ዳንኤል 11 ጸረ ክርስስቶ ~ ፓስተር አስፋው በቀለ www.operationezra.com

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 21 พ.ค. 2020
  • እኔም በሜዶናዊ በዳርዮስ መጀመሪያ ዓመት አጸናውና አበረታው ዘንድ ቆሜ ነበር።
    2 ፤ አሁንም እውነትን አሳይሃለሁ። እነሆ፥ ሦስት ነገሥታት ደግሞ በፋርስ ይነሣሉ፤ አራተኛውም ከሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል፤ በባለጠግነቱም በበረታ ጊዜ በግሪክ መንግሥት ላይ ሁሉን ያስነሣል።
    3 ፤ ኃያልም ንጉሥ ይነሣል፥ በትልቅ አገዛዝም ይገዛል፥ እንደ ፈቃዱም ያደርጋል።
    4 ፤ እርሱም በተነሣ ጊዜ መንግሥቱ ይሰበራል፤ እስከ አራቱ የሰማይ ነፋሳት ይከፋፈላል። ለዘሩ ግን አይከፋፈልም፥ እንደ ገዛበትም አገዛዝ አይሆንም፤ መንግሥቱ ይነቀላልና፤ ከእነዚህም ለሌሎች ይሆናልና።
    5 ፤ የደቡብም ንጉሥ ከአለቆቹም አንዱ ይበረታሉ፤ እርሱም ይበረታበታል ይሠለጥንማል፤ ግዛቱም ታላቅ ግዛት ይሆናል።
    6 ፤ ከዘመናትም በኋላ ይጋጠማሉ፤ የደቡብም ንጉሥ ሴት ልጅ ቃል ኪዳን ለማድረግ ወደ ሰሜን ንጉሥ ትመጣለች፤ የክንድዋ ኃይል ግን አይጸናም፥ እርሱና ክንዱም አይጸናም፤ እርስዋና እርስዋን ያመጡ የወለዳትም በዚያም ዘመን ያጸናት አልፈው ይሰጣሉ።
    7 ፤ ነገር ግን ከሥርዋ ቍጥቋጥ አንዱ በስፍራው ይነሣል፤ ወደ ሠራዊቱም ይመጣል፥ ወደ ሰሜንም ንጉሥ አምባ ይገባል፥ በላያቸውም ያደርጋል፥ ያሸንፍማል።
    8 ፤ አማልክቶቻቸውንና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎቻቸውን ከብርና ከወርቅም የተሠሩትን የከበሩትን ዕቃዎች ወደ ግብጽ ይማርካል፤ እስከ ጥቂትም ዓመት ድረስ ከሰሜን ንጉሥ ጋር ሳይዋጋ ይቀመጣል።
    9 ፤ ይህም ወደ ደቡብ ንጉሥ መንግሥት ይገባል፥ ነገር ግን ወደ ገዛ ምድሩ ይመለሳል።
    10 ፤ ልጆቹም ይዋጋሉ፤ ብዙ ሠራዊትንና ሕዝብን ይሰበስባል፤ እርሱም ይመጣል፥ ይጐርፍማል፥ ያልፍማል፤ ተመልሶም እስከ አምባው ድረስ ይዋጋል።
    11 ፤ የደቡብም ንጉሥ ይቈጣል ወጥቶም ከሰሜን ንጉሥ ጋር ይዋጋል፤ ብዙ ሕዝብንም ለሰልፍ ያቆማል፥ ሕዝቡም አልፎ በእጁ ይሰጣል።
    12 ፤ ሕዝቡም በተወሰደ ጊዜ ልቡ ይታበያል፤ አእላፋትንም ይጥላል፥ ነገር ግን አያሸንፍም።
    13 ፤ የሰሜንም ንጉሥ ይመለሳል፥ ከቀደመውም የበለጠ ብዙ ሕዝብ ለሰልፍ ያቆማል፤ በዘመናትና በዓመታትም ፍጻሜ ከታላቅ ሠራዊትና ከብዙ ሀብት ጋር ይመጣል።
    14 ፤ በዚያም ዘመን ብዙ ሰዎች በደቡብ ንጉሥ ላይ ይነሣሉ፤ ከሕዝብህም መካከል የዓመፅ ልጆች ራእዩን ያጸኑ ዘንድ ይነሣሉ፤ ነገር ግን ይወድቃሉ።
    15 ፤ የሰሜንም ንጉሥ ይመጣል፥ አፈርንም ይደለድላል፥ የተመሸገችንም ከተማ ይወስዳል፤ የደቡብም ሠራዊት የተመረጡትም ሕዝቡ አይቆሙም፤ ለመቋቋምም ኃይል የላቸውም።
