Ethiopia

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 18 พ.ย. 2024

ความคิดเห็น • 23

  • @solomonhailu8131
    @solomonhailu8131 2 ปีที่แล้ว +1

    Konjo tireka tanks

  • @merongedlu8929
    @merongedlu8929 2 ปีที่แล้ว +3

    ሰላም
    ብዙ አይነት ስሜት እየተሰማኝ ነው ።ስብሀት እና በአሉን የመሳሰሉትን እንቁ ደራሲያን የስሜት ስቃይያቸውን እየተጋራሁ፣ የልጅነቴን ድባብ እያስታወስኩ ፣በተራኪያኑ ቅንብር እና ብቃት እየተደመምኩ፣በጀርባ ሙዚቃዎቹ እየተዝናናሁ እና ሌላም ብዙ ብዙ አይነት ስሜት እየተሰማኝ።በወጣትነት ዘመኔ ያነበብኩት መፅሀፍ ቢሆንም ግን እንደአዲስ ቀልቤን ሰጥቼ እያደመጥኩ ነው።
    አንተነህ ባጋጣሚ ለኔ በአንደኛ ደረጃ ከማስቀምጣቸው ተዋንያን መሀል ነህ በዚ መልኩ ሳገኝህ ደሞ በጣም ደስ አለኝ።የልዮ ሰርሳሪ ድምፅ ባለቤት ነህ።
    ስማቸውን አሁን በደንብ አልያዝኩትም እንጂ የሁለቱ ሴቶች ድምፅ እና ብቃት ከየት ነው የመጡት አስብሎኛል።
    ሰብለን የምትርከዋ እህቴ መረቅን ስትተርክ አድምጬ ልቤ ውስጥ ቀርታለች።
    ሁላችሁም ጎበዞች ናችሁ በርቱ እናመሰግናለን
    በበኩሌ ሰብስክራይብ አድርጌያለሁ።

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  2 ปีที่แล้ว

      መልካም አድማጭ ባገኘን ቁጥር ጉልበታችን ይጨምራል ።ክብረት ይስጥልን

  • @ambaw1004
    @ambaw1004 2 ปีที่แล้ว +3

    እንባ እንባ ይለኛል ፣
    ይተናነቀኛል •••••
    እንባ የትአባቱ ፣
    ደርቋል ከረጢቱ፤
    ሳቅ ሣቅም ይለኛል
    ሥቆ ላይስቅ ጥርሴ፤
    ስቃ እየነደደች
    መከረኛ ነፍሤ ፤
    ✍🏿 በዓሉ ግርማ
    የመጨረሻዎቹ ቃሎች በመጽሐፉ የከተባቸው ፤ ድንቅ የኪነት ሠዉ ፤ አቤት ገጸ ባህሪን መዉለድ መፍጠር ሢችልበት

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  2 ปีที่แล้ว +1

      አምብሼ ቅነትህ ሁሌም ከእኔ ጋር ነው ለዚህ ስራ የማእዘን ራሱ ነህ።ክበርልኝ

    • @ambaw1004
      @ambaw1004 2 ปีที่แล้ว

      @@ethioemmatube አመሰግናለሁ ወዳጄ ልቤ፤ እናንተ ሥለተረካችሁት የበዓሉ ግርማ ነፍሥ ተደስታለች እኔንም ጨምሮ

  • @fasikafiseha7958
    @fasikafiseha7958 2 หลายเดือนก่อน

    እየገሰገስኩ ነው

  • @meazabeza2806
    @meazabeza2806 2 ปีที่แล้ว +1

    ደስ የሚል አተራረክ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ 🙏

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  2 ปีที่แล้ว

      ክብረት ይስጥልን

  • @thegestthegest6080
    @thegestthegest6080 2 ปีที่แล้ว

    Waw Tnx

  • @khalidosman3894
    @khalidosman3894 2 ปีที่แล้ว

    Part 6🙏

  • @thegestthegest6080
    @thegestthegest6080 2 ปีที่แล้ว

    Part 6 please

  • @etshuncho2673
    @etshuncho2673 ปีที่แล้ว

    bea ethiopia tarik endazih ayneat atrarke aychea alawkem betam ymgemi new endazih onachiew lelochem mtsehaft trkulen

