"እኔ ነኝ!" --- አርሴማ ደርቤ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 30 ต.ค. 2024

ความคิดเห็น • 1

  • @Sola_mezmur
    @Sola_mezmur 5 หลายเดือนก่อน +2

    📜ሰባቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል "እኔ ...ነኝ" ያላቸው ቦታዎች
    1. የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ
    “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።”
    ዮሐንስ 6፥35
    2. እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ
    “ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”
    ዮሐንስ 8፥12
    3. እኔ የበጎች በር ነኝ
    “ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።”
    ዮሐንስ 10፥7
    4. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
    “መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”
    ዮሐንስ 10፥11
    5. ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ
    “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤”
    ዮሐንስ 11፥25
    6. እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ
    “ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
    ዮሐንስ 14፥6
    7. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ
    “እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።”
    ዮሐንስ 15፥1