ድንቅ የህይወት ምስክርነት…‼️ ፕ/ር ኢያሱ ኤልያስ … የካውንስሉ ፕሬዚደንት Nikodimos Show - Tigist Ejigu

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 27 ม.ค. 2025
  • የተወደዳችሁ የኒቆዲሞስ ሾው ቤተሰቦች፡ ከታች ያለውን link ላይክ በማድረግ facebook ገፃችንን እንድትቀላቀሉ በታላቅ አክብሮት እጋብዛለሁ፡፡ 👇👇
    / nikodimosshow
    ፕሮግራማችንን እየተከታተላችሁ ገንቢ አስተያየታችሁን ሁል ጊዜ ስለምትለግሱን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን፡፡ ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ አዳዲስ ቪዲዮ እንዲደርሳችሁ ሰብስክራይብ ማድረግ አትርሱ፡፡
    This Video Clip is Dedicated Only to Nikodimos Show Channel /Tigist Ejigu/!
    Subscribe today for latest Videos Here:- / nikodimosshow
    Facebook:- / nikodimosshow
    Instagram:- / tigisttg
    Awtaru Kebede,Ethiopia,Ethiopian Gospel Song,Amharic Gospel Song,Wongel,Gospel,Amharic,Mezmur,Protestant,Protestant song,Christian,Evangelical,church,Ephrem Alemu,Tekeste Getnet,Yoseph Ayalew,Kefa Mideksa,lily tilahun,Mesfin Gutu,Tesfaye Gabiso,Hana tekle,Jossy Kassa,Dagi,Dagimawi Tilahun,Samuel Tesfamicheal. Hanfre Aligaze,Tolosa Gudina,Teddy Tadesse,Yosef Bekele,Tesfaye Chala","Teddy Tadesse" "Bereket Tesfaye" frabek125 "Ephrem alemu" "Suraphel Demissie" "Presence Tv" "Holy Tv" "Cj Tv" "Aster Abebe" "feker tube" "MARDA TUBE" "Melkamu tube" "ETHIOPIAN PROPHET'S" "TST APP "yesuf app"
    "Hosannamezmur" "kiyatalkshow" "EthiopianMezmur"
    © Copyright:- #Tigist Ejigu /Nikodimos Show/ 2021

ความคิดเห็น • 656

  • @YMW7777
    @YMW7777 3 ปีที่แล้ว +116

    ይሄንን ወንድም የማውቀው ካናዳ ምድር ሊማር መጥቶ ነው፣
    የሚገርመው almost backslide አድርጌ ፣ የእሁድ ቤ/ክ ተመላላሽ በነበርኩበት ጊዜ፣
    ከዛች ትንሽ ከተማ ጨርሶ ሊወጣ የመጨረሻው ቀን፣ እንዲያገለግል ፕሮግራም ተሰጥቶት፣ ስለ ቅድስና ሰበከ፣ እግዚአብሔር በእርሱ ተናገረኝ፣
    ለመጨረሻ ጊዜ መንገዴን ለማስተካከል በእኔና በእግዚአብሔር ፊት ቃል ገባሁ፣ ውሳኔን ወሰንኩ፣
    ከዛም ድኜ ቀረሁ፣ እግዚአብሔር አምላክ፣ ይመስገን።
    እንድ ቀን አግኝቼው እነግረው ይሆናል ብዬ ሳስብ
    አንድ ቀን በቲቪ አየሁት
    እንዲህ እንዳሁኑ ወፍራም አልነበረም፣
    አሁን በጣም ተለውጧል፣

    • @hiwimimikidane1789
      @hiwimimikidane1789 3 ปีที่แล้ว +2

      ዋዉ ደስ የሚል ምስክርነት ነው ተባረኪ. ድነሽ ቅሪ

    • @almazshifaw6702
      @almazshifaw6702 3 ปีที่แล้ว

    • @almazshifaw6702
      @almazshifaw6702 3 ปีที่แล้ว

    • @emebetbrussow5398
      @emebetbrussow5398 3 ปีที่แล้ว

      ጌታ ክብሩን ይውሰድ !!
      ዘመንሽ በቤቱ ይለቅ !!

    • @shewitfekadu1924
      @shewitfekadu1924 3 ปีที่แล้ว

      ክብር ለቅዱሱ ይሁን🙏❤️
      ነብሴን በምክሩ መለሳት... እንዳልው ዳዊት

  • @solomontekle8393
    @solomontekle8393 3 ปีที่แล้ว +110

    ወጣት በደንብ ስማ ቁልፉን ነዉየተናገረዉ እናት እና አባት አክብር ዕድሜ እንዲረዝም ተባረክ ፕሮፌሰር ገና ትደምቃለህ የምድሪቱ ሀብት ያለዉ አንተዉስ እንካንም ለዚህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መጣህለት ብሩክ ነህ ቲጂ ተባርከሻል!!

  • @AfeworkG
    @AfeworkG 3 ปีที่แล้ว +103

    ሰው ተዘጋጅቶበት አስቦበት ሳይሆን ምስክርነቱ ድንገት ከውስጡ እንደዚህ እየፈነቀለ ሲወጣ በእርግጥም በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ምስክርነት ብለን አዳማጮቹ ልንመሰክር እንችላለን:: እህታችን ትግስት ተባረኪ:: እንደዚህ አይነቶችን በተከታታይ ብታቀርቢ እንዴት ጥሩ ነበር::

    • @ashemanall
      @ashemanall 3 ปีที่แล้ว +3

      ohh lord !!! watching it for third time in tears !!

    • @masreshaashagrie3005
      @masreshaashagrie3005 3 ปีที่แล้ว +1

      እውነት ነው ተባረክ🙏

    • @goanche790
      @goanche790 2 ปีที่แล้ว

      አሜን...🙏🙏🙏

  • @feaaef5243
    @feaaef5243 3 ปีที่แล้ว +82

    ፕሮፌሰር እንደ አንተ አይነቶችን ያብዛልን ነፍስም አልቀረልኝ ጌታን ስላንተ ባረኩት አንተም በብዙ ተባረክ!!!

