❤❤❤Halelujah, Glory to God. Amen Amen Amen be maleda misgana, be ketirim misgana, be lelitim misganayen abezallewu be zimaree yetajjebe abezalewu yene Geta eelliililililililiiiiiililililililililililililieelliililililililiiiiiililililililililililililieelliililililililiiiiiililililililililililililieelliililililililiiiiiilililililililililililili. Hanichiyyee wudd ihitachin lela tsega yidrebilish be Iyesus sim
THE SONG STRIKES ME........... OH GOD YOU DESERVE OUR HOLY PRAISE..... YOU ARE GOD OF GLORY, MERCY, LOVE, PEACE,................. GOD BLESS YOU MORE AND MORE 💕💕💕💕💕💕
“....teaching and admonishing one another in psalms and hymns and spiritual songs, singing with grace in your hearts to the Lord.” - Colossians 3:16 (KJV) Hanniye, be blessed... you are our blessing... 🙏😇
እስትንፋስ ያላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ!!!
1.በማለዳ
የተገባህ ምስጋና አንተ ነህ የኔ ጌታ
የተገባ ክብር ላንተ ነው የኔ ጌታ
በምስጋና ወደፊትህ እቀርባለሁ ላመልክህ
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ይገባሀልና ለስምህ
1-በምስጋና የተፈራህ ገናና አምላክ ነህ
ልዑል አምላክ ብንዘምርህ ብንሰግድልህ አይበቃህ
እልፍ እእላፋት ያንተ ፍጥረት ላንተ ክብር ያዜማሉ
ቀን ከለሊት ያንተን ስራ በምስጋና ያውጃሉ
በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ
በቀትርም ዝማሬዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ
2 ስምህ ሀያል የአማልክቱም አምላክ ገዢ ነህ
ታላቅ ጌታ የሆነልህ ሰማይ ምድሩ ምስጋናህ
መላዕክቱ ላንተ ሞገስ ላንተ ግርማ ይዘምራሉ
ባይገልፅህም በአዲስ ቅኔ ምስጋናህን ያውዳሉ
በማለዳ....
እኔ ብዙ ተደርጎልኛል
ለኔ ብዙ ሆኖልኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይሻለኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅኛል
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን
Music A. Mesfin Densa
Recording Mesfin Densa
Bass Biruk Yohannes(Candy)
Background Vocal -Yacob Million
Mixing and Mastering Nitsuh Yilma
❤❤❤❤🎉
God bless you and your family
kibir lesu bcha yhun. AMEN
😊
@@HannaTekleOfficial አሜን😍❤
3ኛው አልበምሽ ቆንጆ ክርስቲያን አድርጎ ሰርቶኛል, ,,
የአብዛኛው ክርስቲያን የዩንቨርስቲ ቆይታችንን በእግዚአብሔር እግር ስር እንድንቆይ ረድቶናል ። በግሌ ብቻ ልቤን ደግፈው የሚለው ባለውለታዬ ነው ።በትግራይ ጦርነትም በርሱ ተደግፊያለሁ።በብዙ ነገር ደግፎኛል ።አሁን መመረቂያ አመቴ ነው ።በማለዳ ምስጋናዬን እንካ እያልኩ ልመረቅ ነው ።😢❤❤❤ እግዚአብሔርን ስለ አንቺ አመሠግናለሁ
ሲል ሁሉም አግዚአብሔር ይመስገን እንኩዋን ጌታ እረደሽ 🙏🙏🙌🙌🤗🤗👏👏🎉🎉🎉😊😊
Congratulations my love 🎉 God is good!
Ewnt same here
Blessed
wow! enkuan geta redesh ehite
ከዛሬ 12 አመት በፊት የ 10 ኛ ክፋል ተማሪ በነበርኩበት ወቅት በከባድ የ ጨጓራ በሽታ በምሰቃይበት ወቅት ውላችን አይደለም ስኬት አንለያይም ሚለው ዝማሬ በብዙ አፅናንቶኛል ሀኒዬ ዘመንሽ ሁሉ የክብር እና የበረከት ይሁን ❤Much love and respect
Bemin dank wendime ebakih lije tesekaye
I am orthodox but I love your singing(zimare) i listen to all of your albums thanks .
