betam yasazinale egna bekefelinew eko lelaw new eyetetekeme yalew lelawin titenew ahun ley ersu yekefelew sew bekiray eytesekay bet yelem beliw yeneberut lekoriden lemate letenesa hulu bet setachew ena Fatariy Yiylachew Betile 1997 Temezgabiy Tebdiluhal
Look the government always laying, laying, laying, what the hell?.., What the officer 'Ato Shimelis' said is thumps down. Anyways thank you for asked him even if he said nothing.
ከ97ጀምሮ ያለ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ ላይ የተሰራው ግፍ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው
ፍትህ ኮንዶሚኔም ቆጥበን ላልደረሰን እባካችሁ ፈጣሪን ፍሩ
ወንድሜ የአቶ ገብሩ በየነ ጥያቄ ብቻ አይደለም ለምሳሌ እኔ ልክ እንደ እሳቸው ነኝ የሆነው እና በጣም ነው ልብ የሚሰብረው በእውነት ፍትህ ፍትህ ፍትህ እንላለን 😢
ሸገሮች በጣም ተከታታያችሁ ነኝ ስፈልገው የነበረው ጥያቄ መልስ አገኘሁበት ጋዜጠኛው ከ❤ አመሰግናለሁ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ
ምኑ ነው የተመለሰው ??
ለአቶ ገብሩ በየነ ጥያቄ ሀላፊው የሰጡት መልስ ባጭሩ ይህ ነው....
"አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የቦንድ ብድር አቅርቦቱ ትንሽ እጥረት ስላለው እሱ እስኪፈታ ድረስ በምንፈልገው መጠን ብድር እያገኙ መገንባት ሊያስቸግር ይችላል ኢሄ ግን አይፈታም ማለት አይደለም ቀጣይ እኛም ያለብንን እዳ እየቀነስን ስንመጣና አጠቃላይ አሁን ያለው ችግር ሲፈታ የቦንድ አቅርቦቱም በዛው መጠን ሊመጣ ስለሚችል
እድሉን በዛው መንገድ እየፈታን እንሄዳለን ብለን እናስባለን።
አንድ ነገር መልስ የሚባለው የጊዜ ገደብ ሲቀመጥለት ነው። (ቢያንስ ወይ ቢበዛ ተብሎ)
ትክክል @@M_B401
ከነዚህ ሰወች ቤት ፈረሳ እንጅ ቤት ግንባታ አትጠብቁ
ኮንደሚኒየምኮ የቆጠበው ሌላ የሚገባበት ሌላ !!! እያወቅን አንሸዋወዳ !!!
ምናለ እንደኮሪደር ልማቱ ኮንዶሚኒየም ያልደረሰውንም በዘመቻ ብታጠናቅቁና ብታስረክቡ
የእኔ ጥያቀየም ነው በላፈው 2015ተስፋ ሰጥተውን ነበረ
በኛ በር የተሰራውን ለዘመዶቻቸው አደሉ በገበሬ ልጅ ስም ምድረ ካድሬ ወሰደው
የህብረተሰቡ ድምፅና የቅሬታ ፍች ታታሪና ታማኝ፣ የሬዲዮ ጣቢያ ነዉ ሸገር፣ ሁሌም ሸገርና ግርማን አንረሳም።
ቅስምም ልብንም ሞራልንም የሚሰብር፡ ምላሽ ነው፡ በአቶ ሽመልስ የተሰጠው።
