የእየሱስ ክርስቶስን ስዕለ አድኖውን በአህያ ላይ አድርገው በቤተል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን / ሆሳዕና_🌿እንኳን አደረሳችሁ!!🌿

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 10 ก.ย. 2024
  • ††† ሆሳዕና በአርአያም †††
    የዐብይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት ሆሳዕና ተብሎ ይጠራል።ሆሳዕና ማለት፦የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም፦ መድኃኒት እባክህ አሁን አድን፥አሁን ባርከን ማለት ነው።(📖ማቴ፦፳፩፥፩-፲፩/21፥1-11)
    «የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ሆሳዕና በአርአያም እያሉ ይጮኹ ነበር»(📖ማቴ፦፳፩፥፱/21፥9)
    እስራኤላውያን በዕለተ ሆሳዕና ለምን ዘንባባ ይዘው
    ዘመሩ?"ዘንባባ፡-
    ፩, ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል (የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
    ፪, ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ
    ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
    ፫, ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው።
    ፬, ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
    ፭, ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው።
    ፮, ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳዕና
    በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡
    ወ ሥብሐተ ለእግዚአብሔር!
    ወ ለወላዲቱ ድንግል!
    ወ ለመሠቀሉ! ክቡር
    ፮/፰/፳፻፲፬/07/08/2014 ዓ.ም

ความคิดเห็น • 14