  • @chagnimediaoffical
    @chagnimediaoffical 2 ปีที่แล้ว +3

    ደራሲው ክፍል 5 እጅግ ከፍ ብሎ ተሰርቶና ተቀምሞ ደርሷል፡፡
    እነ አንትሽ ዛሬ ደግሞ ገራሚ ሁናችሁ እና ተክተክ ብላችሁ መጣችኋል፡፡
    “ወይ አራዳ…አራዳ….!” የድሮ የኢትቪ ቆየት ያሉ አርካይቭማ አላችሁ ሆ…..
    አቤት የድምጽ ግብዓት ብዛት፣ጥራት እና ተገቢ ስፍራ ሲሆን ይጥማል!
    እንደተከታታይ ድራሚ(ፊልም) እኮመኩም ጀምሬአለሁ!
    አስተያት ለመስጠት አይደለም የምመጣው የምሬን ደስ ብሎኝ ሰምቼ እና ተደንቄ እከታተላለሁ!
    እረ ተራኪያን ተሰብሰቡና እንደ ደራሲው ያለ ድንቅ ስራ እንስራ…ወይኔ ትወና እና በወኔ መስራት…..የእናት ሃገር ወይ ሞት…..የጦርነቱ ድባብ ገራሚ ነው…..
    “ይህ ስራ የጋሽ ስብሃትን ህይወት ነው የጻፈው የሚል በርካታ ቅብብሎሽ ቢኖርም ግን ሲራክ ግን የስብሃትና የበዓሉ ድብልቅ ነው…በአመዛኙ እንደውም በዓሉ ነው ባይ ነኝ!....

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  2 ปีที่แล้ว +2

      ወዳጄ ሰውዬው በአሉ ነዋ።እኛ ከተረክንበት ሽራፊ ጥበብ ይልቅ የእሱ ብአር ትገርማለች ፣ከቆሻሻ መሀል ውበት የምታይበት መለኮታዊ ብሌን አላት።ክህሎቱ ኖሮን ከዚህም በላይ በኳልነው

    • @ambaw1004
      @ambaw1004 2 ปีที่แล้ว

      አማኑዬ ፤ መውደድ አሞራ ነዉ ያርፋል የትም ቦታ እንዲሉ፤ ይህ ደራሲው የተሰኘውን የበዓሉ ግርማ ሥራ እና የነ አንትሽ ወኔ የተመላበት ትወና ወ ትረካ አስደምሞኛል ( ወድጄዋለሁ ) ፤ አማኑዬ ልክ ብለሀል እኔም መጽሐፉን በማደምጥበት ግዜ ሢራክ ( ጋሽ ስብሀት ገ / እግዚአብሔር ) ን ሣይሆን ፤ እንደዉም የበዓሉ ግርማ አሥተሳሰብ እና ዕይታ ሚዛኑ ይደፋብኛል፤ ጋሽ ስብሐት እኮ ሲከትብ እንጂ ሲያወራ አንድ አረፍተ ነገርን ለመግልጽ ሲያሽሞነሙን ሰዓታት ያልፋሉ፤ እና እኔ ከ 10 % ውስጥ 4% ለ ጋሽ ስብሀት ብሰጥ 6% የሲራክ ዕሳቤ እና ምልከታ የራሱ የከያኒዉ የበዓሉ ግርማ ይመስለኛል

