ፍቅረማርቆስ በእንባ አራጨን እኮ 😢 የሚሳም ተራራ የተሰኘውን አዲስ መፅሐፉን ለመጀመሪያ ጊዜ በአትላንታ ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ በተገኘበት መፅሐፉን አስመረቀ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 3 ม.ค. 2025
  • የፍቅረማርቆስ ደስታ ሙሉ ቃለ መጠይቁን ⬇️
    • ፍቅረማርቆስ ደስታ
    የተወዳጁ እና የበርካታ መፅሐፍ ደራሲ የሆነው ፍቅረማርቆስ ደስታ ስኬቱን ሳይሆን ውድቀቱን ”የሚሳም ተራራ“ በተሰኘውን አዲስ መፅሐፍ በሎሬት ኪነጥበባት ማዕከል ባዘጋጁት ዝግጅት ላይ ከአንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ በተገኘበት በአማረ ሁኔታ Sunday April 07, 2024 አስመርቆአል።
    "ትናንታችን ውስጥ ያለፍነው ዛሬ አለ፤ ነጋችን ውስጥም ዛሬ ሕያው ሆኖ ይኖራል። በሕይወት ዑደት ሽቅብ ቁልቁል እንወጣለን፣ እንወርዳለን፣ እናጣለን፣ እንቀበላለን . . .ፀሐይ ትገባለች፣ ትወጣለች - ሰዓቷን ጠብቃ በዛቢያዋ ላይ እየተሽከረከረች! ትናንታችን ዝምታም ነው - አጠንክሮን፣ አስተምሮን የሚያልፍ፤ ዘወር ብለን ስናየው በዐይናችን የምንስመው . . . የምንዘክረው!" የሚሳም ተራራ
    አንጋፋው ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ የሐመር ሕዝብ ባህል ላይ ባተኮሩት እጅግ ተወዳጅ በሆኑት ተከታታይ ‘ኤትኖግራፊክ’ ልብወለድ ድርሰቶቹ ይታወቃል። አሁን ደግሞ “የሚሳም ተራራ” የተሰኘ ድንቅ መጽሐፉን ለበርካታ ዓመታት በጉጉት ሲጠብቁ ለነበሩት አንባቢዎቹ ይዞ ቀርቧል። በዚህም የግለታሪክ መጽሐፉ ፍቅረማርቆስ የሕይወት ጉዞውን ትዕይንታዊ በሆነ ውብ ቋንቋ በመተረክ የትዝታ ብልጭታዎቹን (ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ፣ ከልጅነት እስከ ጐልማሳነት) ሳይሰስት ያጋራናል።
    #artstvworld #ebstvworldwide #ethiopian ##atlanta
    Get the book at :
    a.co/d/2TMoUDA

ความคิดเห็น • 69

  • @Abiye723
    @Abiye723 8 หลายเดือนก่อน +16

    ደረጄ❤ ፍቅሬም❤ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ያድላችሁ። ለትውልድም ለሀገርም አርኣያ ምትሆኑ እንቁ የጥበብ ሰዎች

  • @zewduyadete7631
    @zewduyadete7631 7 หลายเดือนก่อน

    ፍቅረ አንኩዋን ደስ አለህ!!!!

  • @kidistlemma1016
    @kidistlemma1016 8 หลายเดือนก่อน +5

    ደሬ ምርጥ ሰው ነው::ተጠግታችሁ ብታውቁት አይጠገብም::ምርጥ ጏደኛ ደራሽ ወንድም ሲወድ ጥግ ድረስ በቃ ከቀረበህ እንደዚህ ነው::ስለማውቀው እኮራለሁ ምርጥ ወንድም አለኝ::ደርዬ እድሜህ በደስታ ይለቅ::የሰው ልብ ታክማለህ::ልዩ !!!

