረገጠ የሲዖልን ደጅ አያይም የማትማር ነፍስ ደጁም አይረግጥም።
    ቦታው ላይ መጥቶ የተቀበረም ስጋው አይፈርስም ቃል ኪዳኑ የፀና እንደሆነ አፅመ ቅዱሳኑ ምስክር ናቸው ማንም ከቶ ያለ ስላሴ ፈቃድ ሊረግጠው የማይችል የመጥመቀ መለኮት የቅዱስ ዩሐንስ የቃል ኪዳን ፀበል የፈለቀበት ተአምራዊ ገዳም ነው።
    ማንም የማይገባበት ከጣራው ውስጥ የተበሳ ስምጥ ዋሻ የሚታይ ሲሆን እንዴት ይገባሉ የሚለው ነገር ግን ተአምር ሆኖ በዝምታ ከማየት ውጪ መልስ ታጡለታላችሁ ብዙ ፅላቶች ተሰውረውበታል አሁንም ድረስ ስጋ ለበስ ስውራን አባቶች በውስጡ ይገኙበታል።
    በገዳሙ ከ1000 እስከ 1500 ዘመን ያስቆጠሩ አፅመ ቅዱሳን ዛሬም ድረስ ስጋቸው ሳይፈርስ አጥንታቸው ሳይከሰከስ፤ጥርሳቸው ሳይወልቅ ፤ልብሳቸው ሳይቀደድ ቆባቸው እንዳለ ፂማቸው ሳይነቃቀል በግልፅ ይታያሉ።
    የፃድቁ አቡነ በረደድ አፈር ያልነካው በሳጥን የተቀበረ እንደሆነ የተቀበረበት ሳጥን ምንም ሳይሆን በውስጡ የተቀበረው ሰው ግን ስጋው ይፈርሳል አጥንቱም ይሰበራል ለምስክርነት እርሱ በገዳሙ ይገኛል።
    በእዚህ ገዳም ድርሳናት ገድላት ፤ነዋይተ ቅዱሳኑ በሙሉ ከወርቅ ብቻ የተሰሩ የተለበዱ ሲሆን ደብረ ወርቅ ተብሎም ይጠራ ነበር ነገር ግን ገዳሙ ከተመሰረተ ከ400 ዓመት በኃላ ታላቅ ቃጠሎ ገደሙ ላይ ደርሶበታል የተነሳው እሳትም የሚያጠፋው ጠፍቶ ለብዙ ጊዚያት ሲነድ የነበረ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ የገዳሙ መገልገያ ሊወድም ችሏል።
    ፃድቁ አቡነ በረደድ ገድላቸው ጨምሮ በርካታ ንዋይተ ቅዱሳት ተቃጥለው ገዳሙ እስከ 2000ሺ ዓመተ ምሕረት ድረስ ተዘግቶ ኖረ ከ2ሺ ዓመተ ምሕረት በኃላ በአባ ኢሳያስ በሚባሉ አሁን ገዳሙን በአመኔትነት የሚመሩት አባት አማካኝነት ዳግም ገዳሙ ተከፈተ።
    አንዱን የዋሻ ቤተመቅደስ ወደ ነበረበት ለመመለስ አንፆ ለመጨረስ የወሰደው ጊዜ ከ25 እስከ 30 ቀን ብቻ ነው በመንፈስ ቅዱስ አይል በፈቃደ እግዚአብሔር ለመሰራት በቅቷል።
    ይህን ገዳም ዳግም እንዳይዘጋ አሁን እየመጡ ያሉት መነኮሳት እንዳይበተኑ ከክቡር አባታችን ጋር ምሽቱን ሙሉ የተወያየን ሲሆን አንድ የልማት ስራ ለማስጀመር የተረከቡት 30ሺ ሄክታር ያላቸው ሲሆን በከብት እርባታ፤በወፍጮ ስራ በሽመና ለማደራጀት ጥናት እየተሰራ ሲሆን ወደ ፊት ወደ እናንተ አደርስና ገዳሙን እንታደገዋለን።
    ወዳጄ 5 ዋሻ አንዱ የተክለሃይማኖት ነው፤ሌላው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፤የአቡነ መልከ ፀዴቅ፤ የአቡነ በረደድ እና የቅዱስ ሚካኤል ዋሻ ነው።
    ፃድቁ አባታችን አቡነ በረደድ ብዙ ከተጋደሉ በኃላ በደብረ መዳኒት በአቡነ መልኬ ፄዴቅ ገዳም ሱባዬ ሳሉ በእዛው አረፉ ከእዚህም የተነሳ ገዳማቸው ነጎድጓድ ቅድስት ስላሴ ካረፈው ከእዚህ ቅዱስ ስፍራ እንዲው ገዳምህ ቃል ኪዳኑ አንድ ይሁን ሲል አምላካቸው አፀናላቸው።
    ሁለቱም ገዳማት ቃል ኪዳናቸው አንድ ሆነ የፃድቁ በረከት የቅድስት ስላሴ ቸርነት በሁላችንም ላይ ይደርብን ።

