ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን፣ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት ከቫቲካን ሜልቲ ሚዲያ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ክፍል አንድ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 3 ก.ค. 2024
  • በላቲን ቋንቋ (Ad limina apostolorum) በመባል የሚታወቀው በየአምስት አመቱ በመላው አለም የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ አባላት ወደ ሮም እና ቫቲካን በመምጣት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ የሚመለከት ሲሆን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው ከሀይማኖት፣ ከማህበራዊ እና ከባህላዊ እይታ አንጻር በመገምገም እና በመለየት የገጠማቸውን ተግዳሮት እና ልዩ ሁኔታዎችን ለማሳየት ታልሞ የሚከናወን ስብሰባ ነው። የኢትዮጲያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጓባኤ አባላት ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት በተመለከተ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን፣ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት ከቫቲካን ሜልቲ ሚዲያ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።

ความคิดเห็น •