  • @tselatadnew4567
    @tselatadnew4567 8 หลายเดือนก่อน +3

    ፍቅረማርቆስ እድሜና ጤና ይስጥህ

  • @oa4682
    @oa4682 7 หลายเดือนก่อน

    ድንቅ ታሪክ ነው ፣ይህ ታሪክ በፊልም መሰራት አለበት ለሌሎች ማስተማሪ ይሆናል።

  • @meseretbarke9195
    @meseretbarke9195 8 หลายเดือนก่อน +2

    እጅግ የማደንቀው ደራሲ ዕእድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ አንድ ጊዜ አዲስ አበባ 22 አካባቢ 1998 ፊርማ ፈርሞልኛል እስካሁንም አስቀምጬዎለው አከብርሓለው ኑርልን ❤❤❤

  • @tarikuterefe2386
    @tarikuterefe2386 8 หลายเดือนก่อน +6

    ድንቅ ነው !!..መፅሐፉ ገና ከጅምሩ እሚቀመጥ አይደለም:: ፍቅሬ ቀሪ ዘመንህ የተባረከ ይሁን::

  • @AmsaluKz-zl1bo
    @AmsaluKz-zl1bo 7 หลายเดือนก่อน

    ምርጥ ሰው

  • @derejebekele8641
    @derejebekele8641 8 หลายเดือนก่อน +6

    ፍቅረማርቆሰ እግዚአብሔር ረጅም ዕደሜና ጤና ይሰጥህ።እናመሰግናለን ።

  • @gezegeta923
    @gezegeta923 8 หลายเดือนก่อน +3

    የሚቆጨኝ ከሀገር መራቅ ምን ያህል ብዙ ነገር እንደሚያስቀር ነው፥፥ ይሄ ስራ ሀገር ቤት ብሄራዊ ቲያትር በሽህወች ሰው ተገኝቶ፣በትልቅ መድረክ በተመረቀ ነበር፥፥ ግን ስደት መከራ ነው፥፥ በትንሽ ክፍል፣ባሉት ሰወች፣በጠባብ ክፍል ይመረቃል፥፥ ይሁን ካለማድረግ በብዙ እጥፍ ይሻላል፥፥ እናመሰግናለን፥፥ ሀገራቺን ሰላም ሲሆን ሁሉም በሀግር ደስ ይላል፥፥ አንድ ቀን፥፥

  • @HadasGebregziabhair
    @HadasGebregziabhair 8 หลายเดือนก่อน +5

    I have never seen honest man like ato Fikremarkos, he is brilliant and strong guy, tks a lot afro link

  • @getahunterefegemechis2662
    @getahunterefegemechis2662 8 หลายเดือนก่อน +2

    "እንደ አለመታደል ሆኖ አብዛኛዎቻችን ጥሩ ሰዎች አይደለንም ግን ጥሩ ሰዉ መሆን እንችላለን "

  • @dessalegnwonbarga2144
    @dessalegnwonbarga2144 8 หลายเดือนก่อน

    ዋው !!!!!! እጅግ አስደናቂ ነው ደሬ ክበርልን ዶ/ር እንዳለጌታ እንዳለውው ተራራ የሆነውን ሰው ስላቀረብክልን እናመሰግናለን መፅሀፉ በእርግጠኝ አነበዋለሁ ቤተሰቦቼም ያነቡታል

  • @abiykebede3019
    @abiykebede3019 8 หลายเดือนก่อน +1

    Woy Gud! Gash Fikremarkos! I am so happy to see your journey turning where you are today! You are such an amazing, humble, and kind person! May God bless you with more success 🙏

  • @asfawabebe9035
    @asfawabebe9035 8 หลายเดือนก่อน +2

    Lalombe (FikreMarkos Desta) my favorite writer congratulation.

  • @kingsolomon9771
    @kingsolomon9771 7 หลายเดือนก่อน

    I don’t know what word can express my feelings for your amazing works. But congratulations 🎉🎉❤even after all this hard time. Never give up and you are so human. Hope to see you with more works.

  • @YosefAdmasu-i1c
    @YosefAdmasu-i1c 8 หลายเดือนก่อน

    እግዚአብሔር ያሳድጋት

  • @HadasGebregziabhair
    @HadasGebregziabhair 8 หลายเดือนก่อน +5

    Afro link for me you are no. 1 TH-camrs, all your video it's almost a class specially for the young generation, great job and well-done

    • @AfroLink-ATL
      @AfroLink-ATL  8 หลายเดือนก่อน

      Wow, thank you!

