DW Amharic የጥር 24 ቀን 2017 የዓለም ዜና

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 7 ก.พ. 2025
  • የጥር 24 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ “አሁን ያለውን የፖለቲካ ጩኸት እንዳትመለከቱ” የሚል ጥሪ ለብልጽግና ፓርቲ አባላት አቀረቡ። ዐቢይ በፕሬዝደንትነት ለሚመሩት ፓርቲ “ከፊታችን ያለው አስደማሚ ዘመን ነው” የሚል ተስፋ ሰጥተዋል። በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ እና በትግራይ ክልሎች ያሉትን ጨምሮ በኢትዮጵያ በመካሔድ ላይ የሚገኙ “ግጭቶች ጠንሳሽ ትናንትና ፖለቲካ ሲያንቦጫርቁ የነበሩ ሰዎች ናቸው” ሲሉ ከሰዋል።
    • የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሀገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ በሆነችው ኦምዱርማን በሚገኝ ገበያ ላይ በከባድ መሣሪያ በፈጸመው ድብደባ 54 ሰዎች መገደላቸውን የሱዳን መንግሥት አስታወቀ። ሰብሪን በተባለው ገበያ ላይ በተፈጸመው ጥቃት 158 ሰዎች መጎዳታቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
    • ኤርትራ፣ ግብጽ እና ሶማሊያን ጨምሮ ቻይና ከበርካታ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የእስያ ሀገራት እንስሳት ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች።
    • የአረብ ሀገራት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጤማውያንን ወደ ግብጽ እና ዮርዳኖስ ለማዘዋወር ያቀረቡትን ሐሳብ ውድቅ አደረጉ። ዛሬ ቅዳሜ ሐማስ ሦስት ታጋቾች እስራኤል 183 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቀዋል።
    • ሩሲያ ለሊቱን በ46 ሚሳኤል እና በ123 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ድብደባ መፈጸሟን የዩክሬን አየር ኃይል አስታወቀ።
    • የቀድሞው የጀርመን ፕሬዝዳንት ሖርስት ኩለር ከዚህ ዓለም ተለዩ። የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ጽህፈት ቤት ኩለር ከአጭር ጊዜ ሕመም በኋላ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት በበርሊን ከተማ በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን አስታውቋል።

ความคิดเห็น • 7

  • @desalegnteklehaimanot2683
    @desalegnteklehaimanot2683 5 วันที่ผ่านมา +1

    ሰላም ሰላም።

  • @Humed.MohammedAbdella-m6h
    @Humed.MohammedAbdella-m6h 6 วันที่ผ่านมา

    ሰላምለሀገራችንኢትዮጵያእናለመለውዓለም❤?

  • @AbduA.du.a.d
    @AbduA.du.a.d 6 วันที่ผ่านมา +1

    ❤❤❤❤

  • @BakeBati
    @BakeBati 6 วันที่ผ่านมา +1

    ብልፅግነ እንደ ኮርደር ልመት ፍራሽ ከድርውን ወየኔ የዘራ እንክርደድ ስለሆነ መፍረስ አለበት እሱነው ብልፅግና ወደፍት እንደይራማድየደራጋ

  • @ቀጥተኛውመንገድ
    @ቀጥተኛውመንገድ 6 วันที่ผ่านมา +1

    እነደ አሜሪካ ባለስልጣን ባለጌ የለም ለምን እስራኤልን ወደ አሜሪካ አያሰፈሩም!!!!!

  • @ABDIShafi-v8f
    @ABDIShafi-v8f 6 วันที่ผ่านมา

    Ulet new

  • @derejebeyenedegefie8011
    @derejebeyenedegefie8011 6 วันที่ผ่านมา

    Dr. Abey is very brilliant....prosperity party is the only great Democrat Part exist on Earth. All prosperity members should proud.....😂😂😂😂😂😂