    16 ፤ በእርሱም ላይ የሚመጣው ግን እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፥ በፊቱም የሚቆም የለም፤ በመልካሚቱም ምድር ይቆማል፥ በእጁም ውስጥ ጥፋት ይሆናል።
    17 ፤ ከመንግሥቱም ሁሉ ኃይል ጋር ይመጣ ዘንድ ፊቱን ያቀናል፥ ከእርሱም ጋር አንድነትን ያደርጋል፤ ያረክሳትም ዘንድ ሴትን ልጅ ይሰጠዋል፤ እርስዋም አትጸናም ለእርሱም አትሆንም።
    18 ፤ ከዚህም በኋላ ፊቱን ወደ ደሴቶች ይመልሳል፥ ብዙዎችንም ይወስዳል፤ አንድ አለቃ ግን ስድቡን ይሽራል፥ ስድቡንም በራሱ ላይ ይመልሳል።
    19 ፤ ፊቱንም ወደ ገዛ ምድሩ አምባዎች ይመልሳል፤ ተሰናክሎም ይወድቃል፥ አይገኝምም።
    20 ፤ የዚያን ጊዜም በመንግሥቱ ክብር መካከል አስገባሪውን የሚያሳልፍ በስፍራው ይነሣል፤ ነገር ግን በቍጣው ሳይሆን በሰልፍም ሳይሆን በጥቂት ቀን ይሰበራል።
    21 ፤ በእርሱም ስፍራ የተጠቃ ሰው ይነሣል የመንግሥቱንም ክብር አይሰጡትም፤ በቀስታ መጥቶ መንግሥቱን በማታለል ይገዛል።
    22 ፤ የሚጐርፍም ሠራዊት ከፊቱ ይወሰዳል፥ እርሱና የቃል ኪዳኑ አለቃ ይሰበራሉ።
    23 ፤ ከእርሱም ጋር ከተወዳጀ በኋላ በተንኰል ያደርጋል፤ ከጥቂትም ሕዝብ ጋር ወጥቶ ይበረታል።
    24 ፤ በቀስታ ከአገር ሁሉ ወደ ለመለመችው ክፍል ይገባል፤ አባቶቹና የአባቶቹ አባቶች ያላደረጉትንም ያደርጋል፤ ብዝበዛውንና ምርኮውንም ሀብቱንም በመካከላቸው ይበትናል፤ በምሽጎችም ላይ እስከ ጊዜው ድረስ አሳቡን ይፈጥራል።
    25 ፤ በታላቅም ሠራዊት ሆኖ ኃይሉንና ልቡን በደቡብ ንጉሥ ላይ ያስነሣል፤ የደቡብም ንጉሥ በታላቅና በብዙ ሠራዊት ሆኖ በሰልፍ ይዋጋል፤ ነገር ግን አሳብ በእርሱ ላይ ይፈጥራሉና አይጸናም።
    26 ፤ መብሉንም የሚበሉ ሰዎች ይሰብሩታል፤ ሠራዊቱም ይጐርፋል፤ ብዙዎችም ተገድለው ይወድቃሉ።
    27 ፤ እነዚህም ሁለት ነገሥታት ክፋትን ያደርጉ ዘንድ በልባቸው ያስባሉ፥ በአንድ ገበታም ተቀምጠው ሐሰት ይናገራሉ፤ ነገር ግን ፍጻሜው እስከ ተወሰነው ጊዜ ነውና አይከናወንላቸውም።
    28 ፤ ከብዙም ሀብት ጋር ወደ ምድሩ ይመለሳል፥ ልቡም በተቀደሰ ቃል ኪዳን ላይ ይሆናል፤ ፈቃዱንም ያደርጋል፥ ወደ ገዛ ምድሩም ይመለሳል።
    29 ፤ በተወሰነውም ጊዜ ይመለሳል ወደ ደቡብም ይመጣል፤ ነገር ግን ኋለኛው እንደ ፊተኛው አይሆንም።
    30 ፤ የኪቲም መርከቦች ይመጡበታልና ስለዚህ አዝኖ ይመለሳል፥ በቅዱሱም ቃል ኪዳን ላይ ይቈጣል፥ ፈቃዱንም ያደርጋል፤ ተመልሶም ቅዱሱን ቃል ኪዳን የተዉትን ሰዎች ይመለከታል።
    31 ፤ ከእርሱም ጋር ሠራዊቶች ይቆማሉ፥ መቅደሱንም ግንቡንም ያረክሳሉ፥ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፥ የጥፋትንም ርኵሰት ያቆማሉ።
