Logic freshman course chapter 1 የ አዲስ ተማሪወችዩኒቨርሲቲ common course logic

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 3 ก.พ. 2024
  • #Logic
    📚 Logic and Critical Thinking.
    📚 Chapter One - Introducing Philosophy.
    📚 ዛሬ የምንማረው የ Logic and Critical Thinking ኮርስን ነው። ስለ ኮርሱ አንዳንድ ነገር ልበላችሁ።
    📚 ምናልባትም ከመጀመሪያ ሴሚስተር ከባድ ኮርስ ከሚባሉት Logic and Critical Thinking ነው። በዚህ ኮርስ 5 ቻፕተሮችን እንማራለን። ከ 5 ቱ ቻፕተሮች በዋናነት Chapter 2, Chapter 3 እና Chapter 5 ን ለዬት ያለ ትኩረት ሰጥተን እንማማራለን።
    📚 ምክንያቱም Mid exam ፈተናችሁ ላይ Chapter 2 ብዙ ጥያቄ ይወጣበታል። ሰፋ ያለ ማሰላሰል እና ተመስጥኦን የሚጠይቅ የ ፅንሰ ሀሳብ ቻፕተር ነው። Final exam ፈተናችሁ ላይ ደግሞ chapter 5 ላይ ብዙ ጥያቄ ይወጣበታል። ይህ ቻፕተር ደግሞ ፅንሰ ሀሳብንም ሽምደዳንም የሚጠይቅ ወሰብሰብ ያለ ነው። ስለዚህ ሁለቱ ቻፕተሮች ላይ ለየት ያለ ትኩረት ሰጥቼ ለፈተና የሚጠቅማችሁን ነገር እሰጣችሗለሁ።
    📚 ዛሬ Chapter one ንን እንደ መግቢያ መማር እንጀምራለን። ይህ Chapter የ concept ትምህርት እምብዛም አይታይበትም። ፈተና ላይ የምትፈተኑትም በሽምደዳ መልክ ስለሆነ በ MoSHE የተዘጋጀውን PDF ፈተና ሲደርስ ብቻ ሸምድዱት😁 ማለቴ ቃል በቃል አንብቡት ምንም የዞረ ጥያቄ አይወጣበትም። እሺ አሁን ወደ ትምህርቱ። Philosophy ምን አንደሆነ እንመልከት። Philosophy በአማርኛ 'ፍልስፍና' ማለት ነው። ፍልስፍና ማለት ምን ማለት ነው🤔?
    📌 የጥበብ መጀመሪያ ፈጣሪን መፍራት ነው።
    📌 ፍልስፍና ደግሞ ጥበብን መሻት ነው። ስለዚህ ፍልስፍና ከፈጣሪ ህልውና እና ከተፈጥሮ ጋ የሚጋጭ ሳይሆን ስለ ፈጣሪ ና ስለ ተፈጥሮ ምክንያታዊ ዳሰሳ የማድረግ ሳይንሳዊ ሒደት ነው። 😁ስለዚህ ፍልስፍና ሲባል ፈጣሪ ን መቃወም የሚመስለን ልጆች ከዚህ በሗላ ይህንን አስተሳሰባችንን ልንቀይር ይገባል። ለማንኛውም እንደ መግቢያ ያህል እንማረው።
    🌹 Because of its universal nature, it is difficult to define philosophy in terms of a specific subject matter. However, we can define it etymologically as 'love of wisdom‘.
    📚 Philosophy ን ወይንም ፍልስፍናን እንዲሁ በቀላሉ define ማድረግ ወይም ብያኔ መስጠት ይከብዳል። ለምንድን ነው ፍልስፍንናን እንዲህ ነው ብለን መግለፅ ያቃተን🤔?
    📚 ምክንያቱም ፍልስፍና ወይንም Philosophy ሁሉንአቀፍ ወይንም ሁሉንምነገሮች የመዳሰስ ተፈጥሯዊ ባህሪ(universal nature) ስላለው ነው። ይህ ማለት ደግሞ ፍልስፍና specifically አንድ ነገር ለይቶ ማጥናት አይችልም ወይም ስለ አንድ ነገር ብቻ አያጠናም። በዚህም ምክንያት ፍልስፍና(philosophy) ን define ማድረግ ያስቸግራል።