Me too ...still listening..but her song is always difficult to download on TH-cam
Geta eyeterah nw wendeme
ልንረሰርስ ነው ደሞ 🙏🙏
Ewntehn new 2017 bemezmuroch eyetebarekn new
በደንብ
Yessssss
Yessss❤❤❤
yes❤❤❤❤
የተገባህ ምስጋና አንተ ነህ የኔ ጌታ
የተገባህ ክብር ላንተ ነው የኔ ጌታ
በምስጋና ወደ ፊትህ እቀርባለሁ ላመልክህ
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ይገባሃልና ለስምህ
በምስጋና የተፈራህ ገናና አምላክ ነህ
ልዑል አምላክ ብንዘምርህ ብንሰግድልህ አይበቃህም
አእላፋት ያንተ ፍጥረት ላንተ ክብር ያዜማሉ
ቀን ከለሊት ያንተን ስራ በምስጋና ያውጃሉ
በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ - እኔ አበዛለሁ
በቀትርም ዝማሬዬን አበዛለሁ - አበዛለሁ
በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ - እኔ አበዛለሁ
በለሊትም ዝማሬዬን አበዛለሁ - አበዛለሁ
ስምህ ሀያል የአማልክቱም አምላክ ገዢ ነህ
ታላቅ ጌታ የሆነልህ ሰማይ ምድሩ ምስጋናህ
መላዕክቱ ላንተ ሞገስ ላንተ ግርማ ይዘምራሉ
ባይገልፅህም በአዲስ ቅኔ ምስጋናህን ያውዳሉ
በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ - እኔ አበዛለሁ
በቀትርም ዝማሬዬን አበዛለሁ - አበዛለሁ
በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ - እኔ አበዛለሁ
በለሊትም ዝማሬዬን አበዛለሁ - አበዛለሁ
ለኔ ብዙ ተደርጎልኛል ኧረ እኔ ብዙ ሆኖልኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይሻለኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅልኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይበጀኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅልኛል (2)
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን
እግዚአብሔርን ያመስግን (4)
👏
የኔ ጭምት ስላንቺ እግዜአብሔርን አመሰግነዋለሁ ሃኒዬ..ከ2012-2015 አራት ዓመታት ጦርነት እንደ እሳት በተንበለበለበት ጊዜ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ስማር በዛ ስጋት እና ጭንቀት ውስጥ እግዚአብሔር በነዛ 16 track 3ኛ አልበምሽ ላይ አፅናንቶኛል የለትተለት ምግቤ ነበር በፈተናዎች ሁሉ አልፌ ተመረቅኩባቸው እስከዛሬም ያፅናኑኛል❤
እሰትንፋሰ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን አሜን!!!
የቀሩትን ቁጥሮች ቁጭ ብዬ፣እየሄድኩ፣ቆሜ እየጠበኩ ነው ምክንያቱም ሀኒቾ ቅድስተ ቅድሳን የሚያጥን መዝሙር ዘምራለች ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።
ኡፍፍፍፍ ተባረኪ hanaye
አቤት ቅኔ የማያልቅበት ጌታ!!!! ስሙ ይክበራ!!!
ሀኒቾ የተወደድሽ ደስ ይበልሽ!!!
TEBAREKU
እረ እኔም በጣም ብዙ ብዙ ተደርጎልኛል በጣም በጣም...ብ...ዙዙዙ የፀጋ ሁሉ አምላክ ይባረክ!!!
በማለዳ ስነቃ የሰማሁት የመጀመሪያ ዝማሬ ነው... መስማት ማቆም አልቻልኩም...
እግዚአብሔር አምላክ በሰላሙ ይቀፍሽ እህቴ!
