የአፋር ታሪክ/History of Afar የሙዳይቶ ዳንካሊ አውሳ ራሃይቶ ታሪክ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 5 ก.พ. 2025
  • የአፋር ማኅበረሰብ ታሪክ
    የአፋር ሕዝብ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ500 ዓ.ዓ እስከ 15 ዓ.ም ድረስ ከየመን፣ ከግብጽ፣ ከአክሱም ነገሥታት ጋር ግንኙነት እንደነበራቸውና በስተሰሜን ከዳህላክ ደሴቶች ጀምሮ በስተደቡብ እስከ ዘይላ ድረስ ባለው አካባቢ እንደኖሩ ይነገራል።
    የአፋር ስምጥ ሸለቆ የታላቁ ስምጥ ሸለቆ አካል ሲሆን ይህም የጥንታዊ የሰው ልጅ ቅሪተ አጽምና ይጠቀምባቸው የነበሩ የድንጋይ መሳሪያዎች የሚገኙበት ስፍራ ነው። እነዚህ ቅሪተ አካላት በመገኘታቸው የሰው ልጅ አመጣጥን በሚመለከት ምርምር ለሚያደርጉ አጥኚዎች አካባቢው የወርቅ ጉድጓድ ያህል ቀልባቸውን ለመሳብ በቅቷል።
    የአፋር ህዝብ እስልምናን ከመቀበሉ በፊት የራሱ ባህላዊ እምነት ነበረው። እስልምና በአፋር ማኅበረሰብ ዘንድ የተስፋፋው በንግድ፣ በጋብቻ ጥምረቶች እና በመሪዎች ነበር። በንግድ የመስፋፋቱ ምክንያት አፋሮች በቀይ ባህር ንግድ በሚሳተፉ ጊዜ ከሚያገኟቸው ከአረብያ ከመጡ ነጋዴዎች ተምረውት ነው። የጋብቻ ጥምረቶች ደግሞ በዙርያቸው ካሉ ከአርጎባ፣ ከሀረሪ እና ከሶማሌ ሰዎች ጋር በነበራቸው ብዙ ጋብቻዎች ምክንያት ሐይማኖቱን ተምረዋል። ሌላው ደግሞ መሪዎቻቸው እስልምናን ሲቀበሉ ማኅበረሰቡም እምነቱን መቀበሉ እየጨመረ ሄደ።
    እስከ አሁን ድረስ ከተረፉ የታሪክ ምንጮች አፋር ለመጀመርያ ጊዜ የተጠቀሰው በ13ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአንዳሉሳዊው ኢብን-ሰዒድ በተፃፈ ጽሑፍ ነው። በዛም ላይ ዳንካል የተባለ ህዝብ ከሱዋኪን ወደብ አንስቶ ወደ ደቡብ ለዘይላ ቅርብ እስከሆነችው እስከ ማንደብ እንደሚኖር ገልጿል። ዳንካሊ የሚለው ቃል አፋርኛ ቃል ሲሆን ዳን እና ካሊ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተነሳ ነው። ዳን ማለት በአፋርኛ ህዝብ ወይም አገር ማለት ሲሆን ካሊ ደግሞ ህዝቡ የአፋር ምድርን የሚጠራበት ቃል ነበር። ይህም ቃል የአፋር ህዝብን፣ ቋንቋን፣ ባህልን እና አኗኗርን ለክፍለ ዘመናት ሲያመላክት ኖሯል።
    አፋር በኢትዮጵያ መዛግብት ላይ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። ከእነዚህም የመጀመርያው በአፄ አምደ ጽዮን ዜና መዋዕል ላይ ከአዋሽ ወንዝ ማዶ ስላደረገው ዘመቻ በሚገልጽበት ወቅት ነበር። የአፋር አገር በኢትዮጵያ መዛግብት ላይ አዳል ተብሎ ይጠራ ነበር። ይህ አዳል የሚለው ቃልም ከታችኛው አዋሽ ወንዝ አንስቶ ከአቤ ሐይቅ በሰሜን እስካለው አገር ድረስ ያለውን የሚወክል ቃል ነበር። ይህንንም ጆርጅ ሀንቲንግፎርድ "የዳንካሊ ግዛት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ፣ ቋሚ ውኃ ያለበት እና ረግረጋማ ነው" በማለት ገልፆታል። የአምደ ጽዮን ዜና መዋዕል ጸሐፊም በዘመኑ የነበሩት አፋሮች ቁመታቸው በጣም ረጅም እንደነበረ እና ጸጉራቸው የተጎነጎነ እና እስከ ወገባቸው እንደሚደርስ ገልጿል። በውግያ ችሎታቸው በመደነቅም ኃይለኛ ተዋጊ እንደሆኑና ከጦር ሜዳ እንደማይሸሹ ዘግቦታል።
