የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 6 ጎዳናውን አቅኑ በማሙሻ ፈንታ | Matthew Teaching 6 Make His paths straight By Mamusha Fenta

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 14 ม.ค. 2025

ความคิดเห็น • 72

  • @equipmedia2577
    @equipmedia2577  ปีที่แล้ว +46

    #እነሆ_ንጉሥሽ
    #የማቴዎስ_ወንጌል_ትምህርት
    #ጎዳናውን_አቅኑ
    📖 ማቴ 3 : 1-12
    * የዮሐንስ አገልግሎት /ስብከት / ወንጌል
    - ነገሥታት የሚሔዱባቸው መንገዶች ይጠረጋሉ፤ ይስተካከላሉ።
    - በዚህ ክፍል የንጉሡ መንገድ ጠረጋን እንመለከታለን። ዮሐንስ አጥማቂ ብቻ አይደለም፤ እያጠመቀ ለንጉሡ መንገድ ጠራጊም ነበር።
    - የዮሐንስ መልዕክቱ፤ አገልግሎቱ፤ ስራው ወንጌል ነው።
    - ኢሳ 40፡3 ላይ መልዕክተኛዬን እልካለሁ ያለው ይፈጸም ዮሐንስ መጥቷል።
    - "የጌታን መንገድ አዘጋጁ" ሲል "የጌታ" የሚለው "ያህዌን" ነው። የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ እያለ ነው። የኢየሱስን አምላክነት ያሳያል።
    - ዮሐንስ እንዴት ነው መንገዱን ያቀናው? በመስበክ። ዮሐንስ እየሰበከ መጣ፤ መስበክ የግል አስተያየት አይደለም፤ የሚመስለንን ማብራራት አይደለም፤ የሚያነቃቁና ደስ የሚሉንን ነገሮች መንገሪያ አይደለም። አዋጅ ነው፤ የበላይ አካል ትዕዛዝ ማወጃ ነው።
    - የሰው ልብ የሚቀናው በስብከት ነው።
    - ቁ 4-6 (የማይማርከው ማራኪ)
    - አለባበሱ የሚስብ አልነበረም፤ የማረከው በልብሱ አይደለም።
    - ዮሐንስ የበረሀ ሰው ነበር፤ ሰውን ለመማረክ ያደረገው ነገር የለም። አመጣጡ ቀላል ነው ተጽዕኖ የሚያመጣ አልነበረም።
    - ተጽዕኖው እስከ መንግስት ድረስ ይነቀንቅ ነበር። አገር በሙሉ ሀጢአታቸውን እየተናዘዙ ወደሱ ይወጡ ነበር።
    - ተጽዕኖው ከልብሱ ያለፈ፣ ከአኗኗሩ ያለፈ፣ ከገጽታው ያለፈ ነበር።
    - ጎዳናውን ማቅናት፣ ኢየሱስን ማድመቅ ይሔ ነው፤ እኔ ላንስ እርሱ ግን ሊልቅ ይገባል ማለት።
    - አገልግሎት ራሳችንን በድምር ማስተዋወቅ አይደለም።
    - ዮሐንስ ሲታይ የማይማርክ ነው፤ ያልማረከው ግን የለም። ምክንያቱም የሰበከው ወንጌል ነው። ድምጻዊውን ዝቅ አድርጎ ድምጹን ያሰማ ነበረ።
    - በዚህ ጊዜ "ስለእኛ" በዝቷል፣ ተለይቶ ለመታየት በዝቷል። የአካባቢውን ለመምሰል ሳይሆን በመለየት ነው መታየት የምንፈልገው።