    📚 ነገር ግን አንዱን የ ናቹራል ተማሪ what is chemistry ብዬ ብጠይቀው chemistry is a branch of natural science that studies about the nature and composition of matter ብሎ define ማድረግ ይችላል ምክንያቱም chemistry የሚያጠናው ስለ አንድ ነገር ስለሆነ እርሱም ስለ matter እና ከ matter ጋር ስለተያያዙ ነገሮች ብቻ ነው የሚያጠናው። አንዱን የ ሶሻል ተማሪ what is Geography ብዬ ብጠይቀው define ማድርግ ይችላል ምክንያቱም ስለ አንድ ነገር ስለሚያጠና።
    📚 ነገር ግን ፍልስፍና(Philosophy) ን በዚህ መልክ define ማድረግ ይከብዳል። ስለዚህ በምን መልኩ እናብራራው🤔?
    🌹philosophy(ፍልስፍና) 'philo' እና 'sophia' ከተባሉ ሁለት የግሪክ ቃላት የተመሰረተ ነው።
    👉 Philo ማለት Love ነው።
    👉 sophia ማለት wisdom ነው።
    📚 ስለዚህ የ philosophy ቃል በቃል ትርጉሙ love of wisdom ማለት ነው። Love of wisdom ማለት ደግሞ በአማርኛ "ጥበብን መሻት መፈለግ" ማለት ነው።
    🌹ስለዚህ ከ love of wisdom(ጥበብን መሻት) ተነስተን philosophy ን በተወሰነ መልኩ ማብራራት እንችላለን👇።
    📚 Thus, as a pursuit of wisdom, philosophy refers to the development of critical habits, the continuous search for truth,
    and the questioning of the apparent.
    🌹 ስለዚህ philosophy(ፍልስፍና) ማለት በተለያዩ ነገሮች ላይ ጭፍን አመለካከት ከመያዝ ይልቅ ነቂሳዊ(ምክንያታዊ) አመለካከትን የማዳበር ባህል ÷ እውነትን ያለማቋረጥ የመፈለግ ሒደት ÷ በሰዎች ዘንድ ግልፅ መስለው የሚታዩ ነገሮች ላይ ጥያቄ ማንሳት መመራመር እና በተለያዩ dimensions መመልከት ማለት ነው።
    📚 ነገር ግን እንደ ፋላስፎች እይታ መነፅር ከሆነ love of wisdom የሚለው በቂ አይደለም philosiphy ን ለማብራራት። ለምን🤔?
    📚ምክንያቱም wisdom specific መሆን ስለሚችል። ለምሳሌ አንድ ሐኪም(ዶክተር) ስለ ህክምና በቂ ዕውቀት(wisdom) አለው። ነገር ግን ከህክምና ውጭ ስላሉ ነጠሮች በበቂ ሁኔታ ላያውቅ ላይረዳ ላይመራመር ይችላል። ስለዚህ philosophy ደግሞ ሁሉን አቀፍ ነው ስላልን love of wisdom ብቻውን በቂ definition ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ከ love of wisdom በተጨማሪ philosophy ሌሎች ብያኔዎች(definitions) ይኖሩታል። እነሱን እናያለን ስለዚህ Basic features of Philosophy ን እንመልከት።
    #Logic
    📚 Basic Features of philosophy
    የ Philosophy መሰረታዊ መገለጫዎችን ( Basic features ) ወይንም philosophy ን ከሌሎች የትምህርት አይነቶች የሚለዩትን ባህሪያቱን እንመለከታለን ።
    🌹1) Philosophy is a set of views or beliefs about life and the universe, which are often held uncritically.