    • @mekedestilahun5420
      @mekedestilahun5420 ปีที่แล้ว +1

      Llppppp

    • @በፀሎት-ኀ8ጘ
      @በፀሎት-ኀ8ጘ ปีที่แล้ว

      ጌታን ባረኩት ?????ለመሆኑ ሰው ጌታን ይባርካል ወይ ምንፍቅና

    • @tsegayemelis5388
      @tsegayemelis5388 3 หลายเดือนก่อน

      ​@@በፀሎት-ኀ8ጘ" ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት እግዚአብሔርን ባረከ፤ ዳዊትም አለ። አቤቱ፥ የአባታችን የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ተባረክ። "
      (መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 29:10)
      መፅሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል አንብብ/ቢ

  • @legessedjiloofficial7108
    @legessedjiloofficial7108 3 ปีที่แล้ว +58

    እውነትም ድንቅ ምስክርነት ነው። ፕ/ር ኢያሱን በቅርበት አውቀዋለሁ፣ ነገር ግን እንደዚህ አላውቀውም ነበር። ውድ ወንድሜ አሁንም እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ ይባርክህ፣ ከዚህ በላይ ለበረከት ሁንልኝ።

  • @AfeworkG
    @AfeworkG 3 ปีที่แล้ว +102

    ዋው! በጣም ልብ ይነካል:: የእንደዚህ አይነት የወንጌል አርበኞች ውጤት ናት የወደፊቷ የበለፀገች ኢትዮጵያ:: ከፓርቲዎች የተነሳ ሳይሆን ከእግዚአብሔር የተነሳ ኢትዮጵያ መበልፀጏ የማይቀር ነውና:: እሄንን ምስክርነት አወናባጆቹ የገንዘብ ሰባኪዎች ቢሰሙት ልባቸውን ሊቀይር ሃይል አለው:: እግዚአብሔር ይባርክዎት ፕሮፌሰር::

    • @tigestwoldetsadik4316
      @tigestwoldetsadik4316 3 ปีที่แล้ว

      የገባህ

    • @sebk326
      @sebk326 3 ปีที่แล้ว

      ከከከ ከከከከከከ ከከከከከከከከከከከከከከከከከከከከከከከከከአዐጰጰጰጶጰጰጰጰጶጶጵጵጶጶጶጶጵጶጶጶጶጵጶጶጶኸሸ

    • @mimitamire3649
      @mimitamire3649 3 ปีที่แล้ว +1

      ትክክል

    • @AA-jj6gj
      @AA-jj6gj 3 ปีที่แล้ว +1

      ዋው ጌታ ይባርኮት የሚገርም ምስክርነት ነው ጌታ ሁሌ ያከበሩትን ያከብራል ዘመኖት በተድላ ይለቅ ቲጂዬ ተባረኪ

    • @kalekale8217
      @kalekale8217 3 ปีที่แล้ว +1

      አሜን በእውነት ትክክል ኖት አዎ የወጌል ሸቃጮቹ ሊሠሚት ግድ ነው
      እግዚአብሔር፡ይባርኮት

  • @ashemanall
    @ashemanall 3 ปีที่แล้ว +8

    ይሄ ስብከት እንጂ ቃለመጠይቅ አይደለም !!! ohh my GOD ለሶስተኛ ጊዜ እየሰማሁ ነኝ

  • @yergalemmeles2842
    @yergalemmeles2842 2 ปีที่แล้ว +1

    ትግየ እግዝአብሄር ይባርክሽ መጻፍ አልወድም ግን ሁሉ የምታቀርቢው እከታተላለሁ እና የሚገርሙ ምስክርነት ነው የሚታቀርቢው በዚህ ቀጥይ ጌታ ጸጋው ያብዛልሽ 💕💕

  • @yidnekachewteka9679
    @yidnekachewteka9679 3 ปีที่แล้ว +2

    በእምባ የጨረስኩት ቃለ መጠይቅ ለጌታ ውለታ ክብር የሚመልስ ምዑር! ፕ/ር እያሱ የምዑርነት ትምክት ወይም ልቅነት(Intellectual pride or arrogance) ከአንደበትህ አልሰማሁም ያከበርከዉ ጌታ ከዚ በላይ ያክብርህ። ቲጂ ጌታ ይባርክሽ!

  • @rakeb6029
    @rakeb6029 3 ปีที่แล้ว +35

    በእውነት እግዚአብሔር ታማኝ ነው የሚያከብሩትን ያከብራል በጣም ተፅናናሁበት ጌታችን ታማኝ ነው ክብር ሀሉ ለስሙ ይሁን።ቲጂ እግዚአብሔር ይባርክሽ እንደዚህ አይነት ለ life lessonየሚስጡ ስወችን ስለምትጋብዥልን

    • @tenagnesharew2185
      @tenagnesharew2185 3 ปีที่แล้ว

      እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ያብዛልህ ዛሬ ኢትዮጵያ የምትራበው ይህንን ነው ቴጄ ግሩም የሆኑ ዝግጅችሽን አድናቄ ነኝ ተባረኬ

  • @godislove4988
    @godislove4988 ปีที่แล้ว +1

    ጌታ ይባርክህ ያበተ ቡሩክ ዘመንህ ይባረክ ቲጅየ ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ 💜🙏💜

  • @kokialemayehu5676
    @kokialemayehu5676 3 ปีที่แล้ว +50

    ምን አይነት ቅንነት ነው እውነትም ቅኖች እግዚአብሔርን ያዩታል

  • @hiwettulu9602
    @hiwettulu9602 3 ปีที่แล้ว +22

    በጣም አመሰግናለሁ ተጠቅሜያለሁ ዘመንህ ሁሉ የተባረከ ይሁን
    ቲጂዬ ከሰዎች ሀሳባቸውን
    በግልጥ እንዲያወሩ
    የምትሰጪያቸው ሰፊ ፋታ
    የምታደምጪበት ትዕግስት
    የእንግዳ አክብሮት
    በጣም ተባረኪ ደስ ይላል

  • @danielmamo2437
    @danielmamo2437 3 ปีที่แล้ว +18

    ዋው እያለቀስኩ ስማው መንፈስ ይነካል ትክክለኛ ህይወት እንዲ ይነካል

  • @mekedesmezmur4057
    @mekedesmezmur4057 3 ปีที่แล้ว +5

    ከድንቅም ድንቅ የሆነ ከውስጥ የሚገባ የሕይወት ምስክርነት በቃላት ለመግለጽ የማይቻል ክርስትና በሥራ በትምህርት በአግልግሎት በፖለቲካ በማንኛውም አቅጣጫ ህይወት እንዳለው የሚያሳይ ውይይት ፕሮፌሰር ኢያሱ ጌታ አብዝቶ ይባርኮት ለወጣቱ ትውልድ ምሳሌ የሆኑ እናት አባትን ማክበር ለእግዚአብሔርም ቃል ቆሞ መጽናት ህይወትን እንድ ሚያቃና ከአላማ እደሚያደርስ ግሩም ምስክርነት የሀገርና የህዝብ እረኛ ብሎት ያንሳል እንጂ አይበዛም ትዕግስት ጌታ ይባርክሽ እንደዚህ አይነት ትምህርታዊና ጠቃሚ ዝግጅት በማቅርብሽ መልካም አዲስ አመት ለሁላችንም🙏🙏💜

