🔴አዲስ ዝማሬ-ማርያም የሚለው ስም zemari deacon Endale dereje
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 8 ก.พ. 2025
- #mezmur #ethiopia #subscribe #duet #religion
ማርያም የሚለው ስም
ላንቺ ካለኝ ፍቅር የተነሳ
አልውልም አላድርም ስምሽን ሳላነሳ
ፍቅርሽ በደም ስሬ ስምሽ በከንፈሬ
ድንግል ሆይ ይኖራል እየሆነልኝ ክብሬ
ዘወትር ይኖራል እየሆነኝ ክብሬ
.......
ምክንያት ስላረገሽ ጌታ በማዳኑ
ካንቺ ጋር ተሳስሯል ልቤ ቃልኪዳኑ
ላመስግንሽ ብዬ ቃል ከአፌ ባይወጣም
አለ በደም ስሬ ማርያም የሚለው ስም
......
ባልጸናው አእምሮ በልጅነታችን
ማርያም ጣታችን ነሽ መታረቂያችን
አሁንም ላደፈው ለጨለመው አለም
የእርቅ ሰነድ ነሽ የፍቅር የሰላም
.....
የእናትነት ፍቅርሽ እጅጉን ይደንቃል
የምህረት እጆችሽ ሁሌም ተዘርግቷል
የልቤ ናፍቆቱ አንቺ ነሽ ማርያም
ያደራ እናቴ ነሽ ካንቺ አልለይም
.....
ከፍጥረት በሚልቅ የመወደድ ግርማ
ነግሰሽ የምትኖሪ በንጉስ ከተማ
ማርያም ሰላማ ነሽ የክብሬ መገኛ
ድኅነትን ያስገኘሽ ለፍጥረት መዳኛ
ግጥም ዲያቆን ዘማሪ እንዳለ ደረጄ
ዜማ ዲያቆን ዘማሪ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)