    ማኅበረሰቡ ላክኦ ጊሌ እና ታጎሪታ የተባሉ ስለታማ መሳርያዎችንም እየተጠቀመ ኖሯል። የአፋር ማኅበረሰብ በታሪኩ ውስጥ ከአርሶ አደርነት ይልቅ ወደ አርብቶ አደርነት የሚያደላ ህዝብ ነው። ከብት እና ግመል ማርባትም ከጥንት የመጣ የማኅበረሰቡ ልምድ ነው። የከብት እና የግመል ወተትንም እያለቡ አራሪ እና ኮራ በተባሉ ባህላዊ የወተት ዕቃዎች ውስጥ ያስቀምጣሉ።
    ከአፄ አምደ ጽዮን አንድ ክፍለ ዘመን በኋላም በአፄ በእደ ማርያም ንጉሣዊ ዜና መዋዕል ላይ አፋሮች ተጠቅሰዋል። በዜና መዋዕሉም መሰረት የዳናክል መሪ ንጉሠ ነገሥቱ በዶባ ላይ በሚያደርገው ዘመቻ ሊያግዘው እንደነበር ይናገራል። ድጋፉንም ለማሳየት ለንጉሠ ነገሥቱ ፈረስ፣ ቴምር የተሸከመ በቅሎ፣ ጋሻ እንዲሁም ሁለት ጦር እንደላከለት ይዘግባል።
    በ16ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፖርቹጋላዊው አሳሽ ፍራንሲስኮ አልቫሬስ እንደገለጸው ከሆነ የዳንካሊ ግዛት በምዕራብ በኩል በአቢሲንያ፣ በምስራቅ በኩል ደግሞ በአዳል ሱልጣኔት ትዋሰን ነበር። ከዚህ በተጨማሪም የጨው ንግድ በአካባቢው እጅግ በጣም አትራፊ ንግድ እንደነበረ በመግለጽ በዘመኑ ይህ የጨው ማዕድን በአፋር አገር ቅናሽ እንደሆነ ነገር ግን ወደ ሸዋ በገባ ጊዜ ትልቅ ዋጋ ይሰጠው እንደነበር ገልጿል።
    በቀደመው ጊዜ የአፋር ማኅበረሰብ ራሳቸውን በቻሉ ግዛቶች የተዋቀረ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ግዛቶች በራሳቸው ሱልጣን ይተዳደሩ ነበር። ከእነዚህም ውስጥ የአውሳ ሱልጣኔት፣ የግራፎ(ቢሩ) ሱልጣኔት፣ የታድጆራህ ሱልጣኔት፣ የራሃይቶ ሱልጣኔት እና የጎባድ ሱልጣኔት ይመደባሉ። በ1577 ዓ.ም የአዳሉ መሪ ኢማም መሐመድ ጃሳ ዋና ከተማቸውን ከሀረር አንስተው በአሁኗ አፋር ክልል ወደምትገኘው ወደ አውሳ አዘዋወሩ። በ1647 ዓመተ ምህረትም የሀረር ኤምሬት መሪዎች የራሳቸውን ግዛት ለመመስረት ተገነጠሉ። የሀረሪ ኢማሞችም በደቡብ አፋር ያስተዳድሩ ነበር፤ ነገር ግን በ18ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአፋር የሙዳይቶ ሥርወ መንግስት ተገለበጡ። የሙዳይቶ ሥርወ መንግስትም የአውሳ ሱልጣኔትን አቋቋመ። የሙዳይቶ መሪ ሱልጣን ዋና መገለጫም የነበረው የብር በትር ነበር።
    አፋሮች በሁለት ክፍሎች የተከፋሉ ናቸው። እነዚህም አሳይመራ እና አዶይመራ ናቸው። ወደ ውስጥም ሲገባ ወደ መቶ ሀምሳ ክፍለ ጎሳዎች ይከፈላሉ። የአሳይመራዎች አለቃ ጎሳ ሙዳይቶ ነበር፤ የአውሳ ሱልጣንም የሚወጣው ከዚሁ ከሙዳይቶ ጎሳ ነው።
    በ19ነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ካሳ መርጫ(የኋላው አፄ ዮሐንስ አራተኛ) በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ላይ አምጸው እንዳይያዙ ወደ አፋር ሸሽተው ነበር። በዛም አንድ አፋር ሙስሊም አለቃ የነበሩ ሰውን ሴት ልጅ አገቡ፤ እርሷም ተጠምቃ ምሥጢረ ሥላሴ ተባለች፤ ከእርሷም አርዓያ ሥላሴ ዮሐንስ ተወለደላቸው።
