ขนาดวิดีโอ: 1280 X 720853 X 480640 X 360
แสดงแผงควบคุมโปรแกรมเล่น
เล่นอัตโนมัติ
เล่นใหม่
ደግሜ ደግሜ ብሰማ የማይሰለቸኝ ግጥም ''ደስ ይላል መስከረም'' አያ ሙሌ ነብስህን ይማር
አያ ሙሌ የነብስ ምግብ መጋቢ ጻድቅ ባለቅኔ ነበር :: ነብስህን በአጸደ ግነት ያሳርፍ ጌታ !
ዋው ደስ የሚል ግጥም እውነትም ደስስስ ይላል መስከረም ትዝታዬን ቀሰቀሳቹብኝ ሸገሮች
ወይኔ ሙሌ
በጣም ምርጥ ፤❤ እስቲ ደግሞ እራሱ አያ ሙሌ ያነበባቸው የራሱን ግጥሞች post አርጉልን 🙏
ደስ ይላል መስከረም!ገጣሚ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ - አያ ሙሌወዳጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ እነሆ ክረምቱ አለፈ፣ ዝናቡም አልፎ ሔደአበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፣ የዜማም ጊዜ ደረሰየቀሪዮም ቃል በምድራችን ተሰማ፣ በለሱ ጎመራወይኖችም አበቡ፣ መአዛቸውንም ሰጡወዳጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ እንዲል ንጉስ ሰሎሞንእንዲህ እንዳሁኑ መስከረም የጠባ ሰሞንለብልሀቱ፣ ዉሃ ሙላቱ ሲጎድልወቅት ስቆ፣ አዝመራ አሽቶ ሲያደላድልእዮሀ አበባዬ፣ መስከረም ጠባዬ እያሉ እንደ እንቦሳ እየቦረቁ፣ ወገል እያረቁየተጣላ እያስታረቁበገበሬ ሀውዛ ቱፍታ እየመረቁግንፍልታው እፍታው መረቁበሸንበቆ ቅልጥም ዜማ እንደ ከራማ ጣት እስኪያስቆረጥም፣ በዋሽንት እያስረቀረቁወዳጄ ሆያ ተነሺ፣ ዉበቴ ሆይ ነይ ሲሉደስ ይላል መስከረም! እንደ ቢራ ቢሮ አበባ ለአበባዐደይ እንቡር እንቡር በፍቅር ለመክረም አዎ ደስ ይላል መስከረም!ተምሮ መታረምወዶ ተዋህዶ፣ በሳቅ በጫወታበለመለመው መስክ፣ በአንድ ለመረምረምደስ ይላል መስከረም!ከንፈር ሽምያ አፍላ ፍቅር፣ በልብ ማህተም እስኪታተምእሙጷ፣ በአዴይ፣ በፀደይ፣ በከንፈር መፈራረምደስ ይላል መስከረም!የሐምሌን ዶፍ፣ የነሀሴን ዉሽንፍር ሸኝቶየአንጀትን በአንጀት ለመግለፅክራርን አንቺ ሆዬ ለኔ፣ የልቤ ምስለኔ፣ እያሉ ቃኝቶጥጃና ወይፈን፣ ሠደድ ሜዳ አሰማርቶማማ ሥር ተኝቶ በእምነት በፍቅር፣ በተስፋ ተቆራኝቶመሀርን እያሰቡ፣ በስሜት እየሰበሰቡበአጭር ታጥቀው እየከሰቡሠንጋ ለሠርግ፣ ለሚንዜ ጫጉላ እየሳቡሲላፉ፣ ሲላላፉደስ ይላል መስከረም!ብራ ነዋ! አዎ፣ እንግዲህ ብራ ነው እንጂ ብራጎማን ደህና ሰንብት፣ እንግዲህ ደርሶ ሽንብራተመስገን ነው እንጂ ቤዛ አለምእንግዲህስ እንኳን ክፉ፣ የክፉ ስሙ የለምግንስ ባይሆን፣ ያላረሰ ያላደፋረሰአረም ያልነቀለ፣ ያልተቀላቀለቅንድም ያበቀለ፣ በአንድ አብሮ ላይበላግዝት ነው ያለብን፣ ከአባት ከቅድመ አያት እስከ ላሊበላጠብቆ ያረሰ ሰው፣ እርፍ የነቀነቀወፍጮው እያገሳ፣ መስከረም ዘለቀአዎ! ያላረሰ ጎበዝ፣ እርፍ ያልነቀነቀበሐምሌ መባቻ፣ ተጣጥፎ ወደቀ፣ እያሉ እየዘፈኑሁሉም እንደየፈኑ፣ በየጥጉ በየጉድባው እያፈነፈኑየኔ ቢጤዎችም የበይ ተመልካች ሆነው ሲድፈነፈኑእዮሃ! ሞፈር ዉሃ፣ እዮሃ! አንዱ አባይ በረኅአንዱ ጓለሞታ ጭን፣ በለኝ ልበልኅ ምን አለሓደስ ይላል መስከረም!
