ሌላው ቀርቶብን አንተን ባገኘን Morning Devotion የማለዳ ፀሎት | በረከት ለማ |Bereket lemma

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 15 ต.ค. 2024
  • በጣም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የእግዚአብሔር ክብር እጅጉን በሚያስፈራና በሚያስታውቅ መልኩ በሀገራችን ቤተ - ክርስቲያንና ህዝብ ላይ ተንሰራፍቶ እንደነበር ህያዋን ምስክሮች አሁንም አሉ። ይሄ ክብር ዳግም ተመልሶልን በመንፈሱ ተሞልተን የቃሉና የፀሎት ረሃብ ገብቶብን እንደገና ታድሰን ለሀገር መፍትኼ የምንሆንበትን ቀን እጅጉን እናፍቃለሁ።
    ያለ መንፈስ ቅዱስ በመሟሟቅ ያደረግናቸው ስብሰባዎች ፣ አምልኮዎች ፣ ኮንፍራንሶች ሁሉ ነፍሳችንን አዝለዋታል ፤ ምናልባት እንደው መንፈስ ቅዱስን በሌላ ነገሮች ተክተነው እንደሆን እግዚአብሔር ራርቶልን እንደገና ከዚህ የድግግሞሽ ህይወት እንዲያወጣን አንማፀነው።
    አስቀድማችሁ ፅድቁንና መንግስቱን ፈልጉ ተብለን እኛ ግን ከፅድቁና መንግስቱ ይልቅ የሚጨመርልንን ነገር ወደድን ፤ የወደድነው ነገር ደግሞ ከቤቱ አርቆን እያራቆተን ነው። አሁን ባለ በሌለ አቅማችን መንፈስ ቅዱስን እንፈልገው ፣ ቅድሚያ እንስጠው።
    #mezmur #newprotestantmezmur #Bereketlemma #tiktokvideo #amharicmusic

ความคิดเห็น • 204