    በዘመኑም በግብፃዊው ካዲቭ ኢስማኤል ፓሻ ዘመን ግብፅ በአፍሪካ ቀንድ በምታደርገው መስፋፋት ወቅት ሀረር እና በዙርያዋ የሚገኙ አካባቢዎችን በጦርነት ተቆጣጥራ ነበር። የአፋር ሰዎችም የግብፅን ወረራ ለመከላከል ብዙ ጦርነቶችን አድርገዋል።
    በ19ነኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ የራሃይቶ እና የታድጆራህ ሱልጣኔት የቀይ ባህር ወደቦች በአውሮፓ ቀኝ ገዥ ኃይሎች ተወሰዱ። ጣልያኖች የኤርትራን የምፅዋ እና የአሰብ ወደብን ያዙ፤ ፈረንሳዮች ደግሞ ጅቡቲን ያዙ። አውሳ ግን ከወደቡ ርቃ ራሷን ችላ መቆየት ቻለች። አንፃራዊ በሆነ ሁኔታም በአዋሽ ወንዝ ለምለም ቦታ ላይ ስለምትገኝ በበረሃማ ቦታዎች ተከልላ ነበር።
    ዳግማዊ አፄ ምኒልክም የአገር ማቅናት ዘመቻዎችን በሚከውኑ ጊዜ ግዛታቸውን ከሸዋ አንስተው ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ሲያስፋፉ አውሳ ለምኒልክ ግብር በመገበር ራሷን በራሷ ሱልጣን ማስተዳደር ቀጠለች። በመጀመርያው የኢትዮ ጣልያን ጦርነት ወቅትም ላይ ምኒልክ የአውሳ ሱልጣን ከጣልያኖች ጋር ድርድር እንዳያደርጉ አሳመኗቸው።
    በሁለተኛው የኢትዮ ጣልያን ጦርነት ወቅት ሱልጣን ሙሐመድ ራሱን ችሎ እንዲያስተዳድር ተፈቅዶለት የጣልያኖችን ወረራ አልተቃወመም ነበር። አውሳዎችም ሮምን በሚጎበኙ ጊዜ ያዮ እና አሊሚራህ የታሰሩትን ልዑል ራስ ኢምሩ ኃይለ ሥላሴን ጎብኝተው እና የገንዘብ እርዳታም አድርገው ነበር። እንዲፈቱም ጥያቄ ቢያቀርቡም ስኬታማ ግን አልነበሩም። ኢትዮጵያም ነፃ እየወጣች በነበረበት ወቅት ያዮ እና አሊሚራህ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ የፋሽስት ጣልያን ወታደሮችን ማርከው አዲስ አበባ ድረስ ከንጉሠ ነገሥቱ ዘንድ አመጧቸው።
    ይህ ተግባራቸው ያዮ እና አሊመራህ ከኃይለ ሥላሴ ጋር ጥሩ ወዳጅነት እንዲኖራቸው ቢያደርግም ሱልጣን ሙሐመድ ግን ከፋሽስት ጣልያን ጋር በነበረው ህብረት ምክንያት በዚህ ተግባራቸው ደስተኛ አልነበረም። ብዙ አውሳዎች እና ያዮም "ንጉሠ ነገሥታችን ተመልሰዋል፣ ነጮች ተሸንፈዋል" ብለው ሱልጣን ሙሐመድን ተቃወሙት። ሱልጣን ሙሐመድም ያዮን አሳደደው።
    ያዮም ወደ አዲስ አበባም በመሄድ ለንጉሠ ንገሥቱ ያለውን ነገር በማሳወቅ ሱልጣን ሙሐመድ ከሥልጣን መውረድ እንዳለበት አስማማቸው። ያዮም ከሙዳይቶ ሥርወ መንግስት አይዳሂሶ ቅርንጫፍ የዘር ሀረግ ባለ መምጣቱ ምክንያት የአፋር ህዝብ እንደ ሱልጣን እንደማይቀበለው ስለተሰማው ከአይዳሂሶ ጎሳ የመጡት አሊሚራህ ሱልጣን እንዲሆኑ ጠየቀ። ከንጉሠ ነገሥቱም ዘንድ አሊሚራህ ደጃዝማች የተባለ ማዕረግ፣ ያዮ ደግሞ ፊታውራሪ የተባለ ማዕረግ ተሰጥቷቸው፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የክቡር ዘበኛ ወታደሮች ከሥራቸው ተመደበላቸው። ሱልጣን ሙሐመድንም ማርከው ወደ አዲስ አበባ ሰደዱት።
    ማጣቀሻዎች(References)
    1. en.wikipedia.o...
    2. en.wikipedia.o...
    3. eprdfblog.blog...
    4. en.wikipedia.o...