በግርሻ'ጣይ ሰርዶ ነቅሎ፣ በሚያዚያ ንሽ ተርመጥምጦ በግንቦት ሐሩር ተቀቅሎ በፀሐይ አብስሎ፣ በዝናብ አብቅሎከወዳጅ ከዘመድ ተቀላቅሎ ባዝራ ከአህያ አዳቅሎ በባለ በርሸት ሽልም በቅሎ፣ ተፈናጦ አብሮ ገስግሶ ጅራፍ ግርፊያ ሆያ ሆዬ ፣ ቡሄ በሉ ተጫውቶ፣ ኪዳነ ምሕረትን አንግሶደግሞ በወሩ ለአስተሮዬው፣ ግሼን ማሪያም እመአርያም ደጀሰላም ደርሶ ለመሳለም"እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ ዐደይ ለምለም ለኔ እንዳንቺ የለም"እያሉ ድልቂያ ከጀንበር መፍለቂያ እስከ ጀንበር መጥለቂያአለላ ነቅሎ በሀር ሙዳይጀግና ሰውገዳይ፣ አካል እንጉዳይእያሉ ሲያንጎራጉሩደስ ይላል መስከረም!ቡቃያው ጣል ከንበል ሲል ሽሩባዋ ወርዶ እንዲያ ሲዘናፈል ልቤ እንደበቆሎ ያድራል ሲፈለፈልበቀጭን ተሰርታ፣ ስትል ዘንከት ዘንከት ጃሎ ሲል ሊያነጋ፣ አገር በመለከት ለመስቀል ጠንስሶ በማድጋ ገንቦ፣ ለእንግዳ ቀንሶ በሞቴ አፈር ስሆን፣ እያለ ሲያጋፍር ጥርሰ እንጎቻ አስፍቶ፣ አሞጭ በመሰለው እርጎ ፍርፍር እንኳን ሳቅ ጨዋታው፣ ድብድቡ ልፊያው ድገሙኝ ያሰኛል፣ ሰፈፍ የለሽ መውደድ መደዱ በዜማ ሲቆረቆር ኩርፊያውደስ ይላል መስከረም !የሽንብራ እሸት እየጠረጠሩ የልጅነት ሚዜ 'ኧረ አይዋ ክንዴ' እያሉ እየጠሩ አብሮ ወፍ ጥበቃ፣ ማማ ላይ ተሰቅሎ ካፊያውን በገሳ፣ በአንድ ተጠልሎእሳት አቀጣጥሎ፣ በቆሎ ጠባብሶአየሁ አላየሁም፣ ሰማሁ አልሰማሁም፣ በላልቶ አፍ አብሶ ለስለሶ አስፈትሎ፣ የ'ናት ኩታ ለብሶ ላዋቂ ተልኮ፣ ለልጅ ተጎናብሶ ደስ ይላል መስከረም!እንደ ቢራ ቢሮ አበባ ለአበባ፣ ዐደይ እንቡር እንቡር በፍቅር ለመክረምወፉ ከየጎጆው፣ እስከ መናጆው ንቡ ከየቀፎው፣ መረባ ከነ እርፎው በዐደይ ለምለም ህብር፣ ለመስከረም ክብር ቅዱስ! ቅዱስ! ቅዱስ!የዓመት አሥራት ሊያፈስ ሊያስገባለት ግብር ፣በዝማሬ ሲያብር አንጄት ሲበረብር ደስ ይላል መስከረም!