ገድለ ተክለሃይማኖት አርባ ሰባተኛ ምዕራፍ
ฝัง
- เผยแพร่เมื่อ 3 ก.พ. 2025
- ሐዲስ ሐዋርያ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
#ተክለሃይማኖት ማለት ‹‹ የሃይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ›› ማለት ነው፡፡
#እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ #ሐዲስ_ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን #ተክለ_ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በ #ቅዱስ_ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀ ን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው
‹‹ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን
አምላክ አመስግነውታል፡፡ ወላጆቻቸውም ስማቸውን #ፍሥሐ_ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡
የቅዱስ አባታችን በዓላት እነዚህ ናቸው፡- መጋቢት 24 ቀን 1196 ዓ.ም ፅንሰታቸው፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ልደታቸው፣ ኅዳር 24 ቀን ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በሕይወተ ሥጋ እያሉ የሥላሴን መንበር ያጠኑበት ሲሆን ጥር 4 ቀን 1289 ዓ.ም ደግሞ በጸሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት ነው (ነገር ግን የዕረፍታቸውን ቀን ይዞ በዚሁ በጥር ወር በ24 ይከበራል)፣ ነሐሴ 24 ቀን 1296 ዓ.ም ዕረፍታቸው፣ በግንቦት 12 ቀን 1353 ዓ.ም
ፍልሰተ ዐፅማቸው ነው፡፡ ቅዱስ አባታችን በሞት ከማረፋቸው በፊት አስቀድሞ ጌታችን
እንደነገራቸው ሥጋቸው ከነፍሳቸው ከተለየች ከ57 ዓመት በኋላ የካቲት 19 በጸሎት ላይ ለነበሩት ለአቡነ ሕዝቅያስ ተገልጠውላቸው ‹‹ጌታ የገባልኝን ቃል ይፈጸም ዘንድ ሥጋዬ የሚፈልስበት ደረሰ፣ ቀኒቱንም በምስጋናና በጸሎት መንፈሳዊ በዓል አድርጉ፤ እኔ ኃጥኡ በሞትኩበት ቀን
እንደነበረው ምስጋና አቅርቡ፡፡ ሄደህ ለ12 መምህራንና ለልጆቼ ግንቦት 12 እንዲያከብሩ ንገራቸው፡፡ በፍልሰቴ ቀን አባቴ አባቴ የሚለኝ ሁሉ ይምጣ ያኔ እኔ፣ ወዳጄ ሚካኤልና
ልጄ ፊልጶስ አብረን መጥተን እንባርካለን፡፡ ምልክት ይሆንህም ዘንድ በምመጣበት ጊዜ የጠፋው የመቅረዙ መብራት ይበራል›› አሉት፡፡
ከዚህም በኋላ አቡነ ሕዝቅያስ በአባታችን ተባርከው ሄደው በአራቱም አቅጣጫ ላሉት 12 መምህራንና ለክርስትያኖች ሁሉ አባታችን የነገሩትን የፍልሰታቸው በዓል ስለማድረግ ወደ ፍልሰቱ በዓል ያልመጣም በዚያች ቀን (በሰማይ ለምልጃ) አባቴ እንዳይለው እርሱም ልጄ እንዳይለው ጨምሮ መልእክቱን ላከላቸው፡፡ እነርሱም ከያሉበት ተሰብስበው መጥተውየቅዱስ አባታችንን ሥጋቸውን አውጥተው ወደ ቤተክርስቲያን አፍልሰው 3 ጊዜ መቅደሱን አዙረው በዓሉንም አባታችን እንዳሉት በዝማሬና በምስጋና አክብረው ወደ ውስጥ አስገቡት፡፡ በዚህም ጊዜ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ተክለ ሃይማኖት አስቀድመው እንደተናገሩት ጠፍቶ የነበረው መብራት ቦግ ብሎ በራ፡፡ ከቅዱስ ሚካኤልና ከልጃቸው ከአቡነ ፊልጶስ ጋር በመሆንም በዓሉን ያከብር የነበረውን የተክለ ሃይማኖት የጸጋ ልጆቻቸውን ሁሉም ይባርኩ ነበር፡፡
ጸሎታቸውና በረከታቸው ረድኤታቸውና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያንና አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን!