ጸሎተ ቱላዳን፤ ዘረቡዕ። እግዚአብሔር ለቅዱስ ጊዮርጊስ የገለጸለት ስዉር ስም ነዉ።

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 26 ต.ค. 2024
  • #ጊዮርጊስ
    ተወዳጆች ሆይ ይህ ታላቅ ጸሎት ‹‹ጸሎተ ቱላዳን›› ስያሜውን ያገኘው በጸሎቱ ውስጥ በሚገኝ ‹‹ቱላዳን›› በተሰኘው ኅቡእ ስም ነው፡፡ ይህ #ጸሎተ_ቱላዳን ከቀድሞ ጀምሮ አባቶቻችን አጥብቀው ሲጸልዩት እና ራሳቸውን ከጸብአ አጋንንት ሲጠብቁበት የኖረ ነው፡፡
    እግዚአብሔር አምላካችን በንግሥና ለነበሩት ለቅዱስ ዳዊት እና ለጥበበኛው ሰሎሞን ግርማ ሞገስ እንዲኖራቸው ይህን ጸሎት ሰጥቷቸዋል፡፡ እንዲሁም ለቅዱስ ዮሐንስ እና ለቅዱስ ጴጥሮስም በዚህ ጸሎት ኅቡእ ስም እንዲጠቀሙ ጌታ ሰጥቷቸዋል፡፡
    በተለይ ይህን ‹‹ጸሎተ ቱላዳን›› #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ እጅጉን ተጠቅሞበታል፡፡ ወጣቱ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ በከሃዲው በዱድያኖስ እጅ በሰው ኅሊና ለማሰብ የሚከብዱ ሥቃያትን ሲቀበል እና የዱድያኖስ ሟርተኛ ጥንቋዮች የክፉ አጋንንትን ስም እየጠሩ መርዝ ሲያጠጡት በእግዚአብሔር ኃይልና በኅቡእ ስሞች ኀይል አስማታቸውን እየሻረ መርዛቸውን እያረከሰ ይጠቀምበት ነበር፡፡ ስለዚህ እኛም የእነርሱን ፈለግ ተከትለን ልንጸልየውና ልንጠቀምበት ይገባል፡፡
    #ጸሎተ_ቱላዳን_ጥቅሙ_ምንድን_ነው?
    ጸሎተ ቱላዳን ዋነኛ ጥቅሞቹ በሕይወታችን፣ በቤተሰባችን፣ በልጆቻችን በንብረታችን ላይ አደጋ ከሚያደርሱብን ከአጋንንት፣ ከመተት ድግምት እና ከክፉ ሰዎች ገቢራዊ ተንኮል ይጠብቀናል፡፡ ወዳጆቼ እግዚአብሔር ራሳችንን ከክፉ መናፍስት እና ከክፉ ሰዎች ተንኮል እንድንጠበቅ ያልሰጠን ነገር የለም፡፡ እኛ አልጠቀም ብለን እንጂ ከሰማይ የተሰጠን ጸሎትና ጸጋ እንኳን ከምድራዊ ጠላት ከገሃነመ እሳት የምንድንበት ነው፡፡ ስለዚህ የዚህ የጸሎተ ቱላዳን ጥቅሙ መለኮታዊ ጥበቃ እንድናገኝ ይረዳናል፡፡
    #ጸሎተ_ቱላዳንን_ጀምሮ_ማቋረጥ_ለፈተና_ይዳርጋልን?