ወዶ ተዋህዶ፣ ያንጀት ተፈቃቅዶ ባንድ አብሮ ለመክረም ለቅኔ ዘረፋው፣ ጠፈፍ ሲል ፈፋው የቆሎ ተማሪ፣ ያ ተመራማሪ የወላዲት አምላክ፣ የድንግል አዝማሪ ያ ደበሎ ለባሽበእግዚትነ ማሪያም እባካቹህ እባሽ እባካቹህ ቁራሽእያለ ሲለምን ከጥንቅሹ ቅንጥሽ፣ ማሩቴ ባይሰጠው አይቀር መደንገጡ፣ አራሽ አባ ወራሽማብላት የሰለጠው፣ የማይለወጠውበዐይኑ እየመዘነ፣ በልቡ እማይመርጠው ገሩ ባላገሩ፣ ያ ባለሞፈሩ፣ ያ ባለዘገሩ በሞቴ ነው ቋንቋው፣ ስሞት ነው ነገሩደስ ይላል መስከረም!ወዶ ተወሕዶ፣ ያንጀት ተፈቃቅዶ አንድ ልብ አቅዶአንድ ላይ ለመክረምደስ ይላል መስከረም!
ጥቅምትና ኅዳር፣ ቢያዋውል ምንጭ ዳር ታኅሳስና ጥር፣ ዐውድማ አስለቅልቆ፣ ጥሪትም ቢያስቋጥርየካቲት መጋቢት፣ መኸር አስከትቶ፣ ቢያበስል እንደ ዐቃቢትሚያዚያና ግንቦቱ፣ ተርቲበኛው ቀርቦ፣ ወርዶ ራከቦቱየላም ልጅ በዋንጫ፣ ቢቀርብ ሥልባቦቱሰኔ ሐምሌ ነሐሴ፣ እንደ ቄስ ምናሴእያረበረበ፣ ደግሞ እየወረበሰማዩ በመብረቅ ታርሶ ሲስረቀረቅከራሱ እስኪታረቅሁሉም እንደ ግብሩሁሉም እንደ ሙያውአሥራ ሁለቱም ወር እዮሃ አበባዬ መስከረም ሲጠባያኔ ነው ገበያውያኔ ነው መታያውያኔ ነው ማባያውሁሉም እንደ ስራው፣ በጊዜ እንደራሴ፣ የማር መሬት ርስት፣ ለወራትስር ሚዜ ስልጣን የሚመራውግንቦት በጣይ ነዶ፣ ሞቆት ቢንጠራራ ሐምሌ በዶፍ ዝናብ ዉርጅብኝ ቢያቅራራመቻል እንደ ሰጠው፣ ሁሉም እንደ አቅሙ አድሮአደይ ሲፈነዳ፣ እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ ብሎ ተደርድሮያነሳል ዋንጫዉን፣ ኪዳን መጠጫዉንደግሞ ለዘንድሮ፣ ከርሞ መታጫዉንእያጫረ ተስፋ፣ ያልማል መጪዉንደስ ይላል መስከረም!ተምሮ መታረምወዶ ተዋህዶ፣ በሳቅ በጫወታበለምለም መስክ ላይ፣ በአንድ አብሮ ለመክረምጥበብ ሊያጎርስ ፈትፍቶ፣ ትምህርት ቤት አስከፍቶኮፋዳው ደብተር መያዣው ተሰፍቶአንጀት አስሮ፣ ደረት ነፍቶ ጥሮ ግሮ፣ ደክሞ ለፍቶ የከርሞ ሰው ለመባል፣ አውቆ ካዋቂ ጎን ለመሰለፍለመስዋዕትነት ራስን አጭቶ፣ ለቀሪው ለማሳለፍእርሳስ ጠርቦ፣ ኮቢ ወድሮወንድሜ ያዕቆብ ወንድሜ ያዕቆብ ተኛህ ሆይ? ተኛህ ሆይ? ደውል ተደወለ ደውል ተደወለተነሳ ተነሳ!