ልልልልልልል ከማመስገን በቀር ኦኦኦኦኦኦኦ ምን ይሻለኝል ኢየሱስ ጌታ ተባረኪ
ዛሬም ምህረቱ በዝቶልን በህይወት ኖረን በአዲስ ዝማሬ ልናመሠግነው በቃን ተመስገን 🙏🙏🙏
እልልልልልልልልልልልልል በምስጋና የተፈራህ አምላክ ነህ እልልልልልልልልልልልልልልልልልልል በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ በቀትርም ምስጋናዬን አበዛለሁ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
ከሱማሌ ዶሎ
ተባረኪ
ደግሞ ሌላ በረከት ሀሌሉያ ክብር ለፀጋው ባለቤት ለኢየሱስ ❤❤❤ ሀኒዬ ብሩክ ነሽ
A season of singing 🎵 ዘመኑ የዝመሬ ነዉ ዘማሪሆች ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ በላይ በላዩ ላይ እጨመራችሁ ዝማሬ በዝቶልናል
❤❤❤❤እኔ ልቤ ተሰንጥቆ ሊወጣብኝ ነው በዚህ ዝማሬ ❤❤❤❤❤❤❤ ሀንዬ ጌታ ይባርክሽ ኡፍፍፍፍ
አቤቱ እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ሆይ ምን እንላለን ስለ ፀጋህ ስምህ ይቀደስ።
*ምድራችን በጨለማ እና በጭንቅ ባለችበት ጊዜ የምንፅናናበትን የዝማሬ ጎርፍ ነደልክልን።
*አይምሯችን በክፋ ወሬ እና በሀዘን እንዳይሞላ በዝማሬ ዝናብህ አጠብከን።
* ለዚህ ዓለም ከሚመች ተረተረት እና አሉባልታ እንዳንጠመድ TH-cam ን በዝማሬ አጥለቀለክልን። አቤት ፀጋህ!
ለቤተክርስቲያን እያበዛኸው ስላለ ፀጋህ ስምህ ይባረክ። ያፈሰስክልን ይህ ዝማሬ ከመቅደስህ ወጥቶ ምድራችንን በማፅናናትህ ያጥለቅልቅ።
እንዴት ደስ የሚል መዝሙር ነዉ❤❤❤❤ተባረኪልን
አንተን ከማመስገን በቀር ምን ይበጀኛል ። ሀኒቾ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክሽ፣ፀጋ ይብዛልሽ።
💕👍
ቅኔ የማያልቅበት ጌታ ለአስቱ ስጥቻለሁ ለሃኒ አለቀብኝ የማይል ጌታ በተጠጋነው ቁጥር ሁሌ አዲስ ቅኔ አዲስ የምስጋና ዩውዳሴ የአምልኮ በረከት በተጠጉት ልክ ሆኖ በረከትን የሚያፈልቅ በሰዎች ውስጥ ሆኖ ለራሱ መመለኪያ ቅኔ የሚሰጥ ምን አይነት ድንቅ አምላክ ነው ስሙ ይባረክ❤❤❤ሃኒ በሰማሁት ቁጥር ኮሜንት ስፅፍ እራሴን አገኘዋለሁ ተባርከሽ እኛም እንድንባረክበት በረከት ሆንሽን እናመሰግናለን🎉🎉
በጣም ድንቅ
የዜማው እርጋታ
የግጥሙ ውበት
የሙዚቃው ጣዕም ልዩ ነው❤❤❤
ተባረኩልኝ❤❤❤
በሕይወት ዘመን የእግዚአብሔርን ፍቅርና ቸርነት መዘመር ምንኛ መታደል ነው!
አሜን የተገባህ ምስጋና ላንተ ነው ጌታ...❤❤❤
ሐኒዬ እጅግ የተባረክሽና የተወደድሽ ዘማሪት አሁን ደግሞ በሌላ ድንቅ ዝማሬዎች ልትባርኪን ስለመጣሽ ጌታ ይባርክሽ።
ይሄ መዝሙር ቃል አሳጥቶኛል፥ ጆሮዬ ሊሰማ የናፈቀው አይነት ውብ ዜማ ከድንቅ ግጥምና አዘማመር ጋር ተዋህዶ በማፊ ምርጥ ሙዚቃ ታጅቦ ሲሰማ የሚፈጥረው ስሜት በጣም ልዩ ነው። ተባረኪልን
አድናቆቴና ምስጋናዬ ለማፊም ይድረስልኝ፥ በጣም ውብና ደረጃውን የጠበቀ ሙዚቃ ሰርቶልሻል
ስለአንቺ እግዚአብሔርን አመሠግናለሁ
ለምልሚ Hani
የበረከት ሁሉ አምላክ ይባርክሽ ሀና እህታችን።
ሙዚቀኞችም ለጌታ ክብር ስለቀደሳችሁት ብዙ የተባረክ ችሎታችሁ ልዑል አብዝቶ ይባርካችሁ።
የእግዚአብሄር ልጆች ክብር እጅግ ይባረካል። ለክበሩ አብዝታችሁ በስሙ ተገለጡ።
❤❤ምን አይነት መባረክ መታደል ነው ውፍ ፀጋው አሁንም ይብዛልሽ እልፍ ሁኝ ድንቅ ዝማሬ ❤❤እግዚአብሔር ልናመሰግን ተፈጥረናል
ልዑል አምላክ ብንዘምርልህ ብንሰግድልህ አይበቃህም!