    - የዮሐንስ ድምጽ ቤተመንግስት ሊደርስ የቻለው ቀላል ስለነበረ፣ ራሱን ለማጉላት የሚጥር ሰው ስላልነበረ ነው።
    - እኛ ቀለል ብለን ኢየሱስ ይክበድ። የአገልግሎት መለኪያው ኢየሱስ መአዛው ሲሸት፣ ሲወጣ ይሔ ነው ወንጌል።
    - በሔድንበት ሁለ የክርስቶስን ሽታ ይዘን መሔድ አለብን።ኀ
    - የዮሐንስ መልዕክቱ ከቁ7-12 ይገለጣል።
    * ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግቢያው (ከሚመጣው ቁጣ ማምለጫው) ትምክህትን አስወግዶ፤ ከክርስቶስ ጋረሰ ተጣብቆ የተለየ ኑሮ መኖር፤ ፍሬ ማፍራት ነው።
    - የመልዕክቱ አይነት :- መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሀ ግቡ፤ አቅጣጫ ቀይሩ ነው።
    - "መንግስተ ሰማያት" የሚላት የእግዚአብሔር መንግስትን ነው፤ ነገር ግን የምንወርሰውን መንግስት አድራሻ እየተናገረ አይደለም። የስፍራ መጠቆሚያ ሳይሆን "ሰማይ" ማለት "እግዚአብሔር" መሆኑን ለመግለጽ ነው።
    - ይዚህችን የእግዚአብሔር መንግስት ዮሐንስ የዘላለም ሕይወት ይላታል።
    - ዮሐንስ መንግስተ ሰማያትን ቀርባለችና ካልተቀበልናት የሚመጣ ቁጣ አለ ይላል። ጻድቁ እግዚአብሔር ሀጢአትን በሚቀጣበት ጊዜ የዘላለም ቁጣ ይጠብቀናል።
    - የእግዚአብሔር መንግስት መግባት ከሚመጣው ቁጣ መዳን ነው። ወደ ኢየሱስ ስንመጣ ከሲኦል አምልጠናል።
    - የአብርሃም ልጅነት ከመንፈስ፤ በክርስቶስ በመወለድ የተገኘው።
    📖 ገላ 3:7
    * ከዘላለም ቁጣ ለማምለጥ
    1) ትምክህት አስወዱ
    2) ከኢየሱስ ጋር ተጣበቁ
    - ትምክህት አይሸሽግም።
    - ለንስሀ የሚገባ ፍሬ አድርጉ።
    - ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይበረታል ይላል ዮሐንስ።
    - ትምክህት ስበሩና በመንፈስና በእሳት ወደሚያጠመምቀው ኑ ይላል።
    - በመንፈስና በእሳት ማጥመቅ የእግዚአብሔር ልብን የማጥራት፤ ቆሻሻን የማቅለጥ ስራ የሚሰራበት ነው።
    - ዮሐንስ እኔን ተዉና በሱ ተጣበቁና ፍሬ አፍሩ ይላል።
    - ወደ ኢየሱስ መምጣት አጥርቶን ፍሬ እንድናፈራ ያደርገናል።
    - ዮሐንስ የሰበከው ወንጌል፥ አማኝነት ፤ የህይወት ለውጥ ነው።
    - ወደ ኢየሱስ የመጣነው በነበርንበት ለመቀጠል ፈቃድ ለማግኘት አይደለም። ጸጋ እንደፈለግን የመኖር ፈቃድ አይደለም። የታጠብነው በጸዳ ህይወት እንድንኖር ነው። ኢየሱስ ጋር የተተከልነው መልካም ፍሬ እንድናፈራ ነው። ፍሬአችን መልካም ስራችን ነው።
    - የዘላለም ሕይወት በስራችን አይገኝም።
    - ሀይማኖት ውስጥ መወለድ ዋስትና አይደለም።