    32 ፤ ቃል ኪዳኑን የሚበድሉትንም በማታለል ያስታል፤ ነገር ግን አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ይበረታሉ፥ ያደርጋሉም።
    33 ፤ በሕዝቡም መካከል ያሉ ጥበበኞች ብዙ ሰዎችን ያስተምራሉ፤ ነገር ግን በሰይፍና በእሳት ነበልባል በምርኮና በመበዝበዝ ብዙ ዘመን ይወድቃሉ።
    34 ፤ በወደቁም ጊዜ በጥቂት እርዳታ ይረዳሉ፤ ብዙ ሰዎችም በግብዝነት ወደ እነርሱ ተባብረው ይሰበሰባሉ።
    35 ፤ እስከ ተወሰነውም ዘመን ይሆናልና ከጥበበኞቹ አያሌዎቹ እስከ ፍጻሜ ዘመን ይነጥሩና ይጠሩ ይነጡም ዘንድ ይወድቃሉ።
    36 ፤ ንጉሡም እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፤ ራሱንም ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ በአማልክት ሁሉ ላይ ራሱን ታላቅ ያደርጋል፥ በአማልክትም አምላክ ላይ በትዕቢት ይናገራል፤ ቍጣም እስኪፈጸም ድረስ ይከናወንለታል፥ የተወሰነው ይደረጋልና።
    37 ፤ የአባቶቹንም አማልክት የሴቶችንም ምኞት አይመለከትም፤ ራሱንም በሁሉ ላይ ታላቅ ያደርጋልና አማልክትን ሁሉ አይመለከትም።
    38 ፤ በእነዚህ ፋንታ ግን የአምባዎቹን አምላክ ያከብራል፤ አባቶቹም ያላወቁትን አምላክ በወርቅና በብር በዕንቍና በከበረ ነገር ያከብረዋል።
    39 ፤ በእንግዳም አምላክ እርዳታ በጽኑ አምባ ላይ ያደርጋል፤ ለሚያውቁት ክብር ያበዛላቸዋል፥ በብዙም ላይ ያስገዛቸዋል፥ ምድርንም በዋጋ ይከፍላል።
    40 ፤ በፍጻሜ ዘመንም የደቡብ ንጉሥ ከእርሱ ጋር ይዋጋል፤ የሰሜንም ንጉሥ ከሰረገሎችና ከፈረሰኞች ከብዙም መርከቦች ጋር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣበታል፤ ወደ አገሮችም ይገባል፥ ይጐርፍማል፥ ያልፍማል።
    41 ፤ ወደ መልካሚቱም ምድር ይገባል፥ ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ፤ ነገር ግን ኤዶምያስና ሞዓብ ከአሞንም ልጆች የበለጡት ከእጁ ይድናሉ።
    42 ፤ እጁን በአገሮች ላይ ይዘረጋል፥ የግብጽም ምድር አታመልጥም።
    43 ፤ በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ፥ በከበረችም በግብጽ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል፤ የልብያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይከተሉታል።
    44 ፤ ከምሥራቅና ከሰሜን ግን ወሬ ያውከዋል፤ ብዙ ሰዎችንም ይገድል ዘንድና ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ በታላቅ ቍጣ ይወጣል።
    45 ፤ ንጉሣዊ ድንኳኑንም በባሕርና በከበረው በቅዱስ ተራራ መካከል ይተክላል፤ ወደ ፍጻሜው ግን ይመጣል፥ ማንም አይረዳውም።
  • บันเทิง