    Philosophy ማለት ስለ ህይወት ስለ አለም በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ ጥያቄ የሚያስነሱ ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ ያልተገኘላቸው ጉዳዮች ላይ ያለን አመለካከት ወይም ነፀብራቅ ማለት ነው።
    👉ለምሳሌ ስለ ህይወት ብናነሳ ከሞት በሗላ ህይወት አለ ወይስ የለም😮‍💨?
    👉ገነት ና ሲኦል የሚባሉ ነገሮች አሉ😿?
    👉ፈጣሪ አለ? ይህ የሚታየው ገሀዱ አለም ከየት ነው የመጣው? ወዘተ
    📚 ስለዚህ ስለእነዚህ ነገሮች ያለን ምልከታ philosophy ይባላል። ታዲያ ስለእነዚህ ነገሮች እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ የግል ምልከታ ይኖረዋል።(ሰምታችሁ እንደሆነ አንዳንድ ሰዎች "የኔ ፍልስፍና" ይላሉ። አንድ ሰው ወጣ ያለ ሀሳብ ካለው ደግሞ ኸረ እሱ ኮ ፈላስፋ ነው ይባላል ኣ😁።)
    እንዲሁም ደግሞ ስለ እነዚህ ነገሮች በተቻለ መጠን ምክንያታዊ ሀሳብን ተንተርሶ የሚሰጠት ምልከታ አለ። ስለዚህ
    😎 ሁለት ነገሮች አሉ ማለት ነው።
    1ኛ) Having philosophy ( informal sense of philosophy ) - በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ ጥያቄ የሚያስነሱ ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ ያልተገኘላቸውን ጉዳዮች ወይም ነገሮች ላይ የ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ የግል አመለካከት ወይም እይታ Having philosophy ይባላል። "ሀይማኖት የግል ነው ሀገር የጋራ ነው ይባላል😁"
    📚 Having Philosophy ማለት ለነገሮች ያለንን የግል አመለካት ወይንም ፍልስፍና እኔ የማስበው ፣ የኔ እይታ ፣ እኔ የሚመስለኝ ብለን የምንገልፃቸውን ያመለክትልናል ።
    2ኛ) Doing philosophy - በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ ጥያቄ የሚያስነሱ ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ ያልተገኘላቸውን ጉዳዮች ላይ በተቻለ መጠን ምክንያታዊ ሀሳብን ተንተርሶ የሚገኝ ምልከታ doing philosophy ይባላል ።
    📚 ባለን ፍልስፍና ነገሮችን Critical Thinking በሆነ መንገድ Analyze Evaluate Judge እና Understand ማድረግ ስንችል ነው Doing philosophy የሚባለው።
    ✌️Having Philosophy ማለት ማንኛውም ግለሰብ ስለ ነገሮች ያለው የራሱ አመለካከት ና አቋም ነው።
    ✌️ Doing Philosophy ግን ሳይንሳዊ ፍልስፍና ማለት ነው። ሳይንሳዊ ሒደትን ተከትሎ ነገሮችን የማጥናት ሒደት ነው።
    Therefore ,
    critical thinking,critical,basic features of philosophy,nature of philosophy,reflecting,entwrprenarship,freshman course,critizm,fresh course,logic,having,english,philosophy,maths,university