    • @rebeccachristian3365
      @rebeccachristian3365 ปีที่แล้ว +2

      Thank you for attaching the note 📝

    • @lemlemghebremedhinweldeghi5205
      @lemlemghebremedhinweldeghi5205 ปีที่แล้ว +1

      መንፈስ ቅዱስ ስለገለጠው ትምህርት ስሙ ይባረክ፡ ወንድም ማሙሻ ደግሞ ለተጠራህበት ጥሪ ስለታዘዝክ ተጠቅመናል እና ፀጋው ጨምሮ ይብዛልህ !!

    • @መኖሪያዬየዘላለምአምላክእ
      @መኖሪያዬየዘላለምአምላክእ ปีที่แล้ว +1

      በፍሁፍ የምታስቀምጡትን በጣም ወድጄዋለሁ በደብተሬ ላይ ፅፌዋለሁ እኔ በግሌ በጣም ወድጄዋለሁ ተባረኩልኝ

    • @jesusiscoming-repent
      @jesusiscoming-repent ปีที่แล้ว

      I don't even know how to thank you guys for your diligence. May God bless every one of you.
      Thanks to technology we can hear and read this over and over again..

  • @rodasgetachew9347
    @rodasgetachew9347 ปีที่แล้ว +6

    አሜን ህይወታችን የልባችን ጎዳና ለያህዌ ቀንቶ ተዘጋጅቶ በመንፈሰ ቅዱስ በእሳት ተቀድሶ ጠርቶ ታጥቦ የህይወት ለውጥ ሆኖልን ትምክህትን ሰብረን ከኢየሱስ ጋር ተጣብቀን ለንስሐ የሚገባ መልካም ፍሬ አፍርተን ...አፍርተን አልዳንም ስለዳንን እናፈራ ዘንድ ግድ ነው .....ኢየሱስን ከመከለል ከመሸፈን ተጠብቀን እኛ ከስመን የኢየሱስን መአዛ የምናወጣ የስሙን ክብር የምናወጣበት እኔ ሳይሆን እርሱ ብለን በቃልም በኑሮም እርሱን የምናሳይበት እንደ ዮሐንስ ....እኛ ቀለን ኢየሱስን ማክበድ እኛ አንሰን ኢየሱስን ማላቅ አሜን ይሁንልን ... ሌሎች ድምጾች ተከልክለው ይሄ ድምጽ ጮሆ ይውጣ .... አሜን እብደት የሚታገድበት ዘመን ይሁን በፊታችን ያለ ዘመን !!! 🙌🙌🙌🙌🙌❤️❤️❤️❤️አሜን እልፍ ያድርግህ እጅግ የምንወድህ ዶ/ር ማሙሻዬ አንተን የአንተ የሆነውን ሁሉ ጌታ ይባርክ ብዙ ጸጋ ይጨመርልህ❤️ 👏❤️ ወንድማችን ነብይ ዘኔም ተባረክልን ብዙልን ኑሩልን እንደ ዮሐንስ እርሱን በማሳየት እርሱን ክርስቶስን በማላቅ በማድመቅ ተባረኩ እንወዳችሗለን በጣም❤️❤️❤️❤️👏👏 ሁላችሁ ተባረኩልን👏❤️

    • @azadkaya7067
      @azadkaya7067 ปีที่แล้ว

      Goyta yesus abzihu ybarka tebarek n bereket kun.

  • @marthamule9997
    @marthamule9997 ปีที่แล้ว +9

    እግዛብሔረ አምላክ ዘመንህ ህይወት ይባረክ 🙏🙏አሜን

  • @salameskyes7240
    @salameskyes7240 ปีที่แล้ว +6

    አሜንንንንንንን ጌታ መንፈስ ቅዱስ ትኩረቴ አተ ብቻ ይሁን በዚህ ትምረት ህይወቴን ጨምቄ ህዲይ ህያረገኝ ነው በኢየሱስ ስም ጌታ በኔ ይታይ😢🙌ዶክተር ተባረክ አባቴ❤

  • @SirgutTamene
    @SirgutTamene 3 หลายเดือนก่อน

    ዶ/ር ማሙሻ ሁሌ ታስተምረናለህ ወደ ህይወት እንድንተረጉመው ጌታ ይርዳን አንተንግን ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ጌታ ፍሬህን ያሳይህ

  • @genethabdi2647
    @genethabdi2647 ปีที่แล้ว +2

    እግዚአብሄር ይባርክህ ! ተባረክ ዶ/ ር ማሙሻ . በረከታችን ነህ :: እናመሰግነናለን ስለ ቃሉ ::

