Disallowed Expenses & loss carried back (ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎች እና ኪሳራን ወደ ኃላ ማሸጋገር) ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ውሎች

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 12 มิ.ย. 2024
  • ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ውሎች Disallowed Expenses & loss carried back (ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎች ኪሳራን ወደ ኃላ ማሸጋገር) ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ውሎች
    ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ውል ማለት ስራው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በ12 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ከሚገመት በስተቀር (የማምረት፣ የመትከል /የግንባታ ስራ እና ተያያዥ አገልግሎቶች)
    በየግብር አመቱ የተጠናቀቀውን መቶኛ መሰረት በማድረግ ገቢ ሲመዘገብ ወጪውም በተመሳሳይ መቶኛ ከገቢው ላይ ተቀናሽ የደረጋል
    የተጠናቀቀው መቶኛ የሚወሰነው በግብር አመቱ የሚኖረውን ለውጥ እና በአመቱ የወጣውን ወጪ ከአጠቃላይ የውሉ ወጪ ግምት ጋር በማነፃፀር ይሆናል
    ኪሳራ ደርሱአል የሚባለው
    በውሉ ይገኛል ተብሎ የተገመተው ገቢ በእርግጠኛነት ከተገኘው ገቢከበለጠ እና ውሉ ሲጠናቀቅ ገቢና ውጪው መካከል ካለው ልዩነት ሲበልጥ ነው
    ለአዋጅ አንቀጽ 32 አፈፃፀም ከረጅም ጊዜ ውል ጋር ተያይዞ የሚያጋጥም ኪሳራ ተካክሶ እስከሚያልቅ ድረስ ወደኃላ ሊሸጋገር ይችላል (ደንብ 43)
    ለአዋጅ አንቀጽ 32 ለረጅም ጊዜ ከተደረገ ውል ጋር ተያይዞ በውሉ የመጨረሻ ዓመት ኪሳራ የደረሰበት እና በአንቀጽ 26 መሰረት ኪሳራውን እንዲያሸጋግር የተፈቀደለት ቢሆንም ኪሳራውን ማሸጋገር ያልቻለ ሆኖ በውሉ ዘመን መጨረሻ በኢትዮጲያ የንግድ ስራ መስራት ያቆመ እንደሆነ ይህ ግብር ከፋይ የደረሰበት ኪሳራ ወደ ኃላ ተመልሶ በዓምናው/አቻምናው የግብር ዓመት በተቀናሽነት እንዲያዝለት ይደረጋል
    ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎች
    የካፒታል ባህሪ ያላቸው ወጪዎች (ከእርጅና ቅናሽ ውጪ)
    የኩባንያ አክሲዮን /የሽርክና ማህበር መሰረት የሆነውን ካፒታል ለማሳደግ የሚወጣ ወጪ
    ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15% በላይ የሚደረግ የጡረታ/ፕሮቪደንት ፈንድ መዋጮ
    የአክሲዮን ድርሻ እና የትርፍ ድርሻ ክፍፍል
    በመድን፣ በካሳ/በዋስትና ውል መሰረት የተመለሰ/ሊመለስ የሚችል ወጪ/ኪሳራ
    ለበጎ አድራጎት ከተፈቀደው መጠን በላይ የወጣ ወጪ
    ግብር ከፋዩ ለራሱ የሚያወጣው የግል ወጪ
    ማንኛውንም ህግ/ውል በመጣስ የሚጣል የገንዘብ ቅጣት/የሚከፈል ካሳ
    ግበር ከፋዩ በሂሳብ መዝገቡ የሚይዘው በወቅቱ ወጪ ያልተደረገ ነገር ግን ለወደፊት በግብር አመቱ ለሚከሰቱ ጪዎች/ኪሳራዎች መጠባበቂያ የሚያዝ ገንዘብ
    የተከፈለ የገቢ ግብር ወይም ተመላሽ የሚደረግ የተጨማሪ እሴት ታክስ
    የኃለፊነት አበል ከተቀጣሪው ከመቀጠር ከሚያገኘው ገቢ 10% በላይ የሚከፈል የኃለፊነት አበል
    የመዝናኛ ወጪ (የምግብ አገልግሎት ከሚሰጡት፣ በማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ግበርና በስተቀር)
    የንግድ ስራ ሀብትን ግንኙነት ላለው ሰው ሲያስተላልፍ የሚደርስበት ኪሳራ
    የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008 አንቀጽ 27 እና 32

ความคิดเห็น •