ብሎ ተንደርድሮእሱም እንዳባቱ፣ ጠብደል ያለ ባቱእሷም እንደ እናቷ፣ ድርብ መቀነቷህልማቸዉን በደመነብስ እያማተሩወደ ትምህርት ቤት ሲገሰገሱአማርኛው በኛው፣ በነኛ ደግሞ እንደዚያመስተዋድድ መስተጋብር እያሉ ግስ ሲገሱደስ ይላል መስከረም!ሀ ግዕዝ ሁ ካብዕ ሂ ሳልስ ሃ ራብዕልጅ እንዳይራብሄ ሀምስ ህ ሳድስ ሆ ሳብዕያለ አንድ ሀሳብእያሉ ተምሮ ደምሮ ቀንሶ፣ ራስን እንደ መቻልምን አለና ምን ያስመቻልሳለ ባልደራስ፣ አምባው የአምባ ራስቆፍጣናው ወታደር፣ ዘበናይ ዘብ ይደርዓይኑን ከጠላቱ፣ ልቡን ካገሩ ልጅ ያገር ሰው መንቲያ፣ ያው እንደ ጡዋቱጣቱ ከቃታው ላይ የመይሳው ወንድም፣ የነ ደጃች በላይየነ ራስ አሉላ፣ የሀብተ ጊዮርጊስ እምዬ አባመላ ያ ያገር ልጅ ባላ፣ ያ ያገር ልጅ ካስማዋ ብቻ! ዋ ብቻ! ባገር በድንበሩ በወገኖቹ ላይ አንድ፣ አንድ ብቻ ይስማ!ያኔ እሱን አያርገኝ ደፋር ወሮበላያኔማ ምን አለልቡን ቅዳሜ ሹም፣ ነብሱን ለቅበላ።አሁን ይሄን ግዜ፣ በየምሽጉ ስርትጥቅና ዝናሩን፣ እየፈታ ሲያስርእኛ ተደላድለን፣ የሱንም ታድለንበሱ ተመክተን ስናድር ተኝተንየኛውስ የኛው ነው፣ የሱንም የሱንም ተክተን እንዲህ ስንዝናና፣ እንደምን ይኮራየጦር ሜዳው ፋኖ፣ ያ የኔ ዘምናና!ገጣሚ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ - አያ ሙሌ
Mirtu bale kine aya mule RIP, thanks alex
አበጀህ፥ ወንድሜ፤ ዜጋውን/ወንድሙን የሚያከብርና ለስኬታቸው እውቅና የሚሰጥ ሃገሩን የሚያከብርና ለሃገሩ እመርታዎች እውቅና የሚሰጥ ነው። ቡሩክ ሁን።
ድርሰት "ሙሉጌታ ተስፋዬ"ተራኪ "አለማየው ታደሰ" ብላቹ ነው ፖስት ማድረግ ያለባቹ።
ደግሜ ደግሜ ብሰማ የማይሰለቸኝ ግጥም ''ደስ ይላል መስከረም'' አያ ሙሌ ነብስህን ይማር
አያ ሙሌ የነብስ ምግብ መጋቢ ጻድቅ ባለቅኔ ነበር :: ነብስህን በአጸደ ግነት ያሳርፍ ጌታ !