  • @rabihcall4540
    @rabihcall4540 ปีที่แล้ว

    ጌታ ሆይ ልወቅህ እና ልኑርልኝ የቃልህን ብርሃን አብራልኝ አባት😭😭😭😭

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 ปีที่แล้ว +1

    ድንቅ ትምህርት ነው ጸጋ ይብዛልህ ዶክተር
    ራሴን አይቸበታለሁ ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ እድሜህን ያርዝምልን በሚያስፈልግህ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ይሙላልህ ።

  • @yabetsberhanuasfaw7232
    @yabetsberhanuasfaw7232 ปีที่แล้ว +3

    Geta abzito yibarkih Dr. Mamusha................Betam des mil timhirt new..........Geta ahunm abzito tsegawn yabzalik ..........ahunm bezu ersun enditasay ende john yirdak egziabher

  • @mesertkebede4115
    @mesertkebede4115 ปีที่แล้ว +3

    God bless you and your family Dr🙏

  • @merrytesfaye4831
    @merrytesfaye4831 9 หลายเดือนก่อน +1

    ጌታ ይባርካቹ🥰🥰

  • @AOCleumas
    @AOCleumas ปีที่แล้ว +3

    እግዚአብሔር ይባርክህ ፀጋውን ጥበቡን ይጨምርልህ!!!❤❤❤

  • @FantaziaBeautycenter1
    @FantaziaBeautycenter1 ปีที่แล้ว

    እፎይ ተመስገን እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል... እሰይ ሃሌ ሉያ እንዲህ እውነተኛ ወንጌል ያነበብኩትን በጆሮዬ መስማት ስለመሰለኝ እደለኛ ነን ዶ/ር ማሙሻ ፋንታ እንደ አንተ ያሉትን እውነተኞች ያብዛልን አሜን አሜን አሜን የተባረካችሁ ናችሁ ❤

  • @eyerus43enu
    @eyerus43enu ปีที่แล้ว

    Amen ጌታ እየሱስ ሆይ በሕይወታችን ልቀህ ክፍል ብልህ ቀድመህ ታይ .... ጌታ ይባርክህ Dr mamush thanks 🙏🙏❤

  • @jesuschrist15111
    @jesuschrist15111 ปีที่แล้ว +2

    ✞ክብር ለእግዚአብሔር አብ ክብር ለወልድ ክብር ለመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን አሜን።✟❤
    “ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
    - ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

  • @NiyatAsgodom
    @NiyatAsgodom 6 หลายเดือนก่อน

    wow what a wonderful teaching Glory to God.

  • @hanaweba1541
    @hanaweba1541 ปีที่แล้ว

    ዶር ማሙሻ ትምህርትህን የምሰማዉ ሁሌም እግዚአብሔርን ስለምታልቅ ንፁህ ወንጌል ስለምታስተምር ነዉ። ፀጋዉ ይብዛልህ ተባረክ

  • @zinashmamo9676
    @zinashmamo9676 ปีที่แล้ว

    አሜሜሜሜሜሜሜሜሜሜሜሜሜሜእልልልልልልልልልልልልልል አሜሜሜሜሜንንንንንንንንተባረኩ

  • @Aki-rl2wz
    @Aki-rl2wz ปีที่แล้ว +2

    Dr M you’re our blessing may the lord bless you. I have no words may the Lord used you more. ❤💙🙏🙏

  • @Nuhamin.953
    @Nuhamin.953 ปีที่แล้ว +1

    ማሙሻ ዘኔ ተባረኩልኝ እንወዳቹሀለን 🔥🔥😍🙏

  • @zinashmamo9676
    @zinashmamo9676 ปีที่แล้ว +1

    አሜንንንንንን ደግሜ ብሰማው ብሰማው የማይጠገብ መና በዚህ ክፊ ዘመን ተስፋን የሚሰጥ የሚያለመልም መና ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ይሔንን አሳራፊ ቃል የሰጠን።

  • @jiraataadhayesuus8617
    @jiraataadhayesuus8617 ปีที่แล้ว

    Ameeeeen ante Tay Iyesuus 😢😢😭😭🙏🙏🙏

  • @tensumamush9918
    @tensumamush9918 ปีที่แล้ว

    Amennn Amennn.dr mamusha tebarek betifu ayinachinin wede eyesus endinay endinikerb lemtadergun yeabata bariyawoch bemulu tebareku betifu

