Fried Chicken Burger የዶሮ በርገር
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 7 ก.พ. 2025
- ፍራይድ ቺክን በርገር
የዶሮ በርገሩን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ የግብዓት ዓይነት እና የማጣፈጫ ቅመሞች ዝርዝር እና መጠን
ይህ 6 በርገሮችን ለማዘጋጀት የሚረዳችሁ ነው ነገር ግን ብዙ ማዘጀት ከፈለጋችሁ የግብዓት መጠኖቹን ከፍ ማድረግ ይኖርባቹሃል
2 ስላሽ የተከተፈ የዶሮ መላላጫ
ዶሮው ቆንጆ ጠዓም እንዲኖረው ላዩ ላይ የሚገኘውን ተጨማሪ ስብ ማውጣት እንዳትዘነጉ
ዶሮውን ቀምሞ ለማቆየት የሚረዳንን ስልስ ለማዘጋጀት
1 ኩባያ እርጎ
ቅመም በቡና ማንኪያ ልኬት
1 ፓፕሪካ
1 ሮዝሜሪ
1 ጥቁር ቁንዶ በርበሬ
1 የነጭ ሽንኩርት ዱቄት
1 ሚጥሚጣ (ሚጥሚጣ የበለጠ ቃጠል የሚያደርግ ጠዓም ከፈለጋችሁ ብቻ አስገቡት)
1 ጨው
ጨምራችሁ በደንብ ትቀላቅሉት እና ዶሮውን አስገብታችሁ በደንብ ለውሳችሁት በላስቲክ ወይም በሰሃን ሸፍናችሁ ማቀዝቀዣ ውስጥ ለአንድ ሰዓት እና ከዛ በላይ ማቆየት
ዶሮውን የምትሸፍኑበትን ዴቄት ለማዘጋጀት
2 የሾርባ ማንኪያ ፉርኖ ዱቄት
1 የሾርባ ማንኪያ የበቆሎ ዱቄት
የበቆሎ ዱቄቱ ዶሮው የበለጠ ቃ ብሎ እንዲበስል ፣ ቆንጆ ወርቃማ ቀለም እንዲይዝ እና እንደ ብስኩት ከሽ እንዲል ያግዘዋል
ቅመም በቡና ማንኪያ ልኬት
1 ፓፕሪካ ፣ 1 ሮዝሜሪ ፣ 1 ጥቁር ቁንዶ በርበሬ ፣1 የነጭ ሽንኩርት ዱቄት ፣ 1 ሚጥሚጣ እና 1 ጨው
አበሳሰል
ዘይት በ180ዲግሪ ሴንቲግሬድ ታግሉና ወርቃማ ይዘት እስኪይዝ ድረስ ትጠብሱበታላችሁ ከ10-15 ደቂቃ ሊፈጅባችሁ ይችላል
ማባያ ስልስ
ማዮኔዝ
ኬችአፕ
ዳጣ
የስልሶች ድብልቅ
ማባያ
ድንች ጥብስ
የስኳር ድንች ጥብስ
ሰላጣ
መለኛ እንኳን በሰላም መጣክ😊
በውጩ አለም ሼፍ ዩቱበሮች ብዙ ቪዩ ና ብዙ ሰብስክራይብ አላቸው የኛ የኢትዮጵያ ግን ዘርንና ሀይማኖትን የሚሳደቡት ናቸው ቪዩ ና ሰብስክራይብ ያላቸው😏
አዴኛነክ👍👍👍👍👍
እጅህ ይባረክ የምፈልገው🙏👍