ሀና እግዚአብሔር ይባርክሽ🙏
አሜን የሚገርምሽ ይህንን ሁለት ወር ወደዚህ በጣም ወስጤ በይበልጥ ሞልቶት የሚፈሰው እግዚአብሔር ስለማመስገን ነው ተባረኪ ጥሩ መልክትና መንፈስ ያለበት ዝማሬ ነው አንቺ የዘመናችን ድንቅ ሴት ነሽ ብሩክ ሁኝ እንወድሻለን ሀኒዬ😍
ትላንተ አልሰራ ብሎኝ ነበር
ሃኔ ተባረክ ከአ/ምንጭ ❤❤❤
የእግዚአብሔር ስም ይባረክ አሜን
😭😭😭embayen makom akategn abatie menfes kidus nekagn agegnegn ….tebareki haniye
ብዙ ተደርጎልኛል እና አመሰግናለሁ 🙏ሀኒ ተባረኪ ሙሉውን እስክሰማ ቸኩያለሁ😇😇😇
ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ እንደ አንቺ አይነት መንፈስ ያለባትን ዘማሪት ስለሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን በሁለንትናዊ በረከት ጌታ ይባርክሽ❤❤❤❤❤
Praise God, We are Grateful that you're pointing everthing to God, ፀጋውን ያብዛልን, እውነት ነው ልንረሰርስ ነው ሲከብር ጌታ ክብሩን, ፅጋውን እያየን.
አብዝቶ ይባረክሽ.
ለልዑል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ክብር ይሁንለት።
የነፍስ ዝማሬ የሚለውን መዝሙርሽን በጣም ነው ምባረክበት ይሄም እጅጉን ድንቅ ነው ፀጋው ይብዛልሽ
የሰማይ ሽታ ዝማሬ እግዚአብሔር ይመስገን 🙌🏾🔥🔥
ዘመንሽ ይለምልም ባንቺ ያለው የእግዚአብሔር ፀጋ እንዴት ድንቅ ነው ክብር ለጌታ ይሁን
❤❤❤Halelujah, Glory to God. Amen Amen Amen be maleda misgana, be ketirim misgana, be lelitim misganayen abezallewu be zimaree yetajjebe abezalewu yene Geta eelliililililililiiiiiililililililililililililieelliililililililiiiiiililililililililililililieelliililililililiiiiiililililililililililililieelliililililililiiiiiilililililililililililili. Hanichiyyee wudd ihitachin lela tsega yidrebilish be Iyesus sim
የአምልኮ መንፈስ የፈሰሰበት ድንቅ ዝማሬ ነው ተባረኪ ፀጋው ይብዛልሽ።
በረከቶቻችን እስይ ለዚህ ጌታ ይገባዋል 🙌🙌🙌🙌🙌በቋቋዎች ይዘመርለት Hallelujah🙏🙏
You are our blessing hannicho, shine in the Grace of our God
ሃኒ ተባረኪ፡እንደዚ የምስጋና ዝማሬዎች ይብዙልን እ/ር ስለማንነቱ እና ስለ ልጁ ለእኛ ያደረገዉም ሁሌ እሚያስታውሱን፡ያለ ክሊፕ ❤❤❤❤
የጸጋው ባለቤት እግዚኣብሄር የክርስቶስ የሱስ ኣምላኽ እና ኣባት ሃይል ይጨምርልሽ ልምላሜ ይሁንልሽ።
አስቴር አበቤቱ ያወጣቸወን መዝሙር ሳንተገብ ደግሞ ያንቺ መጣ ❤️🙏🏾ተባረኩ ሁለታችሁ እና መስከረም ጌቱ : አዜብ የኔ ምርጦች ናችሁ:: 🙏🏾🙏🏾🙏🏾🙏🏾
#1 ከሙሴ የሚልቅ
#2 ሳሙኤልን እንካ
እስትንፋስ ያለዉ ሁሉ እግዚኣብሄርን ያመስግን 💦💦💦💦 ከዉስጤ እሚፈልቅ ነገር ተሰማኝ መንፈስ ቅዱስ 💦💦💦💦
አንቺን የሰጠን ያህዌ ይባረክ
Praise Lord. This lyrics pointing towards Christ. May lORD bless you!!