  • @anteneh41
    @anteneh41 8 หลายเดือนก่อน +3

    ደሬ እና ፍቅረ ዋው

  • @HadasGebregziabhair
    @HadasGebregziabhair 8 หลายเดือนก่อน +3

    Wow and wow afro link you are always amaze me, I really appreciate all your amazing video specially today i have no word about this video, I can't even stop crying, I like fikre and Dereje haile too, great job and well-done afro link I really appreciate all your video, amazing

  • @HadasGebregziabhair
    @HadasGebregziabhair 8 หลายเดือนก่อน +7

    Ato Fikremarkos I can't even stop crying, aweraru erasu yaselekesal

  • @Serkalem-mn6zo
    @Serkalem-mn6zo 7 หลายเดือนก่อน

    Egnam enamesegnalen

  • @meseretwako1867
    @meseretwako1867 8 หลายเดือนก่อน

    እውይ.,,❤!!

  • @MelonaTube1223
    @MelonaTube1223 8 หลายเดือนก่อน

    ላሎምቤ🙏🙏🌷

  • @ethiomedia7917
    @ethiomedia7917 8 หลายเดือนก่อน +3

    ፍቅረማርቆስ ደስታ በጣም ጎበዝ ፀሀፊ ነው፣ ውጪ ያለን መፅሀፉን የት እናገኛለን?

  • @asfawabebe9035
    @asfawabebe9035 8 หลายเดือนก่อน +1

    I remember when you and me trying to dig a rabithole in boston leaving our best chances at home . That moment was unforgotable now we both reach to the time of the kissed mountain. Congratulations. Lalombe the gold of hammer.

  • @c2beca272
    @c2beca272 8 หลายเดือนก่อน +2

    ❤❤❤ derya God bless u.

  • @Mery-ey5id
    @Mery-ey5id 8 หลายเดือนก่อน

    ሀበሻ ተሰደህ አያግኝህ፣ ቸግሮህ አያግኝህ የ ባሰ ስሜትህን ይሰባብረዋል

  • @AtlabachewChebud
    @AtlabachewChebud 8 หลายเดือนก่อน

    Touching but educative experience.

  • @eskedartessema6318
    @eskedartessema6318 8 หลายเดือนก่อน +3

    የአጎቴን ቁስል አስታወስከኝ😢😢😢😢 በዛ ውስጥ ስላለፈበት ኡሁሁሁሁሁ እንዴት ያማል

  • @yeshiworkgashu3192
    @yeshiworkgashu3192 8 หลายเดือนก่อน

    I love his reading ( Derege)❤ it will be sad we are loosing those treasures ❤

  • @e4p226
    @e4p226 8 หลายเดือนก่อน

    I have much respect to Fikre

  • @sol.kuku.964
    @sol.kuku.964 8 หลายเดือนก่อน

    ከብስካዉ በስተጀርባን ፍቅረ ማርቆስ ወልዶት ጐሳዬ ተስፋዬ አሳደገዉ። ሁለቱ የማይለያዩ ድንቆቻችን ናቸዉ። ኑሩልን

  • @habtamunegash854
    @habtamunegash854 8 หลายเดือนก่อน

    great!!

  • @seifedinm.6756
    @seifedinm.6756 8 หลายเดือนก่อน +3

    I am at page 80( እሚሳም ተራራ).
    I already cried a couple of times.

    • @Betelhem-i2k
      @Betelhem-i2k 8 หลายเดือนก่อน

      Yet agegnhew?

  • @HirutAntero
    @HirutAntero 8 หลายเดือนก่อน

    ❤❤❤ wow my hero

  • @adonawitsamuel
    @adonawitsamuel 8 หลายเดือนก่อน +2

    ማርክ ... በተመሳሳይ መንገድ አልፈናል። የእኔም ተሞክሮ "እንደገና" ከሚል ርዕስ ጋር በሳምንታት ውስጥ ለአንባቢ ይቀርባል። ከአንተ የእኔ የሚለየው በአንድ ነገር ብቻ ይመስለኛል። አንተ አሁንም እግዜርን ታመሰግናለህ። እኔ ግን እርሱን የማመሠግንበት ቀርቶ ሐልዎቱን የምቀበልበት አንድም ምክንያት የለም። ከልጅነቴ ጀምሮ ሁሉን ትቼ የተከተልኩት እግዜር ለእኔ ግድ እንደሌለው ካረጋገጥኩ 20 አመታት አለፉ። እንኳን እነዛ የመከራ ዘመኖችህ አለፉ።

  • @yisaketeketsel8781
    @yisaketeketsel8781 8 หลายเดือนก่อน

    ከመፀሀፍ.ዉስጥአንድርእስአለያባቴነዉመሰለኘ

  • @dawitkebede1080
    @dawitkebede1080 8 หลายเดือนก่อน

    It is painful.