  • @belachewseyoum3677
    @belachewseyoum3677 3 ปีที่แล้ว +14

    ይገርማል - እግዝአብሔር እንዴት አሳምሮ ሰራው !!! ኧረ ያብዛልህ ፣ጌታ ዘለግ ያለ እድሜ ይስጥህ...ወንድማለም 🌹🌹🌹 እንኳን በጌታ ወንድሜ ሆንክልኝ፣ እግዚአብሔር ከበረ🙏

  • @zimitaaychluhum5433
    @zimitaaychluhum5433 3 ปีที่แล้ว +21

    በእውነት ጌታ ይባርክህ ፕሮፌሰር:: ጌታን ስላንተ አመሰግናለሁ:: አቤት ጌታ ሆይ አደራህን እለምንሀለሁ በስምህ ስልጣን ይህንን ሰው በደምህ ሸፍነህ ለበረከት አድርገው::

  • @teferibezabhi7894
    @teferibezabhi7894 3 ปีที่แล้ว +2

    ዶክተር አንተን የሰጠን ጌታ ስሙ ይባረክ የማውቅህ የምወድህ ውድ ቅን የተሰጠ መሪዬ ስለሆንክ ጌታህን በየትም ለማሳየት ያለህ በቁርጠኝነት ሁሌ ይገርመኛል አሁንም እስከመጨረሻው ጌታ ይርዳህ

  • @marthayohannes1590
    @marthayohannes1590 3 ปีที่แล้ว +19

    እግዚአብሔር ይባረክ ስለሁላችሁም ውንድሜ እንዳንተ ያሉትን ጌታ ያብዛልን በጣም ደስ ያለኝ ባላውቃትም ለባለቤትህ ብዙዬ ብርክክክክክ በይልን ለኢትዮጵያ እናቶች እህቶች በሙሉ ረጅም እድሜና ጤና

  • @saraabite90
    @saraabite90 3 ปีที่แล้ว +31

    wonderful message ! The fruit of respecting elders ... Well educated, passionate, God's servant ! wow! Thank you both of You !

  • @nuhuhuh-z4j
    @nuhuhuh-z4j 3 ปีที่แล้ว +21

    Wow wow wow, what an amazing leader. I thank the Almighty God for your leadership and dedication and testimony. It’s up lifting. I don’t have enough words what to say; I simply rejoicing for hearing such roll model for many .

  • @Yabuwelde
    @Yabuwelde 3 ปีที่แล้ว +10

    My Prof. you are so special and humble, ... the fatherly love you gave us is absolutely different, I always told you. God bless you .

  • @tadessehatiyaoge4360
    @tadessehatiyaoge4360 9 หลายเดือนก่อน

    ይሄንን ምስክርነት ደግሜ ሰማሁት በጣም ደስ የሚልና አስተማሪ ነው::እናትና አባትን ለረሱ እነሆ መልእክቱ ይድረሳቸው::ከምንም በላይ ቅንነት ያለበት ሕይወት ነው ፕሮፌሰር ያላቸው:: ክብር ለእግዛብሔር ይሁን❤

  • @yetemarechitafa3216
    @yetemarechitafa3216 3 ปีที่แล้ว +2

    እግዚአብሔር ሆይ እንደው በ እኛ እድሜ የሀገራች ሕዝብ በልቶ ጠግቦ አሳየን በምሕረትህ ጌታ

  • @yemisrachtariso3330
    @yemisrachtariso3330 3 ปีที่แล้ว +1

    በህይዎቶት ብዙ ትውልድ ይድናል እና መፅሐፍ ቢፁፉ እረጅም እድሜ ተመፕው

  • @zerihunzegeye9361
    @zerihunzegeye9361 3 ปีที่แล้ว +1

    የእግዚአብሔር ሰው የተባረክ ነህ ለዘላለም ተባርከ ቅር ይህንን ህይወት ማንም ሰው ቢካፈል መልካም ነው ቢዬ አስባለሁ ቲጂዬ አንቺም ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ እንደዚህ አይነት ሰው በእኛ ዘመን ማየቴና ምስክርነቱን መስማት በጣም ደስ ብሎኛል ትልቅ ትምህርት አግኝቻለሁ ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ በእውነት የተወደድክ አባታችን እንዳንተ አይነት በመንግሥት መስሪያ ቤት ውስጥ 10 ቢኖር ሀገር ትድናለች እግዚአብሔር ቀሪ ዘመንህን ይባርክ የተወደድክ ......❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

  • @zewdituzelleke4804
    @zewdituzelleke4804 3 ปีที่แล้ว +2

    ስንተኛ ጊዜዬ እንኳን እንደሆነ አላውቅም ምስክርነትህን ስሰማ እጅግ በጣም የሚደንቅ ምስክርነት ነው:: እግዚአብሔር ይባርክህ የኔ ወንድም🙏 አቅራቢዋም እግዚአብሔር ይባርክሽ::

  • @ShalomA38
    @ShalomA38 3 ปีที่แล้ว +16

    እግዚአብሔር ይባርካችሁ በጣም ጠቃሚ ጉዳይ ላይ ነዉ የቀረቡት :: የእኛ ትውልድ መዝሙርና ሰብሠባ ማብዛት እንጂ ቅንነት እንዳዚህ ዝቕ ያለ የክርስትና ሕይወት ያለን አመስልም :: ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን:: እናመሠግናለን ቲጂ

  • @emaadd4155
    @emaadd4155 3 ปีที่แล้ว +2

    ይኸ ታሪከዎ መጽሐፍ ቢሆን ብየ ተመኘሁ፡ ወላጆቸዎ በእውነት የተባረኩ ናቸው፡፡ ድል በድል ያራመደዎ አምላክ ክብርና ምስጋና ይድረሰው፡

  • @aresaheylu3312
    @aresaheylu3312 2 ปีที่แล้ว +1

    አመን አመን አመን ድንቅ የእግዚአብሔር በረከት ያለበት የፌጣር ጥበቃ ያልተለየ ሰዉ አሁንም ዘመን ይለምልም ትጅ ተባረክ ለቀጣይም እንደዝ አይነት አባቶች ትምርታዊ ቁምነገሮች የማስተላልፉ አቅርብልን ❤❤❤❤🙏🙏🙏🙏

  • @emeba951
    @emeba951 3 ปีที่แล้ว +16

    ዋው ግሩም የእግዚአብሔር ሥራ ፣ ድንቅ ምሥክርነት ፡ ተባረኩ !!