  • @ilubko8609
    @ilubko8609 ปีที่แล้ว

    I’m so happy to find this channel

  • @Newaccountbunnimeow
    @Newaccountbunnimeow ปีที่แล้ว

    Amen amen amen amen amen blessed

  • @eyesusgetanew7338
    @eyesusgetanew7338 ปีที่แล้ว

    Geta yebarekachehu ewnetegnawene netsuhe Wengele selemetzkerebuline. Kibere le EYSUSE yehune 🙏🙏🙏🌻🙏🌻🙏🌻🙏🌻🌻🙏🌻

  • @tsiontadesse5228
    @tsiontadesse5228 ปีที่แล้ว

    Your amazing Doctor mamusha

  • @mulukenmihretu8711
    @mulukenmihretu8711 ปีที่แล้ว +2

    ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርካችሁ 🙏🙏👏🖐🖐🖐❤️

  • @01Kiyu
    @01Kiyu ปีที่แล้ว +1

    ተባረኩ

  • @binievents9086
    @binievents9086 ปีที่แล้ว

    ዘመናቹ ይባረክ ተባረኩ

  • @bunikefila9423
    @bunikefila9423 ปีที่แล้ว

    አሜን አሜን ስም ከፍ ይበልልን ጌታ ሆይ !!!ጌታ ሆይ ከቃል ጋር የማወደድረው ነገር አይኑረኝ አምላኬ ሆይ !!!!መንፈስ ቅዱስ ነፍሴ ወዳ ተመሰግንሃለች ሁሌ !!! ወንድሜ ፓስተር ተባረክልኝ አንተም በኛ ጌታ በኢየሱስ ስም 🙏 29/01/2023

  • @RahbotNhzbey
    @RahbotNhzbey ปีที่แล้ว +1

    Egziabiher Amlak Abzto ybarkh pastor Mamusha.

  • @masreshalakew1962
    @masreshalakew1962 ปีที่แล้ว

    ዶክተር ማሙሻ እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @seni4086
    @seni4086 ปีที่แล้ว

    Ye zemene yohanes 🙏

  • @kali2839
    @kali2839 ปีที่แล้ว

    Thank you Dr. Mamusha

  • @selamawithaile6129
    @selamawithaile6129 ปีที่แล้ว

    ተባረክ !

  • @getahundebela53
    @getahundebela53 10 หลายเดือนก่อน

    Zemenachu ybarek

  • @desta5885
    @desta5885 ปีที่แล้ว

    ዘመንህ ይባረክ ተባረክ።

  • @Newaccountbunnimeow
    @Newaccountbunnimeow ปีที่แล้ว

    God bless you amazing

  • @tsehayegetachew4599
    @tsehayegetachew4599 ปีที่แล้ว

    አሜኝ አሜን እኔ እኔ ነኝ ያለ እግዚአብሔር ብቻ ሰጋ ለባሽ ራሱን ሲሰተዋዉቅ ያሳፍራል ተባረክ እዉነተኞ ታማኝ አገልጋይ።

  • @tewodrosabera4689
    @tewodrosabera4689 ปีที่แล้ว

    ፀጋ ይብዛላችሁ ።

  • @Ova-7311
    @Ova-7311 ปีที่แล้ว

    ዶር, ብጣም ድንቅ(amazing) ትምህርት ብርክ በል, ሃለሉያ.

  • @rabihcall4540
    @rabihcall4540 ปีที่แล้ว

    እግዚአብሔር በብዙ ይባርካች የቃሉን ብርሃን ያበራል እግዚአብሔር ይባረክ እንዴት እንደምቀናብር

  • @Samry-e13
    @Samry-e13 ปีที่แล้ว

    Adrashachu hit new

  • @daginetmarkos570
    @daginetmarkos570 ปีที่แล้ว

    oh Glory To Migty Gbu D/M

  • @rahwayirgalem8185
    @rahwayirgalem8185 ปีที่แล้ว

    God bless u for showing Jesus boldely in these last days!

