MK TV || ዜና ተዋሕዶ || ከኦርቶዶክሳውያን ሥርዓት ያፈነገጠ አነጋገር

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 27 พ.ย. 2024

ความคิดเห็น • 32

  • @etagdyoutube8262
    @etagdyoutube8262 12 ชั่วโมงที่ผ่านมา +6

    በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው የተዋቂ ሰወች አውደ ምህረት ላይ መተራመስ😢

  • @beteberana-2657
    @beteberana-2657 วันที่ผ่านมา +12

    በጣም አሳሳቢ ነገር ነው። አውደ ምህረቱ እጅግ በጣም ሊፈራ እና ሊከበር የሚገባው ነገር ሆኖ ሳለ ሁሉም ታዋቂ ነኝ ባይ እየመጣ ከፈነጨበት ነገ ላይ ከባድ ዋጋ እንዳያስከፍለን ስጋት አለኝ።

    • @SkyRamaEt
      @SkyRamaEt 6 ชั่วโมงที่ผ่านมา

      አሁንስ ዋጋ እያስከፈለን አይደል እንዴ???

  • @SenaitT-f4z
    @SenaitT-f4z วันที่ผ่านมา +12

    ዲኮሩ እራሱ ቢቀር

  • @teshomenigussu7392
    @teshomenigussu7392 วันที่ผ่านมา +3

    ቃለ ህይወት ያሰማልን የአገልግሎት ዘመኖትን ይባርክልን መምሕራችን ምእመናን በአውደ ምሕረት መገኘት የሚችሉት ለምስክርነት ነው ታዋቂ ስለሆንን እግዚአብሔር በልዩ ሁኔታ አይመለከተንም

  • @zerfietifitu
    @zerfietifitu ชั่วโมงที่ผ่านมา

    በርቱልን❤❤❤

  • @ራያወለላ
    @ራያወለላ วันที่ผ่านมา +2

    ትክክል ቃለህይወትን ያሰማልን ❤

  • @IssayasBekeleDemeke
    @IssayasBekeleDemeke 17 ชั่วโมงที่ผ่านมา +4

    ዓውደ ምህረት ከስብከተ ወንጌልና ከቃለ እግዚአብሔር ውጪ እንዳይፈጸምበት እስካልተደረገ ድረስ የምዕመናን መኮልኮል ፋይዳው ምንድን ነው?
    በዓውደ ምህረት ላይ እርስ በርስ መሞጋገስ፣ ገንዘብ ልመና፣ በተለያዩ መምህራን የድግግሞሽ ስብከት ፣ርዕስ ሳይጠብቁና ከመጠን ያለፈ ጊዜ መውሰድ፣ስለ ልማት ዲስኩር ማብዛት ወዘተ ለምዕመናን ጥቅሙ አልገባኝም!?
    ዛሬም አልመሸምና ስብከተ ወንጌል ተጠናክሮ ይቀጥል፤ የዓውድ ምህረትን ክፍለ ጊዜ ለመንፈሳዊነት ብቻ ይዋል። ዛሬም ብዙ ቤተ ክርስቲያንን ያልተረዳ ምዕመንን እንደያዝን መረሳት የለበትም።