  • @almazsime4584
    @almazsime4584 3 ปีที่แล้ว +7

    እንደዚህ አይነት ሰዎች ወደ ፊት መምጣት ለምድርቱ በረከት ነው የእግዚአብሔርን ፅድቅ መግለጥ ይቻላል!ጌታ ይባርክህ ወንድማችን!!

  • @niyauuu123
    @niyauuu123 3 ปีที่แล้ว +1

    እ/ር አብዝቶ ይባርክ ያብዛልህ በአንተ ውስጥ እየሱስን አይቻለሁ ዘመን ይለምልም።

  • @fedilakedir3048
    @fedilakedir3048 ปีที่แล้ว

    ጌታ የሱስ ጌታ ነው
    ድንቅ ምስክርነት
    ህይወት መንፈስ ያለበት
    አጥንቴን ዘልቆ መቅኔ ውስጥ ገባ
    ድንቅዬ የጌታ ባሪያ
    ደስስስ አለኝ።
    ውውው
    ዋጋ ያስከፍላልና ክርስትና
    ገና ምኑ ተያዘና
    የአባቶቼን ወግ አይቼ
    የሀዋርያትና የነቢያትን ፅዋ ጠ ጥቼ
    ሽልማቴን እቀበላከሁ
    ገና ዋጋ እከፍላለሁ

  • @zessseyoum9963
    @zessseyoum9963 3 ปีที่แล้ว +19

    Wow! Amazing testimony! So much lesson we can take and practice in our life. I hope he is planning to write a book or two!
    How fortunate are his family and his friends!
    So proud of you sir!

  • @mebratgselassie434
    @mebratgselassie434 3 ปีที่แล้ว +7

    እ/ር ድንቅ አምላክ ነው፤ጌታዬን ስለእርስዎ፣ስለእናትዎና ስለአባትዎ እጅግ አከበርኩት። በእያንዳንዳችን ህይወት ብዙ የሚያስደንቅ ነገር እየስራ በሚገርም ከፍታ ላይ ያስቀምጠናል ፤የሚያሳዝነው ግን እነዚያ አሳዳጆች የጌታን ምህረት ሳይቀበሉ መሞታቸው ነው።መጨረሻችንን ያሳምርልን፣ፕ/ር ድንቅ የህይወት ጉዞ!!!! ቲጂዬ ተባረኪልኝ።

  • @ermiasmekuria3625
    @ermiasmekuria3625 3 ปีที่แล้ว +5

    ድንቅ የእግዚአብሔር የማዳን ሃይል ታሪክ:: ለዲሱ የሀገራችን ወጣቱ ትውልድ ልነገር ልታወጅ የሚገባ ታላቅ ምስክርነት:: ውድ ወንድሜ ፕ/ር ኢያሱ ከመሰከርከው በላይ ጌታ ስላደረገልህ ምህረቱንና ፀጋውን ስላበዛልህ አምላካችን ምስጋና ውዳሴ ክብር ይሁን:: አሜን!!
    ጌታ ለበለጠ ትጋት አገልግሎትና ሥራ ለማህበረሰቡ ህይወት ብልጽግና ያብቃህ አንተንና ቤተሰብህን ጌታ በጤንነትና በሰላም ይባርክ:: መልካም አዲስ ዓመትና ዘመን እመኝልሃለሁ::
    ተብረክ!!

  • @berhanufantu843
    @berhanufantu843 2 ปีที่แล้ว

    ዋው!!!!
    በጣም ልብ የሚነካ ምስክርነት ነው።ይህንን comment እየፃፍኩ እንኳን እንባ አየናነቀኝ ነው የምፅፈው።
    እርግጥ ነው
    እ/ር ያለቀን የተቆረጠን ነገር በዘመና መቀጠል ይችላል።ድንቅ ነው የአምላክ ስራ!!!!!
    ወላጅ እናቱን ምንያህል እንደሚወድና የልጅነት ህይወቱን የቀረፀች ቢዝቁት የማያልቅ ፍቅር በውስጡ የተከለች ጀግና እናት ነች።
    አንተ የኢትዮጵያ በረከት ነህ!!!!!
    ስላንተ እ/ር አምላክ ይመስገን!!!!

  • @asegashassefa3712
    @asegashassefa3712 3 ปีที่แล้ว +1

    ለኔ አባቴ ነህ ፕሮፌሰር ግን እንደዚህ አላውቅም ነበር ተባረክልኝ ። ለሁላችንም መፅሀፍ አንብበን ከምናገኘው እውቀት ይልቅ ህይወትህ አስተምሮኛል ። በስጋ እውቀትም በመንፈሳዊም ቀዳሚ መሆን እንደሚቻል ያም ቁልፉ ለእግዚአብሔር እውቅና መስጠት እንደሆነ ተምሬበታለሁ ።

  • @emmyt311
    @emmyt311 3 ปีที่แล้ว +3

    አቤት ጌታ ስንትትትት የተባረኩ ልጆች አሉት⁉ፕሮፌሰርዬ የሰማይ አምላክ ዘመኖን ያለምልመው ነብስ እረሰረሰች‼ ቲጅዬ ተባረኪ‼♥ እየሱስ ጌታ ነው🙏‼

  • @yohannesagonafir8230
    @yohannesagonafir8230 3 ปีที่แล้ว +5

    መልካም ምስክርነት። ስሙትና ተማሩበት። ሳይንቲስትና አማኝ ሆኖ እግዚአብሔርን ማገልገል ይቻላል። ፕ/ር ተባረክ!!"

  • @meserethabtamu5988
    @meserethabtamu5988 3 ปีที่แล้ว +8

    I am proud to say prof. Eyasu is my adviser. His comments are always positive, extremely perceptive, helpful and appropriate. It is a privilege to have you prof. God bless you most!

