6ኛ ትምህርት : የዮሐንስ ወንጌል ዋና ዋና ሐሳቦች - ስለ ኢየሱስ የተሰጡ ተጨማሪ ምስክርነቶች

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 6 ก.พ. 2025
  • ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚተከሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዮሐ. 3፡25-36፣ ዮሐ. 1፡32-36፣ ዳን. 7፡18፣ ዮሐ. 6፡51-71፣ ዮሐ. 5፡36-38፣ ዮሐ. 7፡37-53።
    የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ” (ዮሐ. 12፡32)።
    ኢየሱስ ስለ ራሱ፣ ስለ ማንነቱ፣ ማን እንደላከው፣ ወይም ከየት እንደመጣ ብቻ አስገራሚ ነገሮችን አልተናገረም። ባደረጋቸው ተአምራትና ምልክቶችም ማንነቱን አሳይቷል። አንዳንዶች ስለ ኢየሱስ በግልጽ እንደሚመሰክሩት፡- “ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ይህ ካደረጋቸው ምልክቶች ይልቅ ያደርጋልን? አሉ” (ዮሐ. 7፡ 31)።
    እርሱ የቃሉን እውነት በሚያረጋግጡ ተግባራት ቃላቱን ደግፏል። ድራማው ሲቀጥል ግን በህዝቡ መካከል መለያየት ይጀምራል። በቤተሳይዳ መጠመቂያ አጠገብ ያለው ሰው ፈውስ የአንዳንድ መሪዎችን ቁጣ ቀስቅሷል። 5,000 ሰዎችን መመገቡን ተከትሎ በቅፍርናሆም የተደረገው ውይይት ኢየሱስን ብዙ ሰዎች እንዳይቀበሉ አድርጓል። የአልዓዛር ትንሣኤ በአንዳንዶች ላይ እምነት ቢፈጥርም በሌሎች ላይ ግን የኢየሱስን ፍርድ እና ሞት የሚያስከትል ጠላትነት እንዲፈጠር አድርጓል።
    የዚህ ሳምንት ትምህርት ስለ ኢየሱስ ከተሰጡ ምስክርነቶች የተወሰኑትን ይመለከታል። በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ክንውኖች ውስጥ፣ የኢየሱስ እውነተኛ ማንነት አንዳንድ ገጽታዎች የተገለጡ ሲሆን፣ በአንድ ላይ ሆነው ስለ መሲሑ ኢየሱስ ጥልቅ ራእይ ፈጥረዋል።

ความคิดเห็น • 1