ዋው ደስ የሚል ግጥም
እውነትም ደስስስ ይላል መስከረም ትዝታዬን ቀሰቀሳቹብኝ ሸገሮች
ወይኔ ሙሌ
በጣም ምርጥ ፤❤ እስቲ ደግሞ እራሱ አያ ሙሌ ያነበባቸው የራሱን ግጥሞች post አርጉልን 🙏
ደስ ይላል መስከረም!
ገጣሚ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ - አያ ሙሌ
ወዳጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ
እነሆ ክረምቱ አለፈ፣ ዝናቡም አልፎ ሔደ
አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፣ የዜማም ጊዜ ደረሰ
የቀሪዮም ቃል በምድራችን ተሰማ፣ በለሱ ጎመራ
ወይኖችም አበቡ፣ መአዛቸውንም ሰጡ
ወዳጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ
እንዲል ንጉስ ሰሎሞን
እንዲህ እንዳሁኑ መስከረም የጠባ ሰሞን
ለብልሀቱ፣ ዉሃ ሙላቱ ሲጎድል
ወቅት ስቆ፣ አዝመራ አሽቶ ሲያደላድል
እዮሀ አበባዬ፣ መስከረም ጠባዬ እያሉ
እንደ እንቦሳ እየቦረቁ፣ ወገል እያረቁ
የተጣላ እያስታረቁ
በገበሬ ሀውዛ ቱፍታ እየመረቁ
ግንፍልታው እፍታው መረቁ
በሸንበቆ ቅልጥም ዜማ
እንደ ከራማ ጣት እስኪያስቆረጥም፣ በዋሽንት እያስረቀረቁ
ወዳጄ ሆያ ተነሺ፣ ዉበቴ ሆይ ነይ ሲሉ
ደስ ይላል መስከረም!
እንደ ቢራ ቢሮ አበባ ለአበባ
ዐደይ እንቡር እንቡር በፍቅር ለመክረም
አዎ ደስ ይላል መስከረም!
ተምሮ መታረም
ወዶ ተዋህዶ፣ በሳቅ በጫወታ
በለመለመው መስክ፣ በአንድ ለመረምረም
ደስ ይላል መስከረም!
ከንፈር ሽምያ አፍላ ፍቅር፣ በልብ ማህተም እስኪታተም
እሙጷ፣ በአዴይ፣ በፀደይ፣ በከንፈር መፈራረም
ደስ ይላል መስከረም!
የሐምሌን ዶፍ፣ የነሀሴን ዉሽንፍር ሸኝቶ
የአንጀትን በአንጀት ለመግለፅ
ክራርን አንቺ ሆዬ ለኔ፣ የልቤ ምስለኔ፣ እያሉ ቃኝቶ
ጥጃና ወይፈን፣ ሠደድ ሜዳ አሰማርቶ
ማማ ሥር ተኝቶ
በእምነት በፍቅር፣ በተስፋ ተቆራኝቶ
መሀርን እያሰቡ፣ በስሜት እየሰበሰቡ
በአጭር ታጥቀው እየከሰቡ
ሠንጋ ለሠርግ፣ ለሚንዜ ጫጉላ እየሳቡ
ሲላፉ፣ ሲላላፉ
ደስ ይላል መስከረም!
ብራ ነዋ!