በመዝሙሮችሽ እንደት እንምባረክ! ጌታ ዘመንሽን ይባርክ🙏❤
ሀኒዬ በመዝሙርሽ በጣም ተባርኪያለሁ እየተባረኩም ነው ።በእውነት አንችን ለሰጠን ለእግዚአብሄር ክብር ይሁን።ክብር ለጸጋው ባለቤት ለእግዚአብሄር ይሁን ።ሀኒዬ እግዚአብሄር ዘመንሽን ህወትሽን ይባርክ። የማመስገኛ እርሳችን ነሽ።❤❤❤❤❤
ሀኒዬ መዝሙሮችሽ በጣም ነው ሚባርኩኝ እውነት ከልጅነቴ በጣም ነው ምወድሽ ተባረኪ ❤❤ ጌታ አብዝቶ ፀጋን ይጨምርልሽ!!!
ገታ ሆይ ተመስገን በዘመናት በየግዜው የምንበላውን ስላሳጣህን እላለሁ
ሀንቾ ተባረክ❤❤❤❤😂
ስላላሳጣኸን
አውነት ነው እውነት ነው አውነተኛ ወዳጅ የልብ አወቂ እንደ እርሱ ማን አለ???? "ሃንዬ መልኩ በመልክሽ ደስ ይበልሽ አሁንም ጌታ እየሱስ ፀጋ ይጨምርልሽ መዝሙሮችሽ ሁሉ ሠማያዊ ስለሆኑ ብርክ በይ አቅም ጉልበት በርታት ይሠጣል ሠማይ ሠማይ ብቻ የሚሸት የማያውድ ዙፈኑን የሚከብ ሰለሆነ ተባረኪ በክርስቶስ ደም ተሸፈኝ ልጆችሽ በትውልድ ላይ ተፅኖ ፈጣሪ ይሁኑ አሜን..........
"ታላቅ ጌታ የሆነልህ ሰማይ ምድሩ ምስጋናህ"👐👐👐👐👐👐
Huli egizabherin ebarikelew misganawum be afee nw!
THE SONG STRIKES ME........... OH GOD YOU DESERVE OUR HOLY PRAISE..... YOU ARE GOD OF GLORY, MERCY, LOVE, PEACE,................. GOD BLESS YOU MORE AND MORE 💕💕💕💕💕💕
አሜን እጅግ በጣም ድንቅ ዝማሬ እናመሰግናለን እንቁ እህታችን
ተባረክ ባለጸጋው እግዚአብሔር ለዘለዓለም አለም ይባረክ ❤❤❤
wow! yezemershilet fetari yibarksh!
Elelelelele, elelelelele, elelelelele, Amen, Amen, Amen, Amen, Hallelujah, Hallelujah, Praise God! Amazing and beautiful! God bless you more and more!
ወደር ወሰን ስለሌለው ፍቅርህ ጌታ ሆይ ተመስገን። ልብን የሚነካ ዝማሬ ተባረኩ
'' እስትንፋስ ያለው እግዚያብሔርን ያመስግን '' 👌.... ፕሮቴስታንት አይደለሁም ግን በእርግጠኝነት እንዳንቺ መዝሙሮች ደጋግሜ ያዳመጥኩት የለም እረፍት ሰላም ይሰጡኛል የምር ተባረኪ አምላክ በረከቱን ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥሽ ....እግዚአብሔርን እንደማገልገል ያለ ነገር ምን አለ ? በርቺ 🙏
አሜን ጌታ ሆይ ተመስገን ተመስገን ተመስገን ዘማረ ሃና ጌታ ጸጋውን ይቅብዝልሺ
You're our blessing on this very era. ❤
ሀንዬ ተባረኪ !ዘመንሽ ይባረክ ።በቀደሙ ዝማሬዎችሽ ብዙ ጭለማ ቀኖች ተገፈዋል።
እንዴት እንደምወድሽ ❤❤❤ መዝሙሮችሽን በየእለቱ ነው የምንሰማቸው ህይወት አለበት❤❤❤Haniye
ተባረክ በኢየሱስ ስም ፀጋ ያብዛልሽ ይገባል የኔ ጌታ ላንተ ምስጋና ያንስብኃል እንጂ አይበቃም የታረድክልኝ በግ ክብር ላንተ ይሁን አባ🙏🙏🙏
መፅናናት ሊበዛልን ነው ደሞ
ሀኒ እግዚአብሔር አማላክ አብዝቶ ይባርክሽ። ተባርከንበታል.❤
ተባረኪልኝ በጣም ነው ምወድሽ ማከብርሽ። በዝማሬዎችሽ ውስጥ ነፍስሽ የ ፈጣሪን ፊት ለማየት ስትቃትት መመልከትን ብቻ ሳይሆን እኔም ወደዚያው ዘው ብዬ እንድገባ ስለሚቀላቅለኝ ጌታን በማክበር ነፍሴአብራ ስለምትዘምር ነው ተባረኪልኝ የምለው።
ድንቅ መዝሙር ተባረኪ ሀኒዬ ስላቺ እግዚአብሔር አምላክ ይመስገን ❤❤❤❤❤
Hannicho you know that you are one of my Favorite singer really I thank you for the new and the rest of old Album be blessssssssssssssed!