  • @hailemicael4782
    @hailemicael4782 9 ชั่วโมงที่ผ่านมา

    የእለቱን ዜና ከማንበብሽ በፊት ዕለቱ እና ቀኑን መግለጽ ይገባል፡፡በተረፈ በርችልን፡፡

  • @MeronTeshome-f6i
    @MeronTeshome-f6i 3 ชั่วโมงที่ผ่านมา +1

    እባካቹ አውደምህረትን ለተዎቂሰዎች አትሰጡብን መድረክ አይደለም የክርስቶስ ቃል የሚነገርበት

  • @enyewgashaw4548
    @enyewgashaw4548 16 ชั่วโมงที่ผ่านมา

    kalehiwot yasemalin

  • @አሰፋ
    @አሰፋ วันที่ผ่านมา

    ቃለሕይወት ያሠማልን

  • @geraethiopia
    @geraethiopia วันที่ผ่านมา +1

    እግዚአብሔር ይስጥልን! ቅ/ቤተክርስቲያን ሊቃውቶቿ ወጥተው የሚያስተምሩበት አጥተው በየቦታው እያሉ በትክክል እንኳን የአለምን ስራ የመስራት ፈላጎት ያለጠፋላቸው ታዋቂ ሰዎች አውደምረት ላይ ሲወጡ: የቤክርስቲያንን ስርዐት የተረዱ ምዕናን ወይም አባቶች ብቻ ሊያስተዋውቁት የሚገባውን ነገር ታዋቂ ሰዎች በመታወቃቸው ብቻ እንደነገሩ ሲያደርጉት ይህን ክፋ ቀን እንለፍ እያልን ስናይ ከርመናል።እኔ ሰውን መተቸት የሚያስችል የክርስትና ቁመና የለኝም ግን እውነቱን እውነት ሀሰቱንም ሐሰት ማለትን ቅ/ቤተክርስቲያን አስተምራኛለች ስለሆነም አውደምህረት ላይ የሚወጡት ብዙዎቹ የቤክርስቲያ ጉዳይ አንግብግቧቸው እንደሆነ ባምንም ለገጽታ ግንባታ የሚወጡም እንዳሉ በደንምብ ተረድቻለሁ።የተወደዳችሁ ታዋቂ ክርስቲያን ወንድም እህቶቼ ቅ/ቤተክርስቲያንን በትክክል ልትጠቅሙ የምትችሉበትን እና በትክክል ለድህነት የሚሆነውን የአግልግሎት ዘርፍ ብቻ መርጣችሁ እንድታገለግሉ በትህትና እጠይቃችሗለሁ። በስራችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን አስባችሁ ከሰራችሁ ለኔ በትክክል እያገለገላችሁ ቅ/ቤተክርስቲያንንም ከፍ እያደረጋችኋት እዳላችሁ እደሆነ የምርረዳው ያኔ ነው። አውደምህረት እሳት ነው ሊቃውንቱም በፀሎት በእግዚአብሔር አጋዥነት ይዘውት እንጅ የሚሆን አይደለም።በተካናችሁበት በመክሊታች በስራችሁ በዛ በሚገባ አገልግሉ። የተወዳችሁ ማህበረ ቅዱሳን ከመጣሽ ማርያም ታምጣሽ ነው እና ቤ/ክርስቲያናዊ ትውፌትን እና አሁን አሁን በንግስ በቅዱሳት መፃህፍት ምርቃት በተለያዩ አውደምህረት ላይ እየተደረገ ያለውን ዲኮር ታሳቢ ያደረገ ኘሮግራም እንድትሰሩልን እጠይቃለሁ።በረከታችሁ ይደርብን!!!

  • @seyoum917
    @seyoum917 วันที่ผ่านมา +1

    መምህር ዐቢይ ጌታሁን የተናገሩት ትክክል ነው ።
    ዛሬ ቤተክርስቲያንን በብዛት የወረሯት አዋቂዎች ሳይሆኑ ታዋቂዎች ናቸው ።
    እኛም እንደምእመን ችግር አለብን የታዋቂዎች ተከታይ ነን እንጂ አዋቂ መምህራንን አናዳምጥም ።
    በዛሬ ጊዜ መምህራን እየተባሉ ብዙ ሰባኪዎች አሉ በቅድስና ኑሮአቸው ሳይሆን በመድረክ ላይ ቆመው ሊያስተምሩ ይሞክራሉ ነገር ግን ድካማቸው ከንቱ ነው ።
    አንዳንዶቹ መስቀላቸውን ከውጭ እንዲታይ አንጠልጥለው ይሳደባሉ ግን ማእረጋቸው መምህር ነው ።

  • @lidiya727
    @lidiya727 วันที่ผ่านมา +2

    ማርያምን ይሄ የዝነኞች ነገር አብዛኛውን ሰው እያናደደ ነው ስንት የቤተክርስቲያን ሊቅ አባቶች ወንድሞች እያሉ እነሱ ስለምን ይጋበዛሉ ሲጀመር የነሱ ቦታ አይደለም ከፈለጉ ከምዕመኑ ጋር ይቀመጡ ካልፈለጉ ይውጡ ቤተክርስቲያንን ዝቅ አታድርጉ

  • @tsegayebetelhm5226
    @tsegayebetelhm5226 10 ชั่วโมงที่ผ่านมา

    ነገ ያሥፈራኛል ድሮ ድሮ ለአውደ ምህረቱ የበቁ የተማሩ አገልጋዮች እንኳን አይገባንም ነበር የሚሉት የዘንድሮዎቹ ደግሞ ለዓለምም ለመንፈሳዊም የተገዙ ናቸው አይገባኝምን አያውቁም ፍጥጥ ብለው ያስተምራሉ ብዙ ሥርዓት እየተፋለሰ ነው አረ እባካችሁ ነጋችንን እንድንፈራው አታድርጉን😢መምጣታቸውን አንጠላም ግን እነርሱ ሕዝባውያን ናቸው እንደእኛ ምዕመን ነው ሆነው መቀመጥ ያለባቸው‼️ አባቶቻችን ለገንዘብ እየተሽቀዳደሙ ከብዙ ነገር እያራቁን ነው😢

  • @danimanutd1528
    @danimanutd1528 วันที่ผ่านมา +1

    እውነት ነው፡፡ ለምን አለማዊ የሆኑ አርቲስቶች በአውደ ምህረት ገቢ ለመሰብሰብ ብሎ ማስደፈርና የመጽናኛውን መድረክ መላላጫ መድረክ ማረግ በእውነት ልክ አደለም፡፡
    እንዲ ስንል ደሞ ቅናት ምቀኝነት ምትሉ ደሞ ትክክሉን ያሳያቹ