አዎ፣ እንግዲህ ብራ ነው እንጂ ብራ
ጎማን ደህና ሰንብት፣ እንግዲህ ደርሶ ሽንብራ
ተመስገን ነው እንጂ ቤዛ አለም
እንግዲህስ እንኳን ክፉ፣ የክፉ ስሙ የለም
ግንስ ባይሆን፣ ያላረሰ ያላደፋረሰ
አረም ያልነቀለ፣ ያልተቀላቀለ
ቅንድም ያበቀለ፣ በአንድ አብሮ ላይበላ
ግዝት ነው ያለብን፣ ከአባት ከቅድመ አያት እስከ ላሊበላ
ጠብቆ ያረሰ ሰው፣ እርፍ የነቀነቀ
ወፍጮው እያገሳ፣ መስከረም ዘለቀ
አዎ! ያላረሰ ጎበዝ፣ እርፍ ያልነቀነቀ
በሐምሌ መባቻ፣ ተጣጥፎ ወደቀ፣ እያሉ እየዘፈኑ
ሁሉም እንደየፈኑ፣ በየጥጉ በየጉድባው እያፈነፈኑ
የኔ ቢጤዎችም የበይ ተመልካች ሆነው ሲድፈነፈኑ
እዮሃ! ሞፈር ዉሃ፣ እዮሃ! አንዱ አባይ በረኅ
አንዱ ጓለሞታ ጭን፣ በለኝ ልበልኅ ምን አለሓ
ደስ ይላል መስከረም!
በግርሻ'ጣይ ሰርዶ ነቅሎ፣ በሚያዚያ ንሽ ተርመጥምጦ
በግንቦት ሐሩር ተቀቅሎ
በፀሐይ አብስሎ፣ በዝናብ አብቅሎ
ከወዳጅ ከዘመድ ተቀላቅሎ
ባዝራ ከአህያ አዳቅሎ
በባለ በርሸት ሽልም በቅሎ፣ ተፈናጦ አብሮ ገስግሶ
ጅራፍ ግርፊያ ሆያ ሆዬ ፣ ቡሄ በሉ ተጫውቶ፣ ኪዳነ ምሕረትን አንግሶ
ደግሞ በወሩ ለአስተሮዬው፣ ግሼን ማሪያም እመአርያም
ደጀሰላም ደርሶ ለመሳለም
"እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ
ዐደይ ለምለም ለኔ እንዳንቺ የለም"
እያሉ ድልቂያ
ከጀንበር መፍለቂያ እስከ ጀንበር መጥለቂያ
አለላ ነቅሎ በሀር ሙዳይ
ጀግና ሰውገዳይ፣ አካል እንጉዳይ
እያሉ ሲያንጎራጉሩ
ደስ ይላል መስከረም!
ቡቃያው ጣል ከንበል ሲል
ሽሩባዋ ወርዶ እንዲያ ሲዘናፈል
ልቤ እንደበቆሎ ያድራል ሲፈለፈል
በቀጭን ተሰርታ፣ ስትል ዘንከት ዘንከት
ጃሎ ሲል ሊያነጋ፣ አገር በመለከት
ለመስቀል ጠንስሶ
በማድጋ ገንቦ፣ ለእንግዳ ቀንሶ
በሞቴ አፈር ስሆን፣ እያለ ሲያጋፍር
ጥርሰ እንጎቻ አስፍቶ፣ አሞጭ በመሰለው እርጎ ፍርፍር
እንኳን ሳቅ ጨዋታው፣ ድብድቡ ልፊያው
ድገሙኝ ያሰኛል፣ ሰፈፍ የለሽ መውደድ
መደዱ በዜማ ሲቆረቆር ኩርፊያው
ደስ ይላል መስከረም !
የሽንብራ እሸት እየጠረጠሩ
የልጅነት ሚዜ 'ኧረ አይዋ ክንዴ' እያሉ እየጠሩ
አብሮ ወፍ ጥበቃ፣ ማማ ላይ ተሰቅሎ
ካፊያውን በገሳ፣ በአንድ ተጠልሎ
እሳት አቀጣጥሎ፣ በቆሎ ጠባብሶ
አየሁ አላየሁም፣ ሰማሁ አልሰማሁም፣ በላልቶ አፍ አብሶ
ለስለሶ አስፈትሎ፣ የ'ናት ኩታ ለብሶ
ላዋቂ ተልኮ፣ ለልጅ ተጎናብሶ
ደስ ይላል መስከረም!