ሃና በመዝሙሮችሽ በጣም ተበርካለው ጌታ ዘመንሽን ይባርክ 🥰🥰
🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣ምን ልበልህ ይብዛልህ
አሜን 🙏🙏🙏 ማለዳችንን ለእርሱ እንድናደርግ ጌታ ይርዳን እህታችን ተባረኪ
ለንጉሡ ክብር ይሁን።
ብሩክ ሁኚ ሀኒ❤❤
እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመሰግነዋለሁ ብዙ ተደርጎልኛል ጌታ ኢየሱስ ይባርክሽ ለምልኝ❤❤❤❤❤❤❤
“....teaching and admonishing one another in psalms and hymns and spiritual songs, singing with grace in your hearts to the Lord.”
- Colossians 3:16 (KJV)
Hanniye, be blessed... you are our blessing... 🙏😇
እግዚአብሔር ሆይ ስለ ሀንቾ ተባረክ ❤❤
እግዚአብሔር ሆይ ስለ ስምህ ምስጋና አበዛለሁ ለኔ ብዙ ሆኖልኛል በአንተ .....
Hani, I have been blessed by your gift since I accepted Jesus as my personal savior, oh, you are our gift from God.
ሀኒቾ ጌታ አብዝቶ ይባረክሽ ዘመንሽ ይባረክ በዝማሬዎችሽ ተባርክያለው በጣም ደስ ብሎኛል ፀጋውን ያብዛልሽ
God bless you hani. Lets go to worship fire
ማለዳዬን በዚህ ዝማሬ ጀምሪያለው 🥰
ተባረክ የኔ ጌታ🙏 ሀኒዬ ዘመንሽ ይባረክ❤❤❤
ማለዳዬን በምስጋና ስጀምር ❤
ብሠማው ብሠማው አልጠግብ አልኩ ተባረኪ የዝማሬው ፀጋ ይብዛልሽ በቃ ነፍስ አልቀረልኝም❤❤❤❤❤
ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክሽ ውድ እህታችን❤❤❤❤
አሜን አሜን አሜን ታባርክ ❤
Are hana betam enwedeshalen❤tebareki
I couldn’t stop listening and crying and singing at the same time.
የአባቴ ብሩክ የጌታ ፀጋ ይብዛልሽ።
Not just a song ; Soaked in and Powered by the Holy Spirit.
ሀኒቾቴ ተባረኪልን በጌታ በጉጉት ማለቄ ነው ሙሉውን ልቀቂልን በጣም ነው የምወድሽ እና የኔ feverit ዘማሪ ነሽ ባንቺ መዝሙሮች ታሪክ አለኝ እና በጌታ አሁንም በጉጉት እየጠበቅንሽ ነው ተባረኪ
Hanichoyee የኔ ልዮ ድንቅ ዘማሪ እግዚአብሔር ከዚህ በላይ ፀጋውን ያብዛልሽ ዘላለም ተባርከሽ ቅሪ
Hanna teke የዚህ ትውልድ በረከት🖤🖤🖤
የኔ እናት ለዚህ ያበቃሽ ጌታችን ስሙ ይባረክ። ከልጅነነቴ ጀምሮ እያዳመጥኩሽ ነው ያደኩት ለዛም ነው የኔ እናት ምልሽ ይሄ ድንቅ አልበም ነው የሚሆነው ጌታ ይባርክሽ አብዝቼ ነው ምወድሽ ❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉
ሃኒቾ ተባረኪ ለሊቶችሽ በዝማሬ ይሞሉ ❤❤❤በማለዳ ምሰጋናዬን አበዛለሁ ❤❤ አሜንንንንን
ዘመንሽ ይባረክ።ፀጋውን አብዝቶ ይጨመርብሽ