  • @ኬናን
    @ኬናን 8 หลายเดือนก่อน +1

    ደርዬ እውነት እኔም ምን አለ አጠገቡ በሆንክ ብዬ ተመኘው ተራራውን እስመው ነበር ማንበብና ፍቅር ምን እንደሆነ ከመፅሐፍ ቅዱስ ብኋላ የተገነዘብኩበት ትልቅ ተራራ እንዴት ብዬ ልግለፀው ቃላቶች እንኩን አቅም ያጣሉ እኔ ከዚህ በላይ ምንም ማለት አልቻልኩም 😭😭😭❤

  • @BehailuZeleke-t9x
    @BehailuZeleke-t9x 8 หลายเดือนก่อน

    በጣም ይገርማል መንገድ እና መንገደኛው ያለመገጣጠም ምንም ብዙ አንባቢ ባልሆንም ይህንን ግን የማነበው ይመስለኛል ካልሆንም ለባልቤቴ በስጦታ እሰጠዋልሁ መፅሀፍን ከራሱ ከባለቤቱ ማግኘት ይቻላል? የምኖረው VA ውስጥ ነው

  • @AbdurezakKedir-cg5dh
    @AbdurezakKedir-cg5dh 8 หลายเดือนก่อน

    Jegina!!!

  • @BelayNegash-44
    @BelayNegash-44 8 หลายเดือนก่อน

    አብዛኞቻችን ጥሩ ነን እኮ ጋሽ ፍቅረማርቆስ ጥቂቶቹ ክፉዎች ይሸፍኑታል እንጂ።
    እንደ ተቀፀል አይነት መስዋዕት የሆኑልን ቅን ነፍሶች አሉ። ከ “ያ ትውልድ” ጋ ሆነው ዋጋ የከፈሉ። ግን ዛሬም ደግነታቸውን ያላየን፤ ትንሿ ስህተት ትልቁን አበርክቶ እንዳናየው ስላደረገን።
    እናመሰግናለን! አንተም ከብዙዎቹ ቅን ነፍስ መሀል አንዱ ነህና።

  • @sol7166
    @sol7166 8 หลายเดือนก่อน +2

    Where do I find the Book, here in Northern America?

    • @shalom744
      @shalom744 8 หลายเดือนก่อน +3

      On amazon.

    • @AfroLink-ATL
      @AfroLink-ATL  8 หลายเดือนก่อน +1

      a.co/d/2TMoUDA

  • @heartandsoul4202
    @heartandsoul4202 8 หลายเดือนก่อน

    ከቡስካው በስተጀርባ፣ አቻሜ፣ የዘርሲዎች ፍቅር ካነበብኩለት መፅሃፎቹ በጥቂቱ።

  • @BelayNegash-44
    @BelayNegash-44 8 หลายเดือนก่อน

    እኔም እያለቀስኩ ነው ያነበብኩት።

  • @asfawabebe9035
    @asfawabebe9035 8 หลายเดือนก่อน

    ይብላኝ ለመሠለች።

  • @aman7077
    @aman7077 8 หลายเดือนก่อน

    ❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @tayetessema4908
    @tayetessema4908 8 หลายเดือนก่อน

