ጸሎተ ሃይማኖት - በመጸሐፍ ቅዱስ ክፍላት ውስጥ
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 17 ธ.ค. 2024
- ጸሎተ ሃይማኖትን ከነትርጉሙ ጠንቅቆ ማወቅ ሃይማኖትን በተገቢው መንገድ መረዳት መቻል ማለት ነው። ስለዚህም እያንዳንዳችን ስለ ሃይማኖታችን ብንጠየቅ የጸሎተ ሃይማኖትን ትርጉም ጠንቅቀን ካወቅን ማንነታችንን በሚገባ መግለጽ እንችላለን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ እንደ አባታችን ሆይ እና እንደ እመቤታችን ጸሎት በቃሉ ጸሎተ ሃይማኖትን ማወቅ ይኖርበታል።
ከዚህ በተጨማሪም የጸሎቱ ክፍል በመጸሐፍ ቅዱስ የተረጋገጠ ለመሆኑ በዚህ ቪዲዮ ላይ የተዘረዘሩትን ጥቅሶች እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል!!
፩- ሁሉን በያዘ ሰማይንና ም ድ ር ን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በ አ ን ድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።
፪-ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን።
፫-ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል።
፬-ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም፤በሰማይም ያለ በምድርም ያለ።
፭-ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ። በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ።
፮- ሰው ሆኖ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ፤ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ።
፯- በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ።ዳግመኛም ሕያዋንንና ሙታንንም ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል። ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
፰- ጌታ ማኅየዊ በሚሆን ከአብ በሰረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን፤ እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነቢያት የተናገረ።
፱- ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን።
፲- ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።
፲፩- የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን።
፲፪- የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን። - บันเทิง