እንደ ቢራ ቢሮ አበባ ለአበባ፣ ዐደይ እንቡር እንቡር
በፍቅር ለመክረም
ወፉ ከየጎጆው፣ እስከ መናጆው
ንቡ ከየቀፎው፣ መረባ ከነ እርፎው
በዐደይ ለምለም ህብር፣ ለመስከረም ክብር
ቅዱስ! ቅዱስ! ቅዱስ!
የዓመት አሥራት ሊያፈስ
ሊያስገባለት ግብር ፣በዝማሬ ሲያብር
አንጄት ሲበረብር
ደስ ይላል መስከረም!
ወዶ ተዋህዶ፣ ያንጀት ተፈቃቅዶ
ባንድ አብሮ ለመክረም
ለቅኔ ዘረፋው፣ ጠፈፍ ሲል ፈፋው
የቆሎ ተማሪ፣ ያ ተመራማሪ
የወላዲት አምላክ፣ የድንግል አዝማሪ
ያ ደበሎ ለባሽ
በእግዚትነ ማሪያም እባካቹህ እባሽ እባካቹህ ቁራሽ
እያለ ሲለምን
ከጥንቅሹ ቅንጥሽ፣ ማሩቴ ባይሰጠው
አይቀር መደንገጡ፣ አራሽ አባ ወራሽ
ማብላት የሰለጠው፣ የማይለወጠው
በዐይኑ እየመዘነ፣ በልቡ እማይመርጠው
ገሩ ባላገሩ፣ ያ ባለሞፈሩ፣ ያ ባለዘገሩ
በሞቴ ነው ቋንቋው፣ ስሞት ነው ነገሩ
ደስ ይላል መስከረም!
ወዶ ተወሕዶ፣ ያንጀት ተፈቃቅዶ
አንድ ልብ አቅዶ
አንድ ላይ ለመክረም
ደስ ይላል መስከረም!
ጥቅምትና ኅዳር፣ ቢያዋውል ምንጭ ዳር
ታኅሳስና ጥር፣ ዐውድማ አስለቅልቆ፣ ጥሪትም ቢያስቋጥር
የካቲት መጋቢት፣ መኸር አስከትቶ፣ ቢያበስል እንደ ዐቃቢት
ሚያዚያና ግንቦቱ፣ ተርቲበኛው ቀርቦ፣ ወርዶ ራከቦቱ
የላም ልጅ በዋንጫ፣ ቢቀርብ ሥልባቦቱ
ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ፣ እንደ ቄስ ምናሴ
እያረበረበ፣ ደግሞ እየወረበ
ሰማዩ በመብረቅ ታርሶ ሲስረቀረቅ
ከራሱ እስኪታረቅ
ሁሉም እንደ ግብሩ
ሁሉም እንደ ሙያው
አሥራ ሁለቱም ወር
እዮሃ አበባዬ መስከረም ሲጠባ
ያኔ ነው ገበያው
ያኔ ነው መታያው
ያኔ ነው ማባያው
ሁሉም እንደ ስራው፣ በጊዜ እንደራሴ፣
የማር መሬት ርስት፣ ለወራትስር ሚዜ ስልጣን የሚመራው
ግንቦት በጣይ ነዶ፣ ሞቆት ቢንጠራራ
ሐምሌ በዶፍ ዝናብ ዉርጅብኝ ቢያቅራራ
መቻል እንደ ሰጠው፣ ሁሉም እንደ አቅሙ አድሮ
አደይ ሲፈነዳ፣ እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ ብሎ ተደርድሮ
ያነሳል ዋንጫዉን፣ ኪዳን መጠጫዉን
ደግሞ ለዘንድሮ፣ ከርሞ መታጫዉን
እያጫረ ተስፋ፣ ያልማል መጪዉን
ደስ ይላል መስከረም!