  • @Lula2090
    @Lula2090 11 ชั่วโมงที่ผ่านมา

    ከነሜካፖቸዉ ከነታቱ ፍፁም ድፍረት በተሞላው መልክ ነዉ አዉደምሕረቱ ላይ የሚወጡት

  • @masereshaalemayehu611
    @masereshaalemayehu611 11 ชั่วโมงที่ผ่านมา

    በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ ነዉ 😢😢😢

  • @adisalem1777
    @adisalem1777 17 ชั่วโมงที่ผ่านมา +2

    በዚህ ዘመን ትኩረቱ ስብከተ ወንጌል ላይ ሳይሆን ፤ ገንዘብ ላይ በመሆኑ ታዋቂ ሰዎችን በመጋበዝ የበለጠ ገቢ ማስገኘት ይቻላል የሚለው እሳቤ ለቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ጉዞ ትልቅ ማነቆ ነው።

    • @Lula2090
      @Lula2090 11 ชั่วโมงที่ผ่านมา

      ትክክል

  • @sebhatenegeh
    @sebhatenegeh 16 ชั่วโมงที่ผ่านมา

    በተለይ አትሊስት ይሁኑ አርቲስቶች ዐውደ ምሕረቱን ተቆጣጥረውታል ያውም ያለ ምንም ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ከ
    አንድ ነገር ማድረግ ይጠበቃል

  • @SundayTube
    @SundayTube 7 ชั่วโมงที่ผ่านมา

    እሱ ለኔ ጥያቄም ነው እሄ ማለቴ አይምጡ አይደለም አይሳተፉም ለማለት አይደለም ግን ተዋቂ ስለ ሆነ ብቻ አንዴ ዘፈን እያስተዋወቃ አንዴ ደግሞ እዚህ መድረክ ላይ መተዉ እሄ ነው ምና ምን ማለት ገደብ ያስፈልጓል

  • @MesiBatigst
    @MesiBatigst วันที่ผ่านมา +1

    እባካችሁ ገብረ መስቀል የሚሉትን ሰው ከአውደ ምህረት አውርዱልን በተለይ ዳር ዳር ያሉ አጥቢያዎች ላይ። ሲለው ባህታዊ ሲለው መምህር ሲለው ነብይ ባለብዙ ትንቢት ሲለው በጎ አድራጊ ሰለው ዩቱበር

    • @atmmej
      @atmmej 17 ชั่วโมงที่ผ่านมา

      ሰወችን ለማባረር አትቸኩሉ

    • @SkyRamaEt
      @SkyRamaEt 6 ชั่วโมงที่ผ่านมา

      ገብረመስቀል ዱርዬው ቢዝነስ ማን😂😂😂

  • @yirgalemmekonnen9544
    @yirgalemmekonnen9544 11 ชั่วโมงที่ผ่านมา

    ቤተክርስቲያን ሊቃዉንቷን እየደበቀች አለማዉያንንና ሰርቆ ከባሪዎችን በአዉደምህረቷ ከሰበሰች ቆየች ይህን የፈቀድነዉ ደግሞ ሁላችን ነን ከላይ እስከታች ዉዳሴማርያም በአግባቡ አያዉቅም የተባለን ጳጳስ ይዘን ሁሉን እያዩ ያነካካኛል ብለዉ አፌን በዳቦ ያሉ ማህበራትና ሰብሳቢዎቻቸዉ ጠንክረን መሪ ፈጥረን ያላስከበርናት ምዕመናን እንደዜና ስላቀረባችሁት እናንተም ጭምር ፀሐይ የወጣ ዕለት ከታሪክ ተወቃሽነት አታመልጡም

  • @rob21112
    @rob21112 10 ชั่วโมงที่ผ่านมา

    Esti hullum be channalu milekewun mezmur askumuln...be Betekerstian sayitay sayugebmmegem..hullum youtube lay yilekal, endet new tikiklegnawun kalhonew minleyeww

  • @kirubel1120
    @kirubel1120 วันที่ผ่านมา

    ይሄንን የሚገርመው ህዝበ ክርስቲያኑ ይሄን ያውቃል። በቤተክርስቲያኑ አስተዳደር እርከን ላይ ያሉ ናቸው እያወቁም ሳያውቁም ምንአለበት በማለት ለጥቅም ሲሉ የሚዳፈሩት። አውደ ምሕረት ማለት ሲገባ መድረክ አይደል እንዴ የሚሉ አንዳንዶቹ።

  • @SkyRamaEt
    @SkyRamaEt 6 ชั่วโมงที่ผ่านมา

    እንደነ እሸቱ አይነት እንደነ ይገረም ደጀኔ አይነቱ ነዋ ሁለት ዓለም ውስጥ ሆነው የሚበጠብጡን 😂😂😂😂