ความคิดเห็น • 12

  • @AbdellahHabib-x2g
    @AbdellahHabib-x2g หลายเดือนก่อน

    True historic ❤

  • @ካሳይ
    @ካሳይ หลายเดือนก่อน

    ምርጥ

  • @alemshaygebremarim4642
    @alemshaygebremarim4642 หลายเดือนก่อน

    ሃፀይ ዮሃንስስ ካብ ሃፅይ ተድሮስ ትሃብኡ ሃሳዊይ ኣብይ ርክብካዩ ሃበሬታ፡ ሃፀይ ዮሃንስ ንጣልያን ዝይፍርሁስ ንሃፅይ ተድሮስ፡ 100% ሃቐኛ ታሪክ ኣይኮንካን ትከስት፡

    • @Antenehkinfu
      @Antenehkinfu หลายเดือนก่อน

      😂😂😂😂 tadlsh ketebabnt ena ke denkurna wechi ke telacha wechi ayimrobsh bado new ambebi kelbi zem blsh atchuhi

  • @mohamedshukr
    @mohamedshukr หลายเดือนก่อน +1

    የወሎን ስራልን

    • @IsaacAl-kemis
      @IsaacAl-kemis 17 วันที่ผ่านมา

      ወሎ ቤተ አማራ ነው

  • @henossolomon3165
    @henossolomon3165 หลายเดือนก่อน

    Sultan Alimirah Hanfere has died in Amharic Miyaziya 17 not 16 because it said April 25 not 24.

  • @omerabdela8
    @omerabdela8 4 วันที่ผ่านมา

    The Tribes Hudiato Hadi Hadu Hassoba Obkarto Tora maria Mensa arak Kona are afar Saho Irob Estimated establish over twelve thousands years go high level institutions distinguished Custom Traditional geographic located from bori pinnisula including suwkin samhar adolis kohito hirgigo ragali adaro Aynadib hidida afdage dobato la Hazo Following folfolo fofal af gazeain abaala magale Erbeti dallol depression edga hamus adigrat hademo sanafe homora kasla Aksum gash barka ferawon Malat adokuda afdera hugubta harohar barhale endeli domali Adele sourro eloita two walallo beddu konnaba negdaw Dorra raile kululi dangal badda Ramod buyya idafalo samoti sabat dalbakan dahlak karura wangabo baylul assab halab rahito hayyu takori babal mandab zelah more South eastern include ware dig warder geladin warder gode kabri dahar edga Babur karmara moyale gursum babile errer harer mullu gadmaytu unda pho gadmaytu diridwa gawane mathara nazret zebrit dobti samara logiya melle dawe batti dese kobolisha shewa robit higke addis ababa hawsha assossa gabella gojam design marikos dangila bari dar gonder mekelle gumusa daein homora adwa gumusa daein barih arguda madrat Malat gaddi wagga //"

  • @alemshaygebremarim4642
    @alemshaygebremarim4642 หลายเดือนก่อน

    ዓመድ ፅዮን ትግራዋይ እዩ፡ ተጋሩ ነገስታት ኣብ ታሪኩም ገልፆሞም፡ ኣምሃሩ ክእ ኣይገለፅዎምን፡ ዓፋር ኣስላም እዮም ኢስልምና ክኣ ናይ ተግራይ ነገስታት እዮም መስሪቶሞም😂፡ ዓፋር ኩሉ ግቤ ኣብ ትህትይ ተጋሩ ነግስታት፡ ኣብስንያ ማላት ትግራይ ማላት እያ ኣምሃራ ብሄርስብ ዝጠቓለለ ኣይመስልኩም፡ ትግራይ ኩሉ ግዜ ብሄር ብሄርስብ ምስሃቖፍት እያ፡

    • @antibaathism
      @antibaathism หลายเดือนก่อน

      Amde seyon is from the amhara people