ความคิดเห็น • 92

  • @SenaitGashaw-bn8rb
    @SenaitGashaw-bn8rb หลายเดือนก่อน

    ፓሰተር ጌታ እየሱስ እድሚ ከጢንጋር እሰከቢሰቦችህ እየሱስ ያብዝልህ እንወድሃለን ሁልጊዜም የተማር ያልተማር በኩል አይን የሚይዪ አባት ከጌታ በታች አላየሁም እኔ የጌታን ፊቅር እለተእለት ይጨምርብኝ የስተርን ትምህርቶች ነዉ እንወድሃለን እኔ ልጂህ ጥምቀትን ተምህሪ ተጠምቄአለሁ ጌታ አብዝቶ ይባርክህ አሜን አሜን አሜን ❤❤❤❤❤

  • @alemayehumechanic6228
    @alemayehumechanic6228 ปีที่แล้ว +1

    ፓስተር 💜💜💜💜💜💜💜

  • @Sebli_mossie11
    @Sebli_mossie11 2 หลายเดือนก่อน +1

    ጌታ ሆይ ይሄን እውነትህን ያስተማረክኝ ያተረፍከኝ እኔ ማን ነኝ😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

  • @tagesechtesema6195
    @tagesechtesema6195 ปีที่แล้ว +4

    አሜን አሜን አሜን ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ፓስተር እግዚአብሔር አምላክ እንደ ባለጠግነቱ ብዛት በሚያስፈልገው ሁሉ ይሙላብህ እድሜን ከጤና ጋር ያብዛልህ ይጨምርልህ

  • @fikiriasefaw6494
    @fikiriasefaw6494 ปีที่แล้ว +2

    ፓስተርዬ እግዚአብሔር ረጅም እድሜ ይስጥህ ዘመንህ ይለምልም በእውነት አንተ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሁሉ ያስነሳህ ነህ ! በጣም ብዙ ነገር ብታውቅም ያልገባህን ነገር ደግሞ አላውቅም ማለትን ከአንተ ተምሬአለሁ እግዚአብሔር የሚያስፈልግህን ሁሉ ይስጥህ ። ፍቅረ አስፋዉ ከቤተ አብርሀም መስያኒክ ኮንግርጌሽን (ቀጨኔ)

  • @mintwabasefa3248
    @mintwabasefa3248 2 ปีที่แล้ว +3

    ፓስተር አስፋው ጌታ እየሱስ ዘመንህን ቤተሰብህን ይባርክ ስለ ድንቅ የአስተምሮት ጥበብ እንድንረዳ አቅልለህ ሳታወሳስብ ስለምታስረዳን እናመሰግንሀለን በአንተ ሆኖ የሚያስተምረን የሚመክረን በእውነት ላይ ፀንተን እንድንኖር የምልጃና የፀሎትን ሀይል አልቃሾች የታሰሩትን በእንባ የሚያስፈቱ ልቤን ነካው አሜን የሚፀልዩ አልቃሾች ይብዙሉን ተባረክ ፓስተርዬ አሜን ካስተማርካቸው ወንጌላውያን ይነሱ አገልጋዮች ይነሱ አሜን ስሙን ተሸክመው የሚኖሩ ይነሱ

  • @DD-hh2qx
    @DD-hh2qx ปีที่แล้ว +1

    ጌታ ይበርክህ አሰተምሮህ የማየጠገብ ነዉ አደራሻህ የሰልክ ቁጥርህን የማገኝበት መ ንገድ ቢኖር ደስ ይለኛል ተከታታይ መማር አፈልጋለሁ ጌታ ይባርክህ

  • @user-nn4vh7qg2g
    @user-nn4vh7qg2g 2 ปีที่แล้ว +3

    ዘመንህ ይባርክ ፓስተር በጣምነው የምወድህ

  • @AbebawuPawulosBelete
    @AbebawuPawulosBelete 2 หลายเดือนก่อน

    last 10 days my life completely changed I bless God for giving such a blessed pastor

