እግዚአብሔር ማንንም አይጥልም | መጋቢ ጌታቸው | Pastor Getachew | EAG 6ilo | 2024
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 10 ก.พ. 2025
- እግዚአብሔር ማንንም አይጥልም
የመጽ. ቅ. ክ፦ መጽሐፈ ነገስት ካልእ 2፡ 1-4
ኢሳይያስ 49፡8-16
‘’ እንዲህም ሆነ፤ እግዚአብሔር ኤልያስን በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ሊያወጣው በወደደ ጊዜ ኤልያስ ከኤልሳዕ ጋር ከጌልገላ ተነሣ።
ኤልያስም ኤልሳዕን፦ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ልኮኛልና በዚህ ቆይ አለው። ኤልሳዕም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፥ አልለይህም አለ። ወደ ቤቴልም ወረዱ።
በቤቴልም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ወጥተው፦ እግዚአብሔር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው አውቀሃልን? አሉት። እርሱም፦ አዎን፥ አውቄአለሁ ዝም በሉ አላቸው።
ኤልያስም፦ ኤልሳዕ ሆይ፥ እግዚአብሔር ወደ ኢያሪኮ ልኮኛልና እባክህ፥ በዚህ ቆይ አለው። እርሱም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፥ አልለይህም አለ።’’
ይህ ጊዜ የኤልሳዕ የመጀመሪያ የኤሊያስ የመጨረሻ ጊዜ ነበር
በዚህ ዘመን ሰዎች በቀላሉ ይለያያሉ
ሩት ከኑሃሚን ላለመለየት የጸና አቋም ነበራት
ኤልሳዕ ከኤሊያስ የሚያስቀሩ ብዙ ግፊቶች ቢኖሩም ላለመለየት ወሰነ
የኤልሳዕ አይኖች ያተኮሩት በኤሊያስ ላይ ነበር
ልመናው በኤሊያስ ላይ የነበረው እጥፍ ቅባት ስለነበር እንደለመነው ሆነለት
የነብያት ጉባኤው ኤሊያስን እግዚአብሔር . . . ጥሎት ይሆናል ብለው ማስፈለጋቸው
እግዚአብሔር ማንንም እይጥልም አይረሳም ( ኢሳ. 49፡8-16)
ትኩረታችንን የእምነታችን ጀማሪ እና ፈጻሚ በሆነው በኢየሱስ ላይ ይሁን
እግዚአብሔር ማንንም አይጥልም
እግዚአብሔር ይባርካችሁ