  • @nebertali9708
    @nebertali9708 3 ปีที่แล้ว +9

    ቲጂዬ በጣም እናመሰግናለን ብዙ ነገር ሰንቀናል በሕይወት ፍሬ እድናፈራበት የጌታ ፀጋ ለሁላችንም ይብዛልን ተባረኩ🙏

  • @mamitushikur5918
    @mamitushikur5918 3 ปีที่แล้ว +19

    This is pure Gospel! Glory to God👏Living testimony of God’s faithfulness 🙌🏿 we can listen to you all day long sir! እግዚአብሔር ይገነባል🙌🏿Amen! It’s all about God💯Our God is Able🙌🏿
    You ignite the fire in me!
    Sending my blessings🙏🏻🙏🏻

  • @ሳርዬ
    @ሳርዬ 3 ปีที่แล้ว

    Woooooooowww እንዴት ድንቅ ምስክርነት ነው. ጌታ ስሙ ይባርክ እጅግ በጣም ተባርኪያለሁ ኢየሱስ ያድናል እኛ አማኛች በሁሉ ስራ ዘርፌ ልንገለጥ ልንስራ ያስፍልጋል ፕሮፍስር እግዚአብህር ይባርክህ ቀሪ ዘመኖት ይለምልም ኢየሱስ ጌታ ነው ንፍሴ ሃሴት ተሞላች ውንጌል ብዙ ዋጋ የተክፍለበት ነው ዛሪ ለኛ ነገ ለልጅቻችን መልካም ነገር ማስቀመጥ ግድ ይለናል አሁንም ፀጋው ይብዛ ፀጋ ልዩ ልዩ ነው መንፍስ ግን አንድ ነው አደል የሚለው ቃሎ በተለይ ደጋግመው ስለ ፀድቅ ስለ ቅድስና ይናገሩ ነበር እና እውነት ነው ህይውታችን ይቀድስ ፀድቅ ማድርግ ይብዛልን
    ስለቤተስብ ሲመስክሩ ነፍሴ ሃሴት አደርገች ቤተስቤን በጣም አክብራለሁ ቀና ብዬም አላይ አሁን እንኮን እውጭ ሆኜ የነሱን ትእዛዝ እጠቡቃለሁ ዛሪ ላይ መቁሜ በቤተስቤ ምርቃትና ባርኩት ነው ክጌታ በታች ክብር ይገባቸዋል ተባርኩልኝ. ትጅዬ ብሩክ ነሽ ደሞ ሁሌም አለባበስሽን አደንቃለሁ ስርአትሽ ደስ ይለኛል በካውንሰሉ የዘመርሽው ዝማሪ ውስጤ ነው የቀርው ና የጥንቱ ኢየሱስ ና የናዝሪቱ እየሱስ ስትዘምሪ እንባ አይኖቼ ተሙሉ. ተባርኪ ለምልሜ።።።።።።።።።

  • @HilinaT-ef5pz
    @HilinaT-ef5pz 3 ปีที่แล้ว +1

    እንዴት ደስ እንደሚሉ ብዙ ተማርኩ ብዙ ተጽናናሁ ጌታ ይባረክ እጅ እድሜ እናንተን ሳይ ኢትዮጵያ ተስፋ አላት

  • @wakumageleta4782
    @wakumageleta4782 2 ปีที่แล้ว

    እጅግ የሚያስደንቅ የሕይወት ምሰከረነት ነዉ ስሰማ ትጅዬእኔም የደረግ ጊዜ እኔነም ይህ ህይወት ውሰጥ አልፋለሁ እስር torched ተደርጌአለሁ ከሥራም ተባብሬ ነበር ለመልካም ሆነልኝ ገታ ቲጂ ዬ ይባረክሽ መልካም አገልግሎት ነው ዋጋሽ ከሰማይ ነዉ❤❤😁!!

  • @belhumamo797
    @belhumamo797 2 ปีที่แล้ว

    ፐሮፊስር ጌታ አሁንም ዘምንህ ይባረክ ሰለቤተብህ የሰጠህው ምስክነት ትልቅ ነው ለቤተሰባችው ክብር የሌላችው ብዙ አሉ አሳድገው የተጣሉ ቤቱ ይቁጠረው

  • @Dara-zr7kg
    @Dara-zr7kg 3 ปีที่แล้ว

    ከሰባት ዓመት በፊት እግዚአብሔር ይህን የተከበሩ
    ፕ/ር ተጠቅሞ ለጥያቄ መልስ ሆኖልኛል
    በአካል አላውቃቸውም በኢሜይል ብቻ ነው የምንገናኘው
    የዛሬው የህይወት ምስክርነት ለወደፊቱ ብዙ ትምህርት የተማርኩበት ነው።
    Bless you!!

  • @miminigussie2794
    @miminigussie2794 3 ปีที่แล้ว +1

    ድንቅ ኢትዮጵያዊ እርሶን የመሰለ ኢትዮጵያዊ መኖሩን በማወቄ ደስ ብሎኛል ለካ ዶ/ር አብይ ብዙ የሚያግዙት ድንቅ ኢትዮጵያውያን አሉት እፎይ ደስ አለኝ🙏

  • @hiwotayele5028
    @hiwotayele5028 3 ปีที่แล้ว +1

    አሁንም የጌታ ፀጋ ይብዛሎት ። እጅግ በጣም ተጠቅሜያለሁ ።

  • @gezachewbegashaw1281
    @gezachewbegashaw1281 ปีที่แล้ว

    የሚገርም የትውልድ አባት መሆን የሚችል ትልቅ ሰው። Your humility is humbling. Geta yibarkih wendimachin. God bless you 🙏

  • @HeadUpBiblicalTherap
    @HeadUpBiblicalTherap 3 ปีที่แล้ว +13

    I have no words , how Amazing this is !
    Praise God that God has his own people at every season .
    You both stay blessed

  • @ayinadistilahun6268
    @ayinadistilahun6268 3 ปีที่แล้ว +2

    ፕሮፌሰር እያሱ……በእውነት ጥሩ ምስክርነት ነው የሰማሁት እግዚአብሄር ዘመንህን ይባርክ…… በአካል ባገኞት ደስ ይለኛል

  • @gezahegnberato8515
    @gezahegnberato8515 3 ปีที่แล้ว +3

    ፕሮፌሴር እግዚአብሄር ለንተ ስለሣጣው እውቀትና ፀጋ ጌታዬን እጅግ አከብረዋላሁ።

  • @bezuneshnata4421
    @bezuneshnata4421 3 ปีที่แล้ว +3

    ይገርማል እንደዚህ አይነት የእግዚአብሔር አገልጋይ በዚህ ዘመን መገኘቱ በጣም ድንቅ ነገር ነው እንደእሳቸው አይነት ለእግዚአብሔር የሚኖር ለእውነት የሚኖር እውነተኛ አማኞችን ያብዛልን ይነሱልን

  • @nurobetselotzeleke7585
    @nurobetselotzeleke7585 2 ปีที่แล้ว +1

    ፕሮፌሰር ጌታ ይባርኮት! ቅንነቱዎ፣ ትህትናዎ፣ አስተሳሰቦትና ከንግግሮ ልቆ የሚናገረው ስሜቶ ልብ የሚነካ ነው። እስከ ዛሬ በሰሩባቸው ተቋማት መሳካትን የሰጦት ጌታ አሁንም እርሱ ይርዳዎት! እንወዶታለን!!!