  • @hanamamo6648
    @hanamamo6648 ปีที่แล้ว +3

    እግዚአብሔር ይመስገን የእግዚአብሔር ሰላም ጸጋው ይብዛሎት ፓስተርዬ በምያስተምሩት ትምህርት ልቤ በጣም ይጽናናል።

  • @Ova-7311
    @Ova-7311 ปีที่แล้ว +1

    ፓስተር ጌታ ይብዛልህ, ሃለሉያ

  • @kelemuaabera4871
    @kelemuaabera4871 4 ปีที่แล้ว +11

    ወንድሜ ፓስተር ኦስፋው በቀለ ስለአንተ እግዚአብሔር ይመስገን እንዲህ አይነት ቃሉን አጥንተው መርምረው ዋጋ ከፍለህ ቢያመንም እውነቱን የሚያስተምር ሰው መገኘቱ በጣም ትልቅ እድል እድል ነውና አሁንም ጌታ እግዚአብሔር መልሼ አመሰግናለሁ ወንድሜ ፀጋ ይብዛልህ እኔ የጌታ ልጅ ነኝ ግን ግን ደካማ ነኝና ፀልይልኝ ጌታ እንዲረዳኝ እኔም እፀልያለሁ ስለጌታዬ እየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ማወቅ ና መቅረብ እፈልጋለሁ ወንድሜ ተባረክ ቤተሰብ ሁሉ ይባረክ ለምልምን ብዙዎችችን በምታስተምረው ትምህርት ከሳትንበት ወደ እውነቱ እንመለስ ከሲኦል እንድናመልጥ ጌታ የሱስ ይጠቀምብህ ስለ ጌታ አከብርሐለሁ አዲስ ተማሪ ።

  • @herutkejebokejebo7338
    @herutkejebokejebo7338 2 ปีที่แล้ว +1

    አሜንንንንንንንንን,አሜንንንንንንንን✅✅👍👍ጌታ,ይመስጌን ዘመንህ ቤተሰብህ ህይወትህ ሁሉ ይባረክ

  • @calebtariku8859
    @calebtariku8859 ปีที่แล้ว +1

    ዘመንህን እግዚአብሔር ይባርክ። የክርስትና እይታዬን 360 ድግሪ ቀይሮታል ትምህርቶችህ። አመሰግናለው

  • @zedasefa1687
    @zedasefa1687 10 หลายเดือนก่อน

    amen amen amen beysus seme amen pastor gita segawen yabzalek lemelemilegn

  • @user-vh1rh5qh8p
    @user-vh1rh5qh8p 4 หลายเดือนก่อน

    GOD BLESS U PASTOR,LET HIM GUIDE AND PROTECT US ALL

  • @natnaeltilahun5694
    @natnaeltilahun5694 2 ปีที่แล้ว +1

    Geta yebrkr pastor

  • @ishmaeldassa8268
    @ishmaeldassa8268 4 ปีที่แล้ว +3

    ጌታ ይባርክህ መጋቢ አስፋው ቃሉን በትኩረት ስሰማ ውስጤ ይታጠባል ጸሎትህም ፈውስ ሁኖኛል እውነቱን ማን ያሣየናል የሚሉ ብዙዎች ናቸው እድሜና ጤና ይስጥህ ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ጉዌልፍ ኦንቴርዮ

  • @hiromigs6044
    @hiromigs6044 4 ปีที่แล้ว +4

    🎀ድንቅ መምህር ኖት ! እግዚያብሔር አምላክ ይባርኮት እርሶንና የርሶ የሆኑትን ሁሉ በእርሱ ይባረክ ይጠበቅም ከዚህም በላይ የወንጌሉን እውነት የሚናገሩበትን ፀጋ የፀጋው ባለቤት እርሱ ብሩኩ እግዚያብሔር ፀጋውን ይጨምሩሎ
    ፀጋ ከ እርሶ ጋር ይሁን ብሩክ ኖት!