  • @keludishow
    @keludishow 2 ปีที่แล้ว +2

    የማይዋጥልኝ ሀቅ!!ነበር ከታሪክነት በዘለለ ለዛሬና ለነገ ቅንጣት ለውጥ አያመጣም የሚባል ብሂልን የሚከተል ሠው የመሠጠኝ ፅሁፍ………………
    ከበእውቀቱ ስዩም ድሮና ዘንድሮ
    ጋዜጠኛ፦ቁርስህን ምን በላህ?
    ወጋየሁ ንጋቱ፦ዱለት
    ጋዜጠኛ፦የልብስ ምርጫህ?
    ወጋየሁ፦ቢትልስ ሹራብ
    ጋዜጠኛ፦በትርፍ ጊዜህ ምን ያዝናናሃል?
    ወጋየሁ፦ካርታ ጨዋታ
    … ተፈፀመ…
    ዘንድሮ
    ጋዜጠኛ፦ቁርስህን ምን በላህ?
    አርቲስት፦ ያው እንግዲህ ሠው ሆነን ስንፈጠር ሰውነታችን እንደ ሰውነት ምግብ መጠየቁ አይቀርም አርቲስት ደግሞ እንደ ማንኛውም ሠው ምግብ ያስፈልገዋል ምን ልልህ ፈልጌ ነውለኔ ቁም ነገሩ ለምግብ መኖር ሳይሆንለህዝብ መኖር ነው ህዝቡ የሚጠብቅብህን ነገር ካበረከትክ ቀኑን ሙሉ ባትበላ እንኳን የረሃብ ስሜት አይሠማህም ወደ ጥያቄህ ስመጣ ቁርሴን የበላሁትበቅርቡ የሚዳሰስና የሚቀመስ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበውን ጨጨብሳ ነው።
    ጋዜጠኛ፦የልብስ ምርጫህ?
    አርቲስት፦እንግዲህ ሁላችንም ወደዚህ ምድር ራቁታችንን ነው የመጣነው ራቁታችንን ሆነን ይህችን ምድር እንለቃለን……እያለ ይቀጥላል🤔
    📌 ዘመን ያዘምናል ለሚሉ ትልቅ ማሳያ በድሮ በሬ ማን አረሠ ዝማኔ፣በአሁንና ፣በነገ ውስጥ ብቻ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ ለደረሡት ትልቅ ምስክር ትናንት ለዛሬ ምሶሶ መሆኑን ቁልጭ አርጎ ያሳየን ዛሬም ላይ ሆነን ሳንፈጠር የነበረውን መስታወት ሆኖ ያስቃኘን ድባብ ብዙ በመደመም ውስጥ ትርጉም ያለው እውቀት እንዲኖረን የሆንበት ወርቃማ ጥበብ በዓሉ ግርማ እና የሞያ አጋሮቹ በድሮ ውስጥ ትልቅ ዝማኔን ተሰጥኦን የተጎናፀፉ እውነት ቃል የለኝም።
    አንተነህ ወንድሜ ሁሌም ሀሳቤን ለማስፈር ስገባ ካላመሠገንኩህ ጥበብ ትወቅሠኛለች።ክፍል አራትን በሠብለና በሲራክ ምልሠትና ኩነት በክፍል አምስት ድባቧን በምወዳት የነሲራክ ሠፈር የሼኩና የሲራክ የፅግሽ ጥቁር ዶሮ😂የጦርሜዳው ድባብ ኸረ ስንቱ የጉድ ነው መሳጭ እናም ለኔ ድሮ ነበር ብቻ አይደለም ነገም ነው።

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  2 ปีที่แล้ว +1

      ጥኡም ኮመንት ነው የበእውቀቱ የምር ነው ያሳቀኝ በድጋሚ ክብረት ይስጥልን ።እንዲህ የነጠረ አድማጭ ማግኘት እንዴት ነብስ ያለመልማል መሰለሽ በድጋሚ እጅ እንነሳለን

    • @ambaw1004
      @ambaw1004 2 ปีที่แล้ว

      ከሉዲአችን የኛ የሁላችን ፤ ንግግርሽ መጽሐፍ ነው አይጠገብም፤ ጥሩ ወግ አቅምሰሽናል ፤ በነገራችን ላይ ታውቂ ይሆን አላውቅም ? ደራሲዉ የተሰኘዉ መጽሐፍ ሥለ ጋሽ ስብሐት ገ/ እግዚአብሔር ( ደራሲ ) እንዲያጠነጥን አድርጎ በዓሉ ግርማ የከተበዉ ነበር፤ ቢሆንም በዉስጡ ያለው ሀሳብ ግን የስብአት ስብዕና በከፊል የበዓሉንም አሳይቶኛል ፤

    • @keludishow
      @keludishow 2 ปีที่แล้ว +1

      @@ambaw1004 አዎ አምብዬ ፍንጭአለኝ እንዳልከውም ስስለው የጋሽ ስብሀት ስብእና ይታያል የገረመኝ የሲራክ የጥበብ ዛር ቁንጥንጥነት ከጋሽ ስብሀት ስብእና ጋር ይጣመራል ሌላው ደግሞ አዛኝና ሩህሩህ ልብ ያለው ቸር መሆኑ ነው ከዛ ውጪ ግን ብዙ የበአሉን እምቅ አመለካከት የያዘ ይመስለኛል

    • @ambaw1004
      @ambaw1004 2 ปีที่แล้ว +1

      @@keludishow ልክክ ያለዉን ልክ ብለሻል ከሉዲአችን ፤ መዉደድ አሞራ ነው ያርፋል የትም ቦታ እንዲሉ ይህንን መጽሐፍ አለመውደድ አይቻልም ፤ ድንቅ ነው ሥለዕውነት፤