የሽንግልስ ቫይረስ ክትባት ምንድን ነዉ?

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 29 ส.ค. 2024
  • የሽንግልስ ክትባት ምንድን ነዉ?
    የሽንግለስ ክትባት በሽንግልስ ቫይረስ ሰበብ የሚከሰት በሽታን የሚከላከል ክትባት ነዉ።
    የሽንግልስ ቫይረስ በሰዎች ቆዳ ላይ ዉሃ መሰል ፈሳሽ በመቋጠር እና ስፍራዉን በማቅላት በሰዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም የሚያስከትል ቫይረስ ነዉ። ይህ ቫይረስ ከችክን ፖክስ -chickenpox ጋር ተቀራራቢ ምልክት አለዉ። የሽንግልስ ቫይረስ ለበርካታ ሳምንታት ሳይድን በሰዎች ላይ ልቆይ ይችላል። ቫይረሱ ለወራት የሚቆይ የነርቨ ህመም በሰዎች ላይ ልያስከትል ይችላል።
    የሽንግልስ ቫይረስ ክትባት መከተብ ልምን ያስፈልጋል?
    እድመዎ ከ18 አመት በላይ ሆኖ በህመም ምክኒያት የአካል ንቅለ ተከላ ለማድረግ ተገደዉ ከሆነ፤ ንቅለ ተከላዉን ከማከናዎንዎ በፍት የሽንግልስ ክትባት መከተብ አስፈላጊ ነዉ።
    እድመዎ ከ50 አመት በላይ ከሆኑም ክትባቱን መከተብ ፋይዳዉ የጎላ ነዉ።
    የሽንግልስ ክትባት በሁለት ዙሮች የሚስጥ ሲሆን፤ ሁለተኛዉ ዙር ክትባት የመጀመሪያዉን ክትባት ከተከተቡ በኋል ከ2 ወር እስክ 6 ወር ባለዉ ጊዘ ዉስጥ መከተብ ይኖርቦዎታል።
    የሽንግልስ ክትባት እንዳይከተቡ የሚመከሩ ሰዎች እነ ማን ናቸዉ?
    ነፍሰ ጡር እናቶች ይህን ክትባት እንዲከተቡ አይመከሩም።
    አንዲሁም ለሽንግለስ ቫይረስ ክትባት አላርጂ ያላቸዉ ሰዎች ባይከተቡ መልካም ነዉ።
    የሽንግልስ ክትባት ይጎኒዮሽ ጉዳቶችስ ምን ምን ይሆኑ?
    የሆድ ህምም፤ የትዉከት ስመት
    ክትባቱን የተወጉበት ስፍራ ማበጥ እና መቅላት
    የድካም ስመት፤ ራስ ምታት፤ የሰዉነት ሙቅት መጭመር እና የብርድ ስመት ተጥቃሽ ናቸዉ።
    እነዚህ ምልክቶች በቀላሉ የሚሻሉ ይሆናል።
    የተለዬ የህመም ምልክቶችን ካስተዋሉ ግን በአስቾካይ ወደ ህክምና ተቋማት መሀድ ተገቢ ነው።
    በካናዳ ሃገር አልበርታ፣ ፣ ሰሳክቹዋን፤ ኦንታሪዮ እና ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ግዛቶች የሚኖሩ ወላጆች በ 811 ነፃ የስልክ መስመር እንዲሁም በማኒቶባ የሚኖሩ ከሆነ ደግሞ 204 788 8200 በመደወል ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
    ለተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች በተዘጋጀ የስልክ መስመር 1-833-906-4357 በመደወልም አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
    እንዲሁም የግል ህኪምዎ ጋር በመደወል የምክር አግልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
    ይህ መልእክት የሚተላልፍላቸሁ አክሽን ፎር ሂዩማኒቲ ከካናዳ የማህበረሰብ ጤና ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነዉ።

ความคิดเห็น •