ምሥጢረ ሥላሴ ከቀደሙ ሊቃውንት ምስክርነቶች

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 9 ก.พ. 2025
  • “እግዚአብሔር አንድ ነው፤ የማትከፈል የማትፋለስ መንግስትም አንዲት ናት፤ ከሥላሴ ምንም ምን ፍጡር ደኃራዊ የለም፤ በእነርሱ ዘንድ አንዱ ለአንዱ መገዛት የለም፡፡ አብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፣ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ ሥሉስ ቅዱስ በዘመኑ በቀኑ ሁሉ በግብርም በስምም ሳይለወጥ ሳይፋለስ ጸንቶ ያለ ነው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘሠለስቱ ምዕት ምዕራፍ 19፡5-6)
    “ወንድሞቻችን እኛስ እንዲህ እናምናለን፤ ያልተወለደ እግዚአብሔር አብ በተለየ አካሉ አንድ ነው፤ የተወለደ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስም በተለየ አካሉ አንድ ነው፤ በወደደው የሚያድር የአብ የወልድ እስትንፋስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ አንድ ነው እንላለን፡፡…አብ አምላክ ነው፤ ወልድም አምላክ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው፡፡ ግን ሦስት አማልክት አይባሉም አንድ አምላክ እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ምዕራፍ 25፡2-4)
    “ከሦስቱ ፍጡር የለም ፍጡራን አይደሉምና፡፡ ከዕውቀት ከሃይማኖት የተለዩ መናፍቃን ከቅድስት ሥላሴ መለኮት መከፈልን በአካላት መጠቅለልን ሊያመጡ አይድፈሩ ሦስት አማልክት ብለን አንሰግድም አንድ አምላክ ብለን እንሰግዳለን እንጂ፡፡ በስም ሦስት ናቸው እንላለን፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ባህርይ አንድ ሥልጣን ናቸው፤ በአንድ መለኮት በባህርይ አንድነት የጸኑ ሦስት አካላት ሲሆኑ ከሦስቱ አንዱ የሚበልጥ አንዱ የሚያንስ አይደለም፤ በማይመረመር በአንድ ክብር የተካከሉ ናቸው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ምዕራፍ 60፡6-7)
    “ወልድ ሳይኖር አብ ከአዝማን በዘመን ፈጽሞ አልነበረም፤ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ በዘመን አልነበረም፤ ሳይለወጡ ሳይለዋወጡ በገጽ በመልክ ፍጹማን በሚሆኑ በሦስት አካላት ጥንት ሳይኖራቸው በዘመን ሁሉ የነበሩ፤ ፍጻሜ ሳይኖራቸው የሚኖሩ ናቸው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቴዎፍሎስ ምዕራፍ 68፡5)
    “አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት በባህርይ አንድ ነው ብሎ ማመን ይህ ነው፤ የማይመረመር በቅድምና የነበረ አብ በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤…የማይመረመር በቅድምና ነበረ ወልድም በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤….የማይመረመር በቅድምና የነበረ መንፈስ ቅዱስም በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤ ሐዋርያት ያስተማሩዋት ቅድስት ቤተክርስቲያን የተቀበለቻቸው ቅዱሳት መጻሕፍት እንደተናገሩ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕራፍ 70፡14-17)
    “እኛ ግን በሥላሴ ዘንድ በማዕረግ ማነሥና መብለጥ የለም በመለኮት አንድ ወገን ናቸው እንላለን” (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ተግሳጽ ዘሰባልዮስ)

ความคิดเห็น • 1

  • @hailemariamchonbe5399
    @hailemariamchonbe5399 5 หลายเดือนก่อน

    ቃለ ሕይወት ያሰማልን ቀሲስ