  • @asteryalew8657
    @asteryalew8657 3 ปีที่แล้ว +1

    ዋው ፕ/ር መልካም ትምርታዊ ምሥክርነት ነው ዘመንህ ይባረክ !ያከበርከው ጌታ ሥላከበረህ ክብር ለሥሙ ይሁን ! ለአማኝ ጥሩ ተምሣሌት ነህ ልብ ያለው ልብ ይበል !

  • @asterlebene9946
    @asterlebene9946 2 ปีที่แล้ว +3

    ጌታ ዘመንህን ይባርክ እንደዚ ዋጋ ተከፍሎ የተሰጠንን ወንጌል በአግባብ ለማሰተላለፍ ጌታ ይርዳን እኛ አሁን እንደ ሀይማኖት ለልጆቻችን እያሰተላለፍን ውጤቱን እያየን ነው ትውልድ እያመለጠን ነው ንሰሀ ያሰፈልገናል ማረን ማረን 😭😭😭😭

  • @tesfayebirhane7454
    @tesfayebirhane7454 3 ปีที่แล้ว +2

    ዋው ፕ/ር እግዚአብሔር አምላክ ይባረክህ በእውነት እንዴት እንደተባርክሁ እግዚአብሔር አምላክ እንደዚህ አይነት ወንድምችን ለወንጊል የጭቀኑ ለም መኑ ምሣሌ የሆኑትን ያብዛልን

  • @hiwotkasahun980
    @hiwotkasahun980 3 ปีที่แล้ว +5

    ፕሮፌሰር እጅግ ብዙ አስተማሩኝ ነፍስም አልቀረልኝ ያብዛዎት፣ እድሜ ከጤና ጋር ይጨምርልዎት ፤ ቲጂዬ አንቺም ተባረኪ እወድሻለሁ

  • @tiruneshbeyene2896
    @tiruneshbeyene2896 3 ปีที่แล้ว +1

    ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን
    " በጌታ ደስ ይበልህ የልብህን መሻት ይሰጥሃል" ተብሎ ተጽፉአልና ወንድሜ ሆይ
    እንደዚህ ያለ ልብ ያላቸውን ወገኖች ለኢትዮጵያ ያብዛልን ይጨምር:: የርሰዎንም
    የልብ መሻት ይስጥዎታልና ድጋሜ ምስክርነትን ለማቅረ ዕድሜን ይጨምርልዎ
    እያልኩ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን እላለሁ:

  • @samrawitasefa880
    @samrawitasefa880 3 ปีที่แล้ว +21

    ደስ የሚሉ አባት እግዚአብሔር ይባርኮት እንደርሶ አይነቱን ያብዛልን ቲጂዬ ምርጥ ጀግና የአባቴ ብሩክ እወድሻለሁ

  • @dawitberhane1825
    @dawitberhane1825 3 ปีที่แล้ว +15

    We love you our Br. In the Lord Jesus Christ. You showes us the glimpse of kingdom life and, keep shining until that great day of our Lord appears. I believe you are one of the model's of this days.

    • @sanadubai2365
      @sanadubai2365 2 ปีที่แล้ว

      Dimknew☝️☝️☝️🙏🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️🌹🌹🌹🌹🌹

  • @debebeteklu1451
    @debebeteklu1451 3 ปีที่แล้ว +7

    A very candid & distinguished man! What a blessing he is to our country!!!
    Thank you, TG, for bringing this great man on your show!

    • @meztesh1997
      @meztesh1997 3 ปีที่แล้ว

      A great man indeed!

  • @cecew.2559
    @cecew.2559 3 ปีที่แล้ว +1

    ቃለ መጠይቁን ሁለቴ ደግሜ ነዉ የሰማሁት እጅግ ልብ ይነካል። ፕሮፌሰር ኢያሱ በሚማርክ ሁኔታ ነዉ የህይወት ምሥክርነቱን ያጋራን።ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ የእግዚአብሔርን አብሮነትና በጎነት እያላቀ ነበር። እንዲሁም ለወንጌል የሚከፈለዉ መሥዋዕትነት በከንቱ እንደማይቀር ብዙ በረከት እንዳለዉ አድምቆ አሳይቶናል። እግዚአብሔር አምላክ አሁንም እየባረከ ይባርከዉ። ትጂዬ በጣም እናመሰግናለን አንቺም ጎበዝ ጠያቂ ነሽ በጣም ነዉ ምወድሽ።
    ተባረኩልን!

    • @alemtshayghiwot7524
      @alemtshayghiwot7524 3 ปีที่แล้ว

      በእውነት መንፈስ ቅዱስ በአንተ እንዴት እንደሰራ ትክክለኛ ፃድቅ ምስክር ነህ ዘመንህ ሁሉ ይባረክ።

    • @abadidagnew2321
      @abadidagnew2321 3 ปีที่แล้ว

      የሚገርም ሕይወትን የሚገነባ እጅግ አስተማሪ መካሪ የሆነ የሕወት ስንቅ የ 2014 ትልቅ መንፈሳዊ ስጦታ መልካም ምስክርነት ነው። ስለዚህ ሁሉም ሊማርበት ይገባል እንደዚህ ዓይነት ምስክርነት ሕይወትን ይገነባል። ፕ/ር ኢያሱ ዘመናቸው ይለምልም በሚበልጥ ክብርና በረከት መገለጥ ይሁንላቸው። አዘጋጆችና አቅራቢዎችም ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ ቀጥሉበት!!!!!