  • @josicycle
    @josicycle 10 หลายเดือนก่อน

    Geta eyesus yebarkeke pastor betam Geta be Anet eyetekemegn new

  • @ershayetadesse1181
    @ershayetadesse1181 2 ปีที่แล้ว +1

    you are blessed

  • @user-lf8zg2kn9d
    @user-lf8zg2kn9d 10 หลายเดือนก่อน

    እግዚአብሔር ይባርክህ❤❤❤❤

  • @hannagg5688
    @hannagg5688 ปีที่แล้ว

    Amen❤

  • @mershayedejene4692
    @mershayedejene4692 3 ปีที่แล้ว +1

    ፕስተር በእነም ዘመን አንትንና አንተን ያላሳታኝን አምላከን እግዝያብሄሪን ሁል ግዜም ለዘሌአለምም አከብረለው አመሰግናለሁ እለምነዋለው ደግሞሚ ከዝህ በላይዪጨምርልህ ተባረክ እንዎድሀለን ተባረክ

  • @helentsehaye88
    @helentsehaye88 4 ปีที่แล้ว +3

    ጌታ ዘመንህን ይባርክ ብዙ ጥያቄዎቼን የመለሰ ትምርት ነው you tube ላይ shear ማድረግህ በብዙ ጠቅሞናል ነብስ አልቀረልኝም ወርቅ የሆነ ግዜ ነው ለኔ ፀጋ ይጨምርልህ ወንድሜ።

  • @kidilove1715
    @kidilove1715 3 ปีที่แล้ว +2

    እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ፓስተር

  • @yegledemissie9469
    @yegledemissie9469 4 ปีที่แล้ว +5

    May God blease you Brother Asfaw Bekele thank you for everything you do

  • @Abebechwada-he2xf
    @Abebechwada-he2xf 8 หลายเดือนก่อน

    Tebarek

  • @genettekle4477
    @genettekle4477 3 ปีที่แล้ว +1

    ጀግና ያቤቴ ልጅ

  • @Mercylovefaith
    @Mercylovefaith 4 ปีที่แล้ว +2

    የምንነቃበት ግዜ ነው እግዚአብሔር አይኖቻችንን ይክፈት ጠላት አፍጦ አየሰራ ቤቴክርስትያን በአዚም መሆና ይገርማል ከጸሎት ከቃሉ ይቅር ወሬ ጌታ ሆይ እርዳን አካልህን በመንፈስ ቅዱስ እሳት አቀጣጥሉት

  • @sisuabate4756
    @sisuabate4756 4 ปีที่แล้ว +2

    Geta yebarkh pastor hayel tekbyalew besloth amen amen amen engan bebarkbet berket betef tebark

  • @salameskyas3437
    @salameskyas3437 3 ปีที่แล้ว +1

    የተባረክ ፓስተርዬ

  • @asgdom7944
    @asgdom7944 4 ปีที่แล้ว +2

    ተባረክ

  • @abebatanga7958
    @abebatanga7958 3 ปีที่แล้ว +1

    ተባረክ ፓስተር።

  • @eliastadesse7333
    @eliastadesse7333 2 ปีที่แล้ว +1

    ye Egzabhare sew Gata yebarekot ,,

  • @elbeteledilu5380
    @elbeteledilu5380 3 ปีที่แล้ว +1

    geta Eyesus yibarkh pastorye!

  • @raheltadsse789
    @raheltadsse789 4 ปีที่แล้ว +2

    God bless you Paster tasifeligenalek edima tana yistik

  • @bbhuhh5737
    @bbhuhh5737 3 ปีที่แล้ว +1

    Zemenhi tbareki pastorey Ameeeeeen Ameeeeeeen geta yibareki sile Ante tsaga yibzalhi🙌🙌🙌🙌

  • @atsedezegeye457
    @atsedezegeye457 4 ปีที่แล้ว +2

    አሜን ተባረክ

  • @raheladane9232
    @raheladane9232 4 ปีที่แล้ว +3

    ጌታ ይባርክህ

  • @nishanraday7062
    @nishanraday7062 4 ปีที่แล้ว +1

    ፓስተር አሰፍው ጌታ ይባርክህ

  • @jossy2003
    @jossy2003 2 ปีที่แล้ว +1

    God bless you my true brother in Christ!