ความคิดเห็น • 43

  • @birukfasil6710
    @birukfasil6710 4 หลายเดือนก่อน +3

    በሚያስፈልገኝ ሰአት ነው ያገኘሁ በእውነት እግዚአብሔር እውቀትህን ይባርከው

  • @user-oo3xe3yv3m
    @user-oo3xe3yv3m 3 หลายเดือนก่อน +3

    ዘመንህ ሙሉ የተባረከ ይሁን

  • @abrelo_27
    @abrelo_27 5 หลายเดือนก่อน

    ❤ let's go bro with you excellent 👌

  • @Belaya1028
    @Belaya1028 4 หลายเดือนก่อน

    Thank you very Much our teacher

  • @Belaya1028
    @Belaya1028 4 หลายเดือนก่อน

    thank you very much keep it up your teaching style

  • @SamuelGgiorgis
    @SamuelGgiorgis หลายเดือนก่อน

    Egziyaber yebarkh❤

  • @user-kt2kw9cf5l
    @user-kt2kw9cf5l 2 หลายเดือนก่อน

    በጣም ብሩህ አገላለጽ ።

  • @user-jg1sm3ii7z
    @user-jg1sm3ii7z 5 หลายเดือนก่อน +2

    nice

  • @YibeltalAyenew-eh2bs
    @YibeltalAyenew-eh2bs 3 หลายเดือนก่อน

    ይመችህወንድሜ

  • @MElakuTarekekegn
    @MElakuTarekekegn 2 หลายเดือนก่อน

    በጣም እናመሠግናለን ።chapter 2 መጨረሻውን ስራ ልን

  • @mezigebudesalegnbinalifew
    @mezigebudesalegnbinalifew 2 หลายเดือนก่อน +1

    betam tru new history unit 7 fresh

  • @Delelegn-sf8ig
    @Delelegn-sf8ig 3 หลายเดือนก่อน

    GOD bless you

  • @user-gu5sl2bl4j
    @user-gu5sl2bl4j 4 หลายเดือนก่อน +1

    let's go bro with you excellent 👌

    • @AplusEthiopia
      @AplusEthiopia  4 หลายเดือนก่อน +1

      Many many thanks

  • @AbebawAbineh
    @AbebawAbineh 3 หลายเดือนก่อน

    Sweet

  • @user-pk6kx1vy8b
    @user-pk6kx1vy8b 5 หลายเดือนก่อน +1

    Tanks teacher please continue 🙏

    • @AplusEthiopia
      @AplusEthiopia  5 หลายเดือนก่อน

      eshi gunfan ይዞኝ ነው🙏
      በቅርቡ

  • @TadesseGetaneh-vq9rl
    @TadesseGetaneh-vq9rl 2 หลายเดือนก่อน

    Thanks

  • @user-iv5wm1ox7g
    @user-iv5wm1ox7g 5 หลายเดือนก่อน +3

    PLS PART TWO

  • @FikreKumlechaw
    @FikreKumlechaw 3 หลายเดือนก่อน

    Thanks for much you, and continue ! please ,can you prepare chapter 5 tutorial?

  • @birukfasil6710
    @birukfasil6710 4 หลายเดือนก่อน

    betam arif nw berta tolo tolo yeteleyayu ye fetena tyakewochn sra

  • @birhanufentaye
    @birhanufentaye 3 หลายเดือนก่อน

    thanks

  • @freedomday1126
    @freedomday1126 27 วันที่ผ่านมา

    ስታስምር በጣም አሪፍነው። በረተ።ግን እያስተማርክን ዋና ዋና ነጥቦች ስታከባቸው አንዳንዴ ለያዕቆብ አይታየንም።

  • @MasireshaBinalifew
    @MasireshaBinalifew 2 หลายเดือนก่อน

    Temechitonal Enamesegnalen

  • @user-sh8vz7bk9e
    @user-sh8vz7bk9e หลายเดือนก่อน

    govez bertaa

  • @MillionTesfaye-dc1nj
    @MillionTesfaye-dc1nj 13 วันที่ผ่านมา

    ❤❤

  • @user-op4ys4pj3x
    @user-op4ys4pj3x 4 หลายเดือนก่อน +1

    Chapter 2 pls

  • @Abiyottube
    @Abiyottube 5 หลายเดือนก่อน +1

    fallacy yiseralin pls

  • @Nisirtube3719
    @Nisirtube3719 4 หลายเดือนก่อน

    telegram channel pls

  • @user-it1wy8eo3v
    @user-it1wy8eo3v 3 หลายเดือนก่อน +3

    አንተ ትለያለህ እናመሠግናለን ሳይኮሎጅ ስራልን

  • @SoloSolo-un2hl
    @SoloSolo-un2hl 2 หลายเดือนก่อน

    Critical thinking chapter 3

  • @MuftehudinAbdu-eb2kf
    @MuftehudinAbdu-eb2kf 4 หลายเดือนก่อน

    Telegram link

  • @user-jf6qo1wb9m
    @user-jf6qo1wb9m 4 หลายเดือนก่อน

    Er part 2 yetal

  • @TadesseGetaneh-vq9rl
    @TadesseGetaneh-vq9rl 2 หลายเดือนก่อน

    Chapter 3 alederesegnm

  • @user-jj5sg6fi8q
    @user-jj5sg6fi8q 4 หลายเดือนก่อน

    Chapter 2 ebakachew sirulen

  • @NbsGtub
    @NbsGtub หลายเดือนก่อน

    አተ በትምህርት መሃል ፈታ የምታደርገው ነገርስ!!! እኔ የሶሻል ሚድያ ፍቅር ነው ያለብኝ ምን ይሻለኛል እዲሁም ቲንሽ ነገር ሲጎልብኝ አለም ጨለማ ይሆንብኛል ተስፋ ቢስ እሆናለው ለዛም ነው ሶሻል ሚድያን እንደ መደበቂያ የምጠቀመው!!! እስኪ ምከሩኝ ምን ይሻለኛል???!!!