  • @tsehaywondimu993
    @tsehaywondimu993 3 ปีที่แล้ว

    ቲጂዬ አንቺ መቼም የተባረክሽ ነሽ ውስጥሽም ውጭሽም ያማረ በጣም እንወድሻለን ዘመንሽ ይለምልም ጌታ አንቺን ለቤተክርስቲያናችን በረከት አደርጎ ስለሰጠን ጌታ እናመሰግናለን በሁሉ አቅጣጫ እየጠቀምሽን ስለሆነ ጌታ ደጋግሞ የምትሰፊበትን በብዙ የምታገለግይበትን ፀጋ ያብዛልሽ ድንቅ ምስክርነት እናመሰግናለን፡፡

  • @gospelchannel4957
    @gospelchannel4957 3 ปีที่แล้ว +9

    Indeed a blessing, inspiring and exemplary for present day Christians. Thank you TG, Thank you dear prof Eyasu.

  • @ekhcnationalyouthministry2251
    @ekhcnationalyouthministry2251 3 ปีที่แล้ว

    ፕሮፌሰር ኢያሱ እግዚአብሔር እንደት ትንታግ ከእሳት ውስጥ ያወጣቸው የወንጌል ውጤት የሆኑ ታላቅ ወንድም ናቸው፡፡ ለጌታ ያላቸው ፍቅር፣ የሥራ ትጋታቸውና ቀለል ብለው ሳያካብዱ ሰውን ማገልገል ከሚችሉ ጥቂቶች የሚቆጠሩ፣ የዛሬ ስኬታቸው የሸፈነውን ብዙዎች የሚደብቁትን ትላንት ለረዳቸው ጌታ ክብርና ለሌሎች መታነጽ በቀላል ቋንቋ ገላልጠው በመናገር ሌሎችን ማስተማር የሚችሉ ሰው ናቸው፡፡ አገራቸውንም ሲወዱና ሲያገለግሉ የቆዩ አሁንም ለማገልገል እየተዘጋጁ ካሉ ልበ ቅኖች አንዱ አባት (ታላቅ ወንድም) ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ቅኖችን ያብዛልን፡፡ አባቴ ጌታ ኢየሱስ ዝቅ ብለው እንዳከበሩት ጨምሮ ያክብርልን! እንወዶታለን!

  • @bereketdemissie1147
    @bereketdemissie1147 3 ปีที่แล้ว +6

    Amazing testimony of a man with high elegance! May God keep favoring you and your belongings to the end! Much respect!!

  • @geneth5195
    @geneth5195 3 ปีที่แล้ว +2

    ጌታ እየሱስ አብዝቶ ይባርክህ:: እንድ አንተ ይሉትን ያብዛልን:: ውለታህ በቃላት የሚገለፅ አይደለም:: you are a total package! God bless you!!

  • @alemthehaygebeyehu1840
    @alemthehaygebeyehu1840 3 ปีที่แล้ว +5

    አግዚያብሄር ይገነባል ገንቢ ነው.....praise God 🙌 He is a God of restoration....!!!

  • @lilitsegaye3899
    @lilitsegaye3899 3 ปีที่แล้ว +1

    ጌታ እየሱስ አሰራሩ ድንቅ ነው ስምህ ይባረክ

  • @abrahamberhanu3806
    @abrahamberhanu3806 2 ปีที่แล้ว +1

    I watched it in 2015 EC. But I received great lessons for life long. Thank you professor. May God bless you more and more!!! TG God bless you too.

  • @getinetkaba5993
    @getinetkaba5993 3 ปีที่แล้ว

    እጅግ በጣም አስተማሪ ምስክርነትና ካውንስል ነክ ብዥታን ያጠራ ነው ። Respect professor !!

  • @Godisgreat88J
    @Godisgreat88J 3 ปีที่แล้ว

    የፕ/ር ኢያሱ ኤልያስ የህይወት ምስክርነት፣ እጅግ በጣም አስተማሪ ነው። በህይወቱ እጅግ ተባርኬአለሁ።

  • @hannamekonnen8042
    @hannamekonnen8042 3 ปีที่แล้ว +4

    Can't stop listening this amazing testimony ....May God bless your life ahead.

  • @fghh5572
    @fghh5572 3 ปีที่แล้ว +1

    እሂ ሁሉን መከራ ስቃይ ያዮ የወንጌል አባቶቻችንን ልንዘክር ምስጋና አክብሮት ልንሰጣቸው ይገባል የህይወትን ጣዕም አሳይተውናል ክርስቶስን አስተዋውቀውናል ነብሳችንን ከሲኦል ታድገዋል እናመሰግናለን አሁንም እድሜና ፀጋን ያብዛላችሁ💞😢💔🙏

  • @tamirathailu133
    @tamirathailu133 3 ปีที่แล้ว +8

    Powerful life tetimony ! More grace and blessings to you!!!

  • @hanatolina566
    @hanatolina566 3 ปีที่แล้ว

    በእውነት በጣም የተባረኩበት ምስክርነት ነው ጌታ ቀራ የስራ ዘመኖን ይባርክ. 🙏🙏🙏❤❤

    • @hanatolina566
      @hanatolina566 3 ปีที่แล้ว

      እውነት መንፈስ ቅድስ በምስክርነቶ ውስጥ አልፎ ባርኮኛል. ጌታ ይመስገን

    • @hanatolina566
      @hanatolina566 3 ปีที่แล้ว

      ጌታ ወላጆቸህን ጨምሮ ይባርክ 🙏🙏🙏

  • @tsegayemetaferia6373
    @tsegayemetaferia6373 3 ปีที่แล้ว +2

    ከምንም ነገር ነፃ የሆነና ለእውነት ወንጌል የቆመ እግዚአብሔር ለዘመናችን ያስነሳልን ትልቅ የእግዚአብሔር ሰው ።

  • @axumcake
    @axumcake 3 ปีที่แล้ว +2

    እግዚአብሔር ይባርክሽ ቲጂዬ ብዙ ብዙ ትምህርት ሊሰጡን የሚችሉ ከህይወታቸው እግዚአብሔርን የሚያሳዩ ሰዎችን ስለምታቀርቢልን። ፕሮፌሰር እኔ ገና ዛሬ ነው ያየሁት በተለይ ቤተሰብን አገርን ስለመጥቀም መነሻን ስለአለመርሳት የተናገሩት በልቤ ቀርቷል ፡ እንደዚህ አይነት ክርስትናን ግብረገብን ጥንካሬን የሚያስተምሩ ሰዎች ይህ ትውልድ ይፈልጋል ፡ እኔ ከእርስዎ ዛሬ የተማርኩት በተሰማራሁበት የስራ እና የትምህርት ዘርፍ ጌታንም እያገለገልኩ ውጤታማ መሆን እንደምችል ነው ።

