ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ነገ ፓርላማ ሊቀርቡ ነው

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 18 ส.ค. 2024
  • ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ነገ ሐሙስ ሰኔ 27፤ 2016 በሚካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ከፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሊሰጡ ነው። ጥያቄዎቹ የፌዴራል መንግስት የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ላይ ያተኮሩ ናቸው ተብሏል።
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ፤ በዓመት ሁለት ጊዜ ለፓርላማ ሪፖርት ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው በ2008 ዓ.ም የወጣው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር እና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ ይደነግጋል። ምክር ቤቱ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ፤ በነገው ስብሰባ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎች የመንግስታቸውን የዘንድሮ በጀት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የተመለከቱ እንደሚሆኑ ገልጿል።
    “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ሁለት የፓርላማ አባላት፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተነገራቸው የፌደራል መንግስት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ሳይሰጣቸው መሆኑን አስታውቀዋል። ጥያቄዎቻቸውን አስገብተው እንዲያጠናቅቁ ቀነ ገደብ የተሰጣቸው እስከ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ መሆኑን የገለጹት የፓርላማ አባላቱ፤ ሆኖም ሪፖርቱ የተላከላቸው በበነጋታው መሆኑን አስረድተዋል።(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น • 1

  • @hvgygg1483
    @hvgygg1483 หลายเดือนก่อน

    Hirko