  • @gezahegngessesse5112
    @gezahegngessesse5112 ปีที่แล้ว +1

    ጌታ ይባርካችሁ 🙏

  • @elisabeth.feleke2317
    @elisabeth.feleke2317 ปีที่แล้ว

    May God bless you

  • @yodittezaz1419
    @yodittezaz1419 8 หลายเดือนก่อน

    ተባረክ

  • @daginetmarkos570
    @daginetmarkos570 ปีที่แล้ว

    am so blss

  • @almazwoldemichael7915
    @almazwoldemichael7915 ปีที่แล้ว

    እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @erutsolomon3348
    @erutsolomon3348 ปีที่แล้ว

    Blesse you

  • @gelilaabisolom133
    @gelilaabisolom133 ปีที่แล้ว

    Glory to Lord 🙏🙏🙏 Dr mamush more more blessing

  • @habtid
    @habtid ปีที่แล้ว

    አገልጋይ መሆን እንደ ዮሐንስ መስበክም መሲሁን ጌታ ክርስቶስን:: ጌታ ይባርክህ ወ/ም ማሙሻ

  • @URIMAGAPE
    @URIMAGAPE 4 หลายเดือนก่อน

    እነሆ መንገዱን አስተካክሉ ጎዳናውን አቅኑ 😍 ንጉሱ መቷል

  • @lemlemghebremedhinweldeghi5205
    @lemlemghebremedhinweldeghi5205 ปีที่แล้ว

    Blessing brother Mamusha & all of brethren of Equip media family, I am growing by the Word of God, thanks again !!

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 ปีที่แล้ว +1

    መጥምቁ ዮሃንስ ስለ ጌታ ሲናገር የጫማውን ልሽከም የማይገባኝ ፣ እኔ ላንስ እሱ ሊልቅ ይገባል ሲል ዮሃንስ እንደዛ ካለ እኔ ምን ልበል እላለሁ ።

  • @selamugenetu9253
    @selamugenetu9253 ปีที่แล้ว

    እቀጥላለሁ

  • @Grace_ministry8
    @Grace_ministry8 ปีที่แล้ว

    1:04:23-1:06:23

  • @SirgutTamene
    @SirgutTamene 3 หลายเดือนก่อน

    በዛን ቀን ባልሰማውም ዛሬ ስሰማው ግን ተባርኬበታለው ልቤ ተነክቷል

  • @getayalewe1009
    @getayalewe1009 ปีที่แล้ว

    Dr. Mamusha forgot about the John Baptist theory he has gone, now you are the John the Baptist, it is your turn to be the voice of God, and you are the great voice of God. To learn under the feet of people is not only to be lucky but also to be blessed. Mary sat at the Lord's feet and heard the voice of God, but Martha complained About Mary to the Lord.
    King David is the voice of the people. But King Saul is the noises of the nations.
    King David was chosen by God to be the leader of Israel, but King Saul was chosen by the will of the Israelites.
    In a peaceful country where there is a democracy, the people vote to elect a leader by giving their Voice.
    But in a country where there is no peace People stir up violence riot and disturb with their noisy words.
    The dead will rise from spiritual death when they hear the voice of Jesus Christ, the Son of God. But these spiritually dead people may be able to listen to the voices of others, but the voices that the dead hear apart from the Lord's voice are not real voices, It's a noise so spiritually dead people never raise from the dead, Therefore, they will disappear forever. Lazarus who was in the grave heard the voice of the Lord and rose from the dead, but he did not listen to the voice of the angel and the people.
    There are spiritual coffins operating these days. Many of them want to hear the voices of angels or saints, but they cannot save them. Only the voice of the Son of God saves, all else is noise.

  • @Dani_habeshawi_27
    @Dani_habeshawi_27 ปีที่แล้ว

    ለትውልድ መልስ ነህ

  • @yodittezaz1419
    @yodittezaz1419 8 หลายเดือนก่อน

    ተባረክ

  • @krieesten
    @krieesten ปีที่แล้ว

    1:04:23-1:06:23