ความคิดเห็น • 29

  • @tttthhhy3456
    @tttthhhy3456 2 ปีที่แล้ว

    ልዑል እግዚአብሔር በእነዚህ ቅዱሳን አባት በቃል ኪዳኑ ይማረን

  • @almnatgete7566
    @almnatgete7566 ปีที่แล้ว

    Amen amen amen ksdet mless lbate abgh selasa

  • @zigeredagerelase2220
    @zigeredagerelase2220 2 ปีที่แล้ว

    የ ኣቡነ በረደድ በረከታቸው ከኛ ጋራ ይሁንልን 🙏🙏🙏

  • @tesfahunayalew1770
    @tesfahunayalew1770 2 ปีที่แล้ว

    ቦታውንለማየት የድግልማሪያምልጅ ፍቃዱይሁንልኝ አሜን

  • @user-qn7pb6yx3c
    @user-qn7pb6yx3c 2 ปีที่แล้ว +1

    መታደል ነው በረከታቸው ይደረሰን

  • @misiraaguddato3570
    @misiraaguddato3570 2 ปีที่แล้ว

    አሜን አሜን አሜን

  • @senaitgebremedhin7460
    @senaitgebremedhin7460 ปีที่แล้ว

    🌻እግዚአብሔር ይመስገን 🌻
    አሜን (3) ቃለ ሂወት ያሰማልን 🙏
    የቅዱስ አባታችን በረከታቸው ይደርብን 🤲🤲🤲

  • @user-gc3ng8sw3j
    @user-gc3ng8sw3j 6 หลายเดือนก่อน

    አገሬ እልልልልልልልልልል አያት ቅርማያቴ ዘርማዘሬ እዝህ ታላቅ አገር ገዳም ነዉ ከእዝህ መፈጠሬ ክብር ለቅጣሪያ አሚን የአያቶቸ ቦታ ❤❤❤❤❤❤❤

  • @misiraaguddato3570
    @misiraaguddato3570 2 ปีที่แล้ว

    ቃለ ህይወትን ያሰማልን

  • @birukyeshambel1046
    @birukyeshambel1046 2 ปีที่แล้ว

    በረከታቸው አይለየን

  • @zinashdejen6761
    @zinashdejen6761 2 ปีที่แล้ว

    Amen 👏👏👏

  • @danmar8071
    @danmar8071 2 ปีที่แล้ว

    የጻድቁ አባታችን አቡነ በረደድ በረከት፥ረድኤታቸው ድል የማትነሳ እምነታቸውን ያድለን ዘንድ እንዲሁም ከዚህ ቅዱስ ስፍራ ሄደን በንሰሐ እንታጠብ ዘንድ ወልደ አብ ና ወልደማርያም በሁለት ልደት የከበረው የሆነው የትንሳኤው ንጉስ፥ አሸናፊያችንን ሞት ድል የነሳው መመኪያችን ዳግም በሚያስፈራ መለኮታዊ ግርማው የሚገለጠው ቅዱስ አማኑኤል በጎ ፈቃዱ ይሁንልን።

  • @tameghaa5255
    @tameghaa5255 ปีที่แล้ว

    በረከታቸዉ ይደርብን

  • @user-bh7on7ik4b
    @user-bh7on7ik4b 2 ปีที่แล้ว +1

    አሜን አሜን አሜን ⛪️✝️👏👏👏👏👏🥰🥰🥰

  • @tttthhhy3456
    @tttthhhy3456 2 ปีที่แล้ว

    እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር የአባታችን የአባ በረድ በረከታቸዉ ይደርብን አሜን፫

  • @alemetsehayealemayehu4506
    @alemetsehayealemayehu4506 2 ปีที่แล้ว

    አሜን አሜን አመን ቃለህይወት ያማልን ::

  • @davidbelay7423
    @davidbelay7423 2 ปีที่แล้ว

    አመጸኛ በጻድቃን ስም አምጽ ሰዎች በትክክል ለእግዚአብሔር ተገዝተው በንስሃ እና በመቀደስ መንግስቱን እንዳይወርሱ የገነት በር ላይ ቆመሕ ለክ አንዳባትሕ መንገዱን አስቀይስ ማስተዋሉን ይስጥሕ

  • @feqrtemarymi9021
    @feqrtemarymi9021 2 ปีที่แล้ว

    Amen Amen Amen Kalwotin Yasamalin Abatachin Rajimi Edme Kaxena Yisxilini Ekan bselami maxachu 👏👏👏 🙏🙏🙏💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️🥰🥰🥰🙏🙏🙏

  • @JMGD44
    @JMGD44 2 ปีที่แล้ว

    የሌለ ነገር አታውሩ። ጠንቆዬች

    • @atihan3391
      @atihan3391 ปีที่แล้ว

      Lebonan yadelesh/eh

    • @atihan3391
      @atihan3391 ปีที่แล้ว

      Lebonan yadelesh/eh

  • @yohansmahari2497
    @yohansmahari2497 7 หลายเดือนก่อน

    ቦታው የት ነው 🙏🙏🙏

  • @misiraaguddato3570
    @misiraaguddato3570 2 ปีที่แล้ว

    እሺ የገዳሙ አካውንት ስጡና ይቅርታ ቦታው የት ነው

  • @misiraaguddato3570
    @misiraaguddato3570 2 ปีที่แล้ว

    አሜን አሜን አሜን

  • @misiraaguddato3570
    @misiraaguddato3570 2 ปีที่แล้ว

    አሜን አሜን አሜን

  • @misiraaguddato3570
    @misiraaguddato3570 2 ปีที่แล้ว

    አሜን አሜን አሜን

  • @hiritabvs1500
    @hiritabvs1500 2 ปีที่แล้ว

    አሜን አሜን አሜን

  • @user-en4lg1yq2w
    @user-en4lg1yq2w 2 ปีที่แล้ว

    አሜን አሜን አሜን