  • @beamlaktesfaye9963
    @beamlaktesfaye9963 3 ปีที่แล้ว +4

    God Bless You Papa Professor Eyasu, truly inspired by your story and well informed the price our fathers and mothers have paid for the Gospel of Christ. I feel responsible because now is our turn to pay the price,

  • @betsegadegnalehu4484
    @betsegadegnalehu4484 3 ปีที่แล้ว +2

    እግዚአብሔር ይመስገን ሰው አለው ቅሬታ አለው የጠፉትን የሳቱትን የሚመልስበት፡፡ የኛ ጌታ ኢየሱስ ተባረክ ተመስገን ለዘለዓለም ፀጋ ይብዛላችሁ፡፡

  • @SennvLove-m9f
    @SennvLove-m9f ปีที่แล้ว

    wow wow ምን ብዬ መፃፍ እንዳለብኝ አላውቅም ዝም ብለክ ተባረክ ውድ ያባቴ ልጅ እስከ ፍፃሜክ ብርክ በልልን ለዚ ዘመን ታስፈልገናለክ ❤❤

  • @azebgera8601
    @azebgera8601 2 ปีที่แล้ว

    አቤት የንግግር ችሎታህ ውሰጥህን ያሰጎበኛል ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እመኝልለሐለሁ አሁንም ጨምሮ ፈጣሪ ይባርክህ ፖ 🙏

  • @abayabay690
    @abayabay690 3 ปีที่แล้ว +3

    እግዚአብሔር እንደዚህ አይነት ሰዎች ለምድራችን ያብዛልን :: እግዚአብሔር ዘመኖትን ይባርክ እረጅም እድሜ ይስጦት!

  • @habtamudegu2024
    @habtamudegu2024 2 ปีที่แล้ว

    amazing. I can not expect this. ooooh Jesus you are beyond my understanding. I simply say be glory n the highest. professor long life and good working time to our country.

  • @terefezewde4533
    @terefezewde4533 3 ปีที่แล้ว

    ወንድማችን በእውነት ምን ልበል በጣም የምትገርም ወንድማችን፥የምትወደው እግዚአብሔር አሁንም ከዚህ በበለጠ ጸጋ እና ባርኮት ያብዛልህ ። እግዚአብሔር በሁሉም አቅጣጫ ያስፋህ ። አምናለሁ እንደ ስምህ ይህችን ምድር ይዘህ እግዚአብሔር ወዳየልን ከፍታ እንደምታሻግር።በመንገድህ ሁሉ እግዚአብሔር ጥበብ ማስተዋሉን ይብዛልህ ።ዘርህና ትውልድህ ይባረክ።

  • @matuselahelamo1216
    @matuselahelamo1216 3 ปีที่แล้ว +1

    ዋዉ በጣም አስተማሪ መልዕክት ነው ; የህይወት ትርጉም እንድህ ስሆን ።።።። ተበረኩ ።

  • @asterhabte7069
    @asterhabte7069 3 ปีที่แล้ว +2

    እንዲህ ያባቶችን የናቶችን ምስክርነት መስማት በጣም ደስ ይላል ቤተክርስትያን በብዙ መከራ እዚህ እንደደረሰች እንማራለን ተባረኩልኝ

  • @amanuelmathewos6186
    @amanuelmathewos6186 3 ปีที่แล้ว +4

    What amazing testimony.
    God bless you, Professor!

  • @assefatolla3077
    @assefatolla3077 3 ปีที่แล้ว +13

    You are a preacher. God bless you a man of God.

  • @yonaspina438
    @yonaspina438 3 ปีที่แล้ว +11

    TG you are so blessed
    thank you its a great message to those who so called "apologistic" and falsely accused the council.
    I can't get enough word to describe my appreciation to the real Christian and servant of the Lord he is so much blessed .

  • @solomontekalign5974
    @solomontekalign5974 3 ปีที่แล้ว +2

    It is very awesome witness from a senior and elder brother whom I know since long. I am happy to hear from my dear elder brother and hero. It took me back to my high school memo at Sawla. All the challenges that is passed while having high school education and until university. I share some of the high school and life that we have It is an eye opening and a leading testimony for mothers and fathers too. Dear Prof Eyasu Elias, stay blessed. Sincerely,
    Solomon Tekalign (PhD) Associate Professor, Haramaya University, Ethiopia from Zala through Sawla and to AA and now at your Haramaya University, Ethiopia.

  • @yenebecha7099
    @yenebecha7099 2 ปีที่แล้ว +1

    ዋው ለእርሦዎ የደረሰ ጌታ ለእኔና ለዘሬ ይድረሥ ❤❤❤

  • @yacobhailu2812
    @yacobhailu2812 3 ปีที่แล้ว

    እግዚአብሔር ይባረክልን! በገታ ወንድማችን ፕሮፌሰር እንደ እርሶ ያሉትን ጌታ ያብዛልን ፡፡በጣም ደስ ያለኝ ባላውቃቸውም ለባለቤቶ “ፕ/ር” ብዙዬ ጌታ ይባርክልን ይባርክልን! ለኢትዮጵያ እናቶች እህቶች በሙሉ ጌታ ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን፡፡እኔም ስለ እናቴ ወዘሮ ጠጄ ሳስብ እንባ ያንቀኛል፡፡ብቻ በአገራችን የእናቶቻችን ሚና በቀላሉ የሚገለጥ አይደለም፡፡

  • @her-bel
    @her-bel 3 ปีที่แล้ว +1

    What a testimony !!! God bless you more and more Professor. Thank you Tigi.

  • @abelgetu251
    @abelgetu251 3 ปีที่แล้ว +9

    እግዚአብሄር ዘመንህን ቤተሰብህን ሀሳብህን እቅድህን ሁሉ ይባርክ!!!!!!

  • @senaitshumeegato1803
    @senaitshumeegato1803 3 ปีที่แล้ว +2

    ፕሮፌሰር ጌታ ኢየሱስ አሁንም ዘመንህን ይባርክህ 🌻🌻🌻እንዳተ አይነት ልቦችን ያብዛልን ይስጠንየእውነት ወንጌል ሰብከኸናል ጆሮ ያለው ይስማ 🙏🙏🙏