    አንዳንድ ሰዎች ጸሎተ ቱላዳንን ለመጸለይ ይፈራሉ፡፡ የሚፈሩትም ‹‹ጸሎቱ ተጀምሮ አይቋረጥም፡፡ ከተቋረጠ ለፈተና ይዳርጋል›› ከሚል ፍርሃት አዘል እሳቤ ነው፡፡ በመሠረቱ እንኳን ጸሎተ ቱላዳን ቀርቶ ማንኛውንም ጸሎት ባናቋርጥ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ሰው እንደ መሆናችንንና ሩጫ በበዛት ዓለም እንደመኖራችን መጠን በሕመም፣ በለቅሶ፣ በሠርግ እና በአንዳንድ ማኅበራዊ ጉዳዮች ጸሎት ልናስታጉል እንችላለን፡፡
    ጌታችን ‹‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ›› ያለን በተቻለን መጠን ጸሎት እንዳናስታጉል ነው፡፡ ‹‹ትጉና ጸልዩ›› ማለት ጸሎት ሳታቋርጡ ጸልዩ ማለት ነው፡፡ ግን ከላይ በሚያጋጥሙን ሰዋዊ ችግሮች ምክንያት ጸሎት ብናስታጉል ችግር የለውም፡፡
    ጸሎተ ቱላዳን ልዩ ጥቅሙ የመናፍስትን ውጊያ የሚያርቅ እና አጋንንትን የሚቀጠቅጥ ጸሎት በመሆኑም ነው ለመጸለይ የሚፈሩት እና ከተቋረጠ ለፈተና ይዳርጋል የሚሉት፡፡ ስለዚህ እንደማንኛውም ጸሎት ያለ ፍርሃት ተግታችሁ ብትጸልዩት ጉዳት ሳይሆን ብዙ ጥቅም ታገኛላችሁ፡፡
    #ጸሎተ_ቱላዳንን_እንዴት_እንጸልይ?
    ጸሎተ ቱላዳን እንደ ውዳሴ ማርያም በሰባቱ ዕለታት የተዘጋጀ በመሆኑ እንዲሁም በውስጡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ባለ ኅቡእ ስሙ መልክአ ሥቃዩ ስላለበት በቀኑ በርትቶ መጸለይ ይገባል፡፡ ባለ ኅቡእ ስሙ መልክአ ሥቃዩ ለጊዮርጊስም ከብዙ ፈተናና ከመተት ከድግምት ከክፉ አጋንንት ተንኮል ይጠብቀናል፡፡
    ጸሎተ ቱላዳን በሌሊት አልያም በጠዋት ከምግብ በፊት ብንጸልየው ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም ጠዋት ከቤት ስንወጣ ምን እንደሚገጥመን፣ አጋንንት በሥራ፣ በሕይወት እንዴት ባለ ፈተና እንደሚፈትነንና ለአደጋ እንደሚያጋልጠን ስለማናውቅ ውሎአችን የሰላም እና የመለኮታዊ ጥበቃ እንዲሆን ጸልየነው ብንወጣ መልካም ነው፡፡
    #ጸሎተ_ቱላዳን_ውስጥ_ስለሚገኙት_ኅቡእ_ስሞች_ማብራሪያ?
    ጸሎተ ቱላዳን ላይ አስገራሚ፣ አስደናቂና ለማንበብ ከበድ የሚሉ ኅቡእ ስሞች ይገኛሉ፡፡ ኅቡእ ስም ማለት የተሰወረ ስም ማለት ነው፡፡
    ወለላይቱ እመቤት ድንግል ማርያም መጥቁል የተባለ ጋኔን ሳቢ አጋንንት ስቦ በአጋንንት ሊያጠፋት በመጣ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ብታመለክት ‹‹ዮሰሜር፣ አድሜሽ፣ ድቸር፣ አዶናዊሮስ፣ ሰራሰቅስርኤል›› የተባሉ ኅቡእ ስሞች ተገልጾላት ብትጸልያቸው እነዚያ ኹሉ አጋንንት ከጠንቋዩ ከመጥቁል ጋር በመብረቅ አልቀዋል፡፡
    ጸሎተ ቱላዳንን አንዳንድ ሰዎች የጠንቋይ መጽሐፍ ነው ይላሉ። ይህንን የሚሉት ስለ ጸሎቱ የማያውቁና ጸሎቱን የማይጠቀሙበት ናቸው። በተለይ አጋንንት የሚጎትቱት የሚጠነቁሉት ጸሎቱ ጥንቆላቸውን መተታቸውን ስለሚፈታና ስለሚሽር ይቃወሙታል።
