AMHARIC POEM MULLUGETA TESFAYE -ሙሉጌታ ተስፋዬ - BY SOLOMON NIGUS

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 6 ก.พ. 2025
  • ..የአያ ሙሌ ነገር ግራ ነው! ሕይወቱም ሲበዛ ዥንጉርጉር ናት፡፡
    ለምሳሌ ተራ ገጣሚ ነው እንዳንል እጅግ ተወዳጆቹ ሙዚቃዎች የርሱ አሻራ ያረፈባቸው ኾነው እናገኛለን፡፡ ብኩን ሰው ነው እንዳንል በኢህአፓ እሳት ፖለቲካ ዉስጥ ተወልዶ፣ በማርክሲዝም ሌኒኒዝም ነዶ፣ በብአዴን በስሎ፣ በNGO ደመወዝ ከብሮ፣ በኢህአዴግ ላዕላይ ቤት ገብቶ፣ በጋዜጠኝነት ሠርቶ፣ ከመንግሥት አፓርታማ ተበርክቶለት የሴኮ ቱሬ ጎረቤት ኾኖ የኖረ ሰው ነው፡፡
    ደግሞ ያን ሰምተን ለአንቱታ ስናዘጋጀው ድንገት ሥራውን ጥሎ ይጠፋል፡፡ ዘበኛ፣ ኩሊ፣ ወዛደር፣ ጎዳና ተዳዳሪ ይሆናል፡፡ ብቻ ያያ ሙሌ ነገር ለወሬም አይመች፡፡
    ---
    ፍቅር አዲስ "አንድ ሰው " የታምራት ደስታ "ሃኪሜ ነሽ "ብጽአት ስዩም ‹‹አደራ ልጄን አደራ›› እያለች በእንባ የምታዜመውን ግጥም የጻፈላት ሙሌ ነው፡፡ ለአበበ ተካ ‹‹ወፊቱ››ን የጻፈለት ሙሌ ነው፡፡ ለሀና ሸንቁጤ፣ ለኩኩ ሰብስቤ እያልን ብንቀጥል ማቆምያ የለንም፡፡ ቆንጥሮ እየሰጠ አንበሽብሿቸዋል፤ ፍዝ ኾኖ አድምቋቸዋል፡፡ እነሱን የዝና ማማ ላይ ሰቅሎ እሱ እታች ወርዶ ይተኛል፡፡ ጎዳና፡፡

ความคิดเห็น • 1