  • @greeceathens9187
    @greeceathens9187 3 ปีที่แล้ว +1

    Amennnnn

  • @tsehayegetachew4599
    @tsehayegetachew4599 3 ปีที่แล้ว +1

    WOW you are great anointed teacher god bless you for ever🙏🙏🙏✝️🧎‍♀️

  • @meazadaniel6260
    @meazadaniel6260 3 ปีที่แล้ว +1

    Pestor Asfawe endete lagnhe ehllu mashfun lmgzat. Bless you and your family.

  • @yohsnesalula5372
    @yohsnesalula5372 4 ปีที่แล้ว +1

    Pastor God bless you and keep you 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @weinitsadik7115
    @weinitsadik7115 4 ปีที่แล้ว +1

    Pastor geta yebrkeh betam bezu terminal geta zemanh ena heiweth yebrka 🙏🙏

  • @raheltsehaye1852
    @raheltsehaye1852 3 ปีที่แล้ว +1

    Geta yebarkeh

  • @abrahammelese7607
    @abrahammelese7607 3 ปีที่แล้ว +2

    በነብዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኵሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል ማቴ 24፥15

  • @fikirtea.9256
    @fikirtea.9256 4 ปีที่แล้ว +4

    May God help you!!!!

  • @belayberihun8130
    @belayberihun8130 4 ปีที่แล้ว +2

    Thankyou.

  • @tsegeredayemane3640
    @tsegeredayemane3640 4 ปีที่แล้ว +2

    God bless you

  • @Jesus-bp3bv
    @Jesus-bp3bv 4 ปีที่แล้ว +3

    Wow on time.......
    May God bless you all your family!!

  • @meseretworkureta8723
    @meseretworkureta8723 3 ปีที่แล้ว +1

    Amen. Tebarek

  • @meazadaniel6260
    @meazadaniel6260 3 ปีที่แล้ว +1

    GETA YBRKH Tbarke

  • @Mercylovefaith
    @Mercylovefaith 4 ปีที่แล้ว +1

    ጌታ አየሱስ አብዝቶ ይባርክህ

  • @almaznegash1889
    @almaznegash1889 3 ปีที่แล้ว +1

    Yebarekhe

  • @asfawgezahagne6866
    @asfawgezahagne6866 3 ปีที่แล้ว +1

    Asfaw Kebede from Long Beach CA.

  • @hirutfeyisa4080
    @hirutfeyisa4080 4 ปีที่แล้ว +1

    Pastor geta tsegawn yabzaleh nurlen tebarek

  • @higdefshiftahager7129
    @higdefshiftahager7129 3 ปีที่แล้ว +1

    Bless you more our dear brother 🙌

  • @iam78782
    @iam78782 4 ปีที่แล้ว +2

    Bless u pastor

  • @yergalemtereda938
    @yergalemtereda938 4 ปีที่แล้ว +2

    Amen Amen Amen !!! antem tebarek

  • @meseretworkureta8723
    @meseretworkureta8723 3 ปีที่แล้ว +1

    May God bless you and your family...

  • @Mercylovefaith
    @Mercylovefaith 4 ปีที่แล้ว +1

    Amen

  • @sinanusinanu6457
    @sinanusinanu6457 4 ปีที่แล้ว +3

    Blessed you pastor

  • @yordanosdotti4876
    @yordanosdotti4876 4 ปีที่แล้ว +1

    Wow was listening for many hours your teaching amazing teacher
    God bless you

  • @ArsemaVlog
    @ArsemaVlog 3 ปีที่แล้ว +1

    Glory to GOD !!!!!!!