    ኢትዮጲያዊው ታላቁ ጻድቅ አቡነ አባለ ክርስቶስም ሲወለዱ በሰውነታቸው ላይ የእግዚአብሔር ኅቡእ አስማት በሰውነታው ላይ ተስሎ/ተቀርጾ/ ነው የተወለዱት፡፡ ኅቡእ ስሙም ‹‹ዲካባ፣ ማርትያስ፣ ክስብኤል›› የሚሉ ነበሩ፡፡
    የአቡነ አባለ ክርስቶስ አባት ቅዱስ አርቃድዮስ እና እናታቸው ቅድስት ታውክልያ በልጃቸው ሰውነት ላይ ስለተቀረጹት ኅቡእ ስሞች ደንግጠው ሲጨነቁ ሳለ ቅዱስ ሚካኤል በድንገት ተገልጸላቸው፡፡
    ቅዱስ ሚካኤልም በልጃቸው ሰውነት ላይ ስለተቀረጸው ኅቡእ ስም ሊተረጉምላቸው እንደ መጣ ነግሯቸው ዲካባ፣ ማርትያስ፣ ክስብኤል ማለት ‹‹አጋንንትን የሚያስር፣ ጠላትን የሚያርቅ›› ማለት ነው ብሎ ተርጕሞላቸው ተሰውሯቸዋል፡፡
    ወዳጆቼ በጸሎተ ቱላዳን ውስጥ ያሉትም ኅቡእ ስሞች አጋንንት የሚያስሩ፣ በእኛ ላይ ያላቸውን ተንኮል የሚሽሩ፣ መተት እና ድግምትን ከእኛ የሚያርቁ ፣ የሚዋጉንን አጋንንት የሚያስጨንቁ እና የሚያደቁ ናቸው፡፡
    ስለዚህ ኅቡእ ስሞችን ወለላይቱ እመቤት ድንግል ማርያምም ትጸልይባቸው ስለነበር ቅዱስ ዳዊት፣ ጥበበኛው ሰሎሞን፣ ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ ጸለዩት እኛም በጸሎተ ቱላዳን ውስጥ ባሉት ኅቡእ ስሞች ግር ሳንሰኝ በርትተን በመጸለይ አጋንንትን ልንዋጋ ይገባናል፡፡ ኅቡእ ስሞች በእግዚአብሔርና በቅዱሳን መላእክት የሚታወቁና የሚተረጐሙ ስለሆኑ ሳንሰለችና ሳንጠራጠር እንጸልያቸው፡፡
    #Mahtot_Tube #ቤተ_ቅኔ #Bete_Qene #Agape_Ze_Ortodox #ቀሲስ_አሸናፊ_ገብረ_ማርያም #ሃዲስ_ኪዳን_ዘኦርቶዶክስ_Zemare_Hawaz_Tegegne #ሐዲስ_ዜማ_ቲዩብ #Rama_tube #Samson_Negash #Mulken_Kebede #Zemenay_Gosaye_Official #Gashaye_Melaku #Zemarit_Tirhas #Tabor_ታቦር_Tube #Memher_Mehreteab_Asefa #Et_Art_media #Awutar_Tube #Quanquayenesh_Media #SeifuONEBS #Donkey_Tube #ቀደሜጸጋ_ሚድያ_Kedametsega_media #Feta_daily #zemarit_tsigereda_tilahun #zemari_solomon_abubeker #zemari_ezira_hailemichael #zemarit_hana_merawi #zemarit_zemena_ygosaye #zemarit_fekirte_feleke #zemarit_zerfe_kebede #zemari_tewodros_yosef #mezmur_ortodoxe #New_Ethiopian_mezmur #zemari_tewodros_yosef #zemari_chernet_senai #zemarit_mertnesh_tilahun #Etiopian_Ortodoxe_Mezmur #masiyas_tube #mestehaf_kidus #መዝሙር_ዘ_ኦርቶዶክስ #የጠዋት_ዝማሬዎች #አኮቴት_ቲዩብ #ፍኖተ_ጽድቅ #orthodox #መዝሙረ_ማኅሌት #የማለዳ_ዝማሬ #ምስጋና #medlot_media #መድሎት #nisebiho_mezmur #Mahbere_Kidusan #Eotc_Tv #Adugna_Zema #Chernet_Senai

ความคิดเห็น •