    ጋዜጠኛ ደረጄ በመድረክ ላይ ከቀረበ ብርቱና ለዘመናት የሚሻገር ቁምነገር አለ። የቋንቋ ጅረት በደረጄ ይፈሳል። ውብና ማራኪ የሀሳብ ልእልና ስነምግባራዊ ሙያነት ይታያል። ደሪ አለባበሱ ሽቅርቆር ፣ግርማ ሞገሱ ልዩ ነው። በሱ ፊት መጠየቅ ውሸትም ኩሸትም ይዞ አይሆንም። ተጠያቂው እራሱን ከሚያውቀው በላይ እሱ አውቆት ከነመረጃው ያቀርባል። አንባቢ በመሆኑ ከመጠየቁ በፊት እራሱን ጠይቆና አሰላስሎ የሚቀርብ ተወዳዳሪ የሌለው ዘመን ተሻጋሪ ጋዜጠኛ ነው። የሚደነቀውን ፍቅረማርቆስ በዚህ መድረክ በሱ መተዋወቁ ተገቢ ነው። ፍቅረማርቆስ አንተም ስምህና ምግባርህ ክቡርና ድንቅ ነው። ገድልህን በፅሁፍ ስራህ ገልጠህ ለኛ አቅርበህልናል።አዲሱ ትውልድ ከዚህ ገድል ከተሞላበት ደራሲ ብዙ ሊማር ይገባል። ሁላችሁም በርክቱልን። እኛንም ልብ ይስጠን።
    እድሜና ጤና ለሁላችሁ።

  • @makiabebe4211
    @makiabebe4211 8 หลายเดือนก่อน +1

    የኢትዮጵያ ነገር እንደዚህ ሆኖ ቀረ በየዘመኑ ይሄን መከራ የሚያሳልፊ ኢትዮጵያ አሁንም በዚህ ዘመን ይሄን አሰቃቂ የጨካኞች መከራ የሚያሳልፊ ኢትዮጵያ አሉ መቼ ይሆን ከዚህ አዙሪት የምንወጣው?

    • @makiabebe4211
      @makiabebe4211 8 หลายเดือนก่อน +1

      ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን
      አባጣ ጎርባጣ ሜዳ ገደሉን
      ማየት ይሻለኛል ኃይልን ከየትአገኝሁ
      ለካስ ኤልሻዳዩ አግዞኝ ቆሚያለሁ።

  • @ethiomediatube7752
    @ethiomediatube7752 8 หลายเดือนก่อน

    💚💛❤🇨🇬😭😭😭💪💪💪💪

  • @tselatadnew4567
    @tselatadnew4567 8 หลายเดือนก่อน

    መጽሐፋ ኢትዮጵየ ገብቷል

  • @Mery-ey5id
    @Mery-ey5id 8 หลายเดือนก่อน

    America kebad hager nw. Wanaw mecheresha telweto megegnetu nw

  • @meseretgebra4421
    @meseretgebra4421 8 หลายเดือนก่อน

    Ere auuuu kal atahu

  • @girmazeleke8819
    @girmazeleke8819 8 หลายเดือนก่อน +1

    በነካ እጅህ የሴራ ፓለቲካ የደም መንበር ደራሲን ያየ ሰው ሽመልስን አቅርብልን አትፍራ

  • @saraamagreedavid6763
    @saraamagreedavid6763 8 หลายเดือนก่อน

    እንዲነበብ መፅሐፍ ይደርሳል አእምሮውም እጁም እድሜ ልኩን ስራ አልፈቱም ውስጡ ያለውን እውቀት አልሰሰተም አልደበቀም ታሪክን ትውፊትን በጣቱ አሻራ አስቀምጦአል ለራሱ ግን ያልኖረ

  • @woldetewolde9193
    @woldetewolde9193 7 หลายเดือนก่อน

    ይህ ኋላ ሰቆቃና ልቅሶ መነሻው ምንድን ነው ብላችሁ ታውቃላችሁ? ጋዜጠኛው ደረጀም ቢሆን መጽሐፎቹን አንብቦ ያቀርባል እንጂ መነሻውና መዳረሻውን። ለምን? አይመረምርም። መልሱ ከኢሕአፓ የጋራ አመራር የሚመነጭ መሆኑን ማን በነገራችሁ ።

  • @asmmmkge
    @asmmmkge 8 หลายเดือนก่อน

    የማይጫን አህያ

  • @TINTAG.S
    @TINTAG.S 7 หลายเดือนก่อน

    አንተ ጊዜ የከዳህ የወያኔ አለቅላቂ ኢትዮጵያ ከስረህ አሜሪካን ታለቀልቃለህ...

  • @asmmmkge
    @asmmmkge 8 หลายเดือนก่อน

    ጌጃ እብድ ውሻ

    • @MulePetros
      @MulePetros 8 หลายเดือนก่อน +3

      አይባልም የአስተሳሰብ ደሃ አትሁን