  • @tayeterefe779
    @tayeterefe779 4 ปีที่แล้ว +1

    waw GODBLESS brother

  • @aseralemu6113
    @aseralemu6113 3 ปีที่แล้ว +1

    Pastor edme yisithe

  • @user-jn4cc3wn2j
    @user-jn4cc3wn2j 3 ปีที่แล้ว +1

    Negash Adugna in isreal

  • @dagitamirat21
    @dagitamirat21 5 วันที่ผ่านมา

    Pastor geta amelaki yibarik tsega yibezale ka talake akiberot ga ande teyake alegn ba Isaiah 43 veres 3 please abiraralen thank you pastor

  • @user-jn4cc3wn2j
    @user-jn4cc3wn2j 3 ปีที่แล้ว +1

    ሰላምታየ ይድረስ ለፓስተር አስፋው በቀለ
    እኔ ኢትዮጺያ እያለሁ ክርስቶስ ከቤቴ ገብቶ
    ተገልጦልኛል 1983 ዓ፣ም በኢትዮ አቆጣጠር ሲሆን በእስራኤል ሀገር ነው የምኖረው አሁንም በምኖርበት ቅድስት ሀገር
    ከምስክር ጋር መጥቶ የምነግርህን ሥማ፡ብሎ ከሁለቱ ፡ አንዱ ፡ተናግሮኝ፡ወጡ።
    ሦስተኛው ፡ዕራይ፡2017 ዓ፦ም በሮፓ አቆጣጠር ፡እንዲህ አለኝ፡ ዘፍ፡ም 7 ቁጥር 12 የሚል ቃል ተነገረኝ
    በ2020 የታሪኩ ምራፍ በኮሮና ተጀመረ።

    • @asfawBekelepastor
      @asfawBekelepastor  3 ปีที่แล้ว

      ጌታ ህያው ነው፤ የሚናገርና የሚያደርግ እርሱ ነው!

  • @abrahammelese7607
    @abrahammelese7607 3 ปีที่แล้ว +1

    ነገር ግን የኃለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን 1ቆሮ 15፥51-52

  • @masetewalyenuren4078
    @masetewalyenuren4078 4 ปีที่แล้ว +1

    Amennn Amennn tebarek yabzalih

  • @habtayaron9542
    @habtayaron9542 ปีที่แล้ว +1

    selam you teaching good about intchris , let tell who are they ,they live in toronto they are spanish the women name is judith mendoza her hasbound l dont know ,but two of them live in toronto ,u will soon

  • @abrahammelese7607
    @abrahammelese7607 3 ปีที่แล้ว +1

    ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ አይደርስምና ? ንጥቀት 2ተሰ 2፥3

  • @ketselayirefu7710
    @ketselayirefu7710 4 ปีที่แล้ว +2

    Pastor Asfaw Geta yebarkeh tsegawenyabzaleh

    • @tesfayediriba2205
      @tesfayediriba2205 4 ปีที่แล้ว

      Bless you abundantly pastor!!! I am following all your services and all are so interesting and useful!!!

    • @meronehabtom1985
      @meronehabtom1985 4 ปีที่แล้ว

      God Bless you all familie paste

  • @user-bb8gz9fd8c
    @user-bb8gz9fd8c 7 หลายเดือนก่อน

    ዳውሎድ ለማድረግ እምቢ እያለኝ ነው ቪዲዮው ኢሜል ምናምን የለኝምና አስቸጋሪ ባይሆንብን ጥሩ ነው

  • @abrahammelese7607
    @abrahammelese7607 3 ปีที่แล้ว +1

    1ኛተሰ 4፥16- ንጥቀት አለ ግን ምንም ማከራ አናይምን ?

  • @haileyesusad7879
    @haileyesusad7879 4 ปีที่แล้ว

    Do you believe?

    • @ishmaeldassa8268
      @ishmaeldassa8268 4 ปีที่แล้ว

      Do you believe? About what? What did you mean by that?

    • @haileyesusad7879
      @haileyesusad7879 4 ปีที่แล้ว +1

      Sorry, that was typed and sent incomplete. I don't remember how I wrote that. Thanks!

  • @Abebechwada-he2xf
    @Abebechwada-he2xf 8 หลายเดือนก่อน

    Tebarek

  • @eyesusfikir9501
    @eyesusfikir9501 4 ปีที่แล้ว +3

    God bless you

  • @tayeterefe779
    @tayeterefe779 4 ปีที่แล้ว +1

    waw GODBLESS brother

  • @greeceathens9187
    @greeceathens9187 3 ปีที่แล้ว +1

    Tebarek