ተምሮ መታረም
ወዶ ተዋህዶ፣ በሳቅ በጫወታ
በለምለም መስክ ላይ፣ በአንድ አብሮ ለመክረም
ጥበብ ሊያጎርስ ፈትፍቶ፣ ትምህርት ቤት አስከፍቶ
ኮፋዳው ደብተር መያዣው ተሰፍቶ
አንጀት አስሮ፣ ደረት ነፍቶ
ጥሮ ግሮ፣ ደክሞ ለፍቶ
የከርሞ ሰው ለመባል፣ አውቆ ካዋቂ ጎን ለመሰለፍ
ለመስዋዕትነት ራስን አጭቶ፣ ለቀሪው ለማሳለፍ
እርሳስ ጠርቦ፣ ኮቢ ወድሮ
ወንድሜ ያዕቆብ ወንድሜ ያዕቆብ
ተኛህ ሆይ? ተኛህ ሆይ?
ደውል ተደወለ ደውል ተደወለ
ተነሳ ተነሳ!
ብሎ ተንደርድሮ
እሱም እንዳባቱ፣ ጠብደል ያለ ባቱ
እሷም እንደ እናቷ፣ ድርብ መቀነቷ
ህልማቸዉን በደመነብስ እያማተሩ
ወደ ትምህርት ቤት ሲገሰገሱ
አማርኛው በኛው፣ በነኛ ደግሞ እንደዚያ
መስተዋድድ መስተጋብር እያሉ ግስ ሲገሱ
ደስ ይላል መስከረም!
ሀ ግዕዝ ሁ ካብዕ ሂ ሳልስ ሃ ራብዕ
ልጅ እንዳይራብ
ሄ ሀምስ ህ ሳድስ ሆ ሳብዕ
ያለ አንድ ሀሳብ
እያሉ ተምሮ ደምሮ ቀንሶ፣ ራስን እንደ መቻል
ምን አለና ምን ያስመቻል
ሳለ ባልደራስ፣ አምባው የአምባ ራስ
ቆፍጣናው ወታደር፣ ዘበናይ ዘብ ይደር
ዓይኑን ከጠላቱ፣ ልቡን ካገሩ ልጅ
ያገር ሰው መንቲያ፣ ያው እንደ ጡዋቱ
ጣቱ ከቃታው ላይ
የመይሳው ወንድም፣ የነ ደጃች በላይ
የነ ራስ አሉላ፣ የሀብተ ጊዮርጊስ እምዬ አባመላ
ያ ያገር ልጅ ባላ፣ ያ ያገር ልጅ ካስማ
ዋ ብቻ! ዋ ብቻ!
ባገር በድንበሩ በወገኖቹ ላይ አንድ፣ አንድ ብቻ ይስማ!
ያኔ እሱን አያርገኝ ደፋር ወሮበላ
ያኔማ ምን አለ
ልቡን ቅዳሜ ሹም፣ ነብሱን ለቅበላ።
አሁን ይሄን ግዜ፣ በየምሽጉ ስር
ትጥቅና ዝናሩን፣ እየፈታ ሲያስር
እኛ ተደላድለን፣ የሱንም ታድለን
በሱ ተመክተን ስናድር ተኝተን
የኛውስ የኛው ነው፣ የሱንም የሱንም ተክተን
እንዲህ ስንዝናና፣ እንደምን ይኮራ
የጦር ሜዳው ፋኖ፣ ያ የኔ ዘምናና!
ገጣሚ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ - አያ ሙሌ
Mirtu bale kine aya mule RIP, thanks alex
አበጀህ፥ ወንድሜ፤ ዜጋውን/ወንድሙን የሚያከብርና ለስኬታቸው እውቅና የሚሰጥ ሃገሩን የሚያከብርና ለሃገሩ እመርታዎች እውቅና የሚሰጥ ነው። ቡሩክ ሁን።
ድርሰት "ሙሉጌታ ተስፋዬ"
ተራኪ "አለማየው ታደሰ" ብላቹ ነው ፖስት ማድረግ ያለባቹ።