  • @birhanufentaye
    @birhanufentaye 3 หลายเดือนก่อน

    bertu

  • @nigussolomon6871
    @nigussolomon6871 4 หลายเดือนก่อน

    ketlbet

  • @user-dr5rl8ox3v
    @user-dr5rl8ox3v 9 วันที่ผ่านมา

    ppt likekln

  • @AplusEthiopia
    @AplusEthiopia  5 หลายเดือนก่อน +3

    👉 Doing philosophy > Having philosophy .
    👉 Having & Doing philosophy cannot treated independently.
    👉 having a philosophy is not sufficient for doing philosophy.
    👆ፈተና ላይ ስለሚወጡ ያዟቸው።
    🌹2) Philosophy is a group of perennial problems that
    interest people and for which philosophers always have sought answers.
    Philosophy የሰው ልጅ ለሚያነሳቸው መሰረታዊ የ ፍልስፍና ጥያቄዎች ለሚባሉት ለምሳሌ
    👉 እውነት ምንድነው ?
    👉 እውቀት ምንድነው ?
    👉 ውበት ምንድነው ?
    👉 ከሞት በሗላ እውን ህይወት አለ(life after death ) ?
    ለሚሉት እና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስን የሚፈልግ ተደርጎ የሚገለጽ ነው ።
    📚Philosophers እነዚህን ለመሰሉ የሰው መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በሚያደርጉት ጥረት ብዙ Theories እና System of thoughts ለምሳሌ Extensionalism , idealism , Realism መወለድ ምክንያት ሆነዋል።
    🌹3) Philosophy is the logical analysis of language and the clarification of the meaning of
    words and concepts.
    ሌላኛው በ እየለት ህይወታችን እንዲሁም በተለያዩ ሳይንሳዊ ስራዎች ውስጥ የምንጠቀማቸው ቃላት ወይንም Terms ምን አይነች ፍቺ ይሰጣሉ የሚለውን እንዲሁም የትርጉም ግርታ እንዳይፈጥሩ ማድረግን ሌላኛው ተግባሩ ነው ።
    Some philosophers see this as the main task of philosophy, and a few claim this is the only legitimate function of philosophy .
    📚 በስፋት chapter 3 ላይ እንመለከተዋለን።
    🌹4) Philosophy is a rational attempt to look at the world as a whole.
    እንበልና አንድን ፖለቲከኛ ፣ ቢዝነስ ማን ወይንም ስፖርተኛ ስለአለም እይታ ብጠይቋቸው ከፖለቲካው ከንግዱና ከስፖርቱ አለም አንፃር ብቻ ያላቸውን እይታ( Fragmented view ) ሊነግሯቹ ይችላሉ ይህን እይታ የተሟላ ማለት አንችልም Philosophy ወንም philosopher ግን በተቃራኒው የሁሉን እይታ በአንድ በማዋሀድ (whole ) ስለ አለም የተሟላ እይታን የሚፈጥርልን ሳይንስ ነው ።
    Philosophy seeks to combine the conclusions of the various sciences and human experience into some kind of consistent worldview.
    🌹5) Philosophy is a process of reflecting on and criticizing our most deeply held conceptions
    and beliefs.
    📚 ፍልስፍና ማለት ስለ አንድ ነገር ምሳሌ ስለ ተፈጥሮ፡ ስለ ማህበራዊ ትስስር ፡ ስለ ዩኒቨርስ ፡ ስለ ውበት ወዘተ የሰው ልጅ ያለውን ጥልቅ የሆነ አመለካከት እና እምነት የሚገልፅበት ፡ የሚያንፀባርቅበት ፡ የሚገመግምበት ፡ የሚተችበት ሒደት ፍልስፍና ይባላል።
    📚 ታዲያ የሰው ልጅ ስለ እነዚህ ነገሮች ያለውን አመለካከት ሲገልፅ ሲያንፀባርቅ ሲገመግም ና ሲተች ምክንያታዊ ሀሳብን መሰረት በማድረግ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመከተል ነው። ስለዚህ 5ተኛ ላይ ያለው የ philosophy definition formal sense of doing philosophy ይባላል።
    ለዛሬ እዚ ላይ ይበቃናል በጥልቅ ለመረዳት Module እንድታነቡ ይመከራል ።
    በቀጣይ Core Fields of philosophy እናያለን።
    📌 መልካም ቀን ።
    🥰A+ Ethiopia .

  • @user-sf7ho9pw3t
    @user-sf7ho9pw3t 4 หลายเดือนก่อน +1

    Endet new telegram chnalal menageghew m.r

    • @AplusEthiopia
      @AplusEthiopia  4 หลายเดือนก่อน +1

      @Aplus_info

    • @DeguBarida
      @DeguBarida 27 วันที่ผ่านมา +1

      Concie interdiction to logic yemelo metafuni felige atawu please atache taregegnale