ይህ ጥያቄ የሁላችንም ጥያቄ ነው እኔም 1997 ዓ፡ም እስትዲዎ ተመዘገብኩ እስከ 2005 ዓ፡ም እጅግ በጉጉት ጠበቅሁኝ እጣ አልወጣልኝም ።በ2005 ዓም የተሻለ አማራጭ 40/60 ምዝገባ ሲመጣ ከአቅሜ የተነሳ ባለ 1 ምኝታ ተመዘገብኩ 3 ጊዜ 40/60 ለእጣ ብቁ ሖኘ እጣ ውስጥ ብገባም አልደረሰኝም ። ከ1997 ዓም ወደ 2005 ዓም ወደ 40/60 የቤት ፕሮግራም የመጣነው ለምን አይታይልንም እኔ በግሌ የተሰማኝ ስሜት እጅግ ክባድ ነው እግዚ አብሔር ያውቀዋል ምክናያቱም በፊት ብቻየን ነበርኩኝ አሁን ግን ልጆች አሉኝ ትዳር አልኝ የግድ ባለ 1 ምኝታ 40/60 ያስፈልገኛል አቅም ያለው በማህበር ይደራጅ ሌላ አማራጭ አለ አቅም የሌለው ግን እጣው ይጠብቅ ተብሎ ነበር አሁን ቤቱ እየተገነባ አይደለም ምንሰማውም እጣ አይውጣም ያለውም ላልተመዘገበ ለልማት ተነሽ ወዘተ እየተሰጠ ነው እኔ በግሌ ተስፋየ እየጨለመ ነው 25 አመት በቤት ክራይ መሰቃየት ከባድ ነው ባልኝ አቅም ወይም ሙያ፡እውቀት አገሬን እጅግ ዋጋ ከፍያለሁ ማለትም በልማት በረሃ ለበረሀ እየዞርኩም ምግብ በለለበት ሙቀቱ በብዛበት ሳላማርር መኪና በማይገባበት 20 ኪሎ ሜትር በእግር እየተመላለስኩ ተራራውን ፡ቁልቁለቱ፡ ጫቃውን እያቆራረጥኩ ለረጅም ጊዜ ፊል በኩንትራት በመብራት ሐይል፡ በኢትዮ ቴሌኮም እና በሌሎችም ድርጅቶች በትጋት ሰርቻለሁ በኢትዮጲያ ባሉ ክልሎች ማለትም በደቡብ፡ በኦሮሚያ ፡በአማራ ፡በአፋር፡ በሶማሌ በሲዳማ እና በሌሎችም የገጠር ወረዳዎችና ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና ኔት ዎርክ ማስፋፋት በአዲስ አበባ እጅግ በርካታ የልማት ስራዎች ማለትም በኤሌክትሪክ ባቡር ፡በቴሌ በኮፐርም በፋይበርም ስራ፡ በመንግዶች የሰብቤዝና በኮብል ስራዎች፡ በውዳጅነት ፓርክ ስራ በተለያዩ የሙያ ስራዎች እስኪመረቅ ድረስ አሁንም ባለኝ ሙሉ አቅም ቀንም ማታም ከኑሮ አንጻር እየሰራሁም ኑሮውን አልቻልኩትም ምንም ሱስ የለብኝም ይህን ሁሉ ሰርቸ ግን መኖሪያ ቤት የለኝም እኔ የእድሜየን ከግማሽ በላይ ጨርሻለሁ ነገር ግን ልጆቸስ ለማን አቤት ልበል ማንም የለኝም ኢትዮጲያ ሀገሬ አይን ፡ጀሮ ቢኖራት ካደረግሁላት አንጻር መኖሪያ ቤት ትሸልመኝ ነበር። ይህን 8:34 ያቀረባችሁት ፕሮግራም ካለፈም ባየው ባየሁበት ሰዓት እያለቀስኩ ይህንን መልክት ለሚመለከተው አካል እድታስተላልፉልኝ በልዑ እግዚ አብሔር ስም እጠይቃለሁ። እግዚ አብሔር በእናንተ በኩል ስራውን ሊሰራ ይችላል። በእውነት ለናንተም ትልቅ በረከት ነ ው አመርሰግናለሁ።
በጣም ብዙ ቁጥር ባዶ ቤቶች አሉ በጣም ብዙ እኛ እየቆጠብንም የቤት ኪራይም እየከፈልን እንሰቃያለን እነሱ ይቀልዳሉ ብዙ ዝግ ባዶ እጣ ያልወጣባቸው ቤቶች አሉ ወገኖቼ 😢😢😢😢😢
በ2005 ስንመዘገብ በአምስት አመት ውስጥ ሁላችሁም ይደርሳችኋል ተብለን ነበር ያ ማለት ከስድስት አመት በፊት ሊሰጠን ስለሚገባ ቤት ነው እየጠየቅን ያለው
በጣም ትንሽ ሰው ነበር በዛን ግዜ የተመዘገበው። ከዛ በኋላ ግን በዘመድ እየሰገሰገሰጉ። ለሌላ ሰው እየተሰጠ ነው። ሌቦች ናችሁ።
እዎነት ነው 2005 ጀምረን እስካሁን እየቆጠብን ነው
የቆጠብነውን ተሰርቶበት ለልማት ተነሽ እና ለሌሎች ልማት ውለዋል።
ሚያሳዝነኝ በተስፋ እድሜዬን እየጨረስኩ ነው።
ያሳዝናል በጣም፡፡ ይህ መልስ አይደለም፡፡
የቤት እድል የለኝም ያለችም ልትፈርስብኝ ነው :: ፈጣሪዬ ሆይ እርዳኝ 😊
እግዚያብሄር ይፈርዳል
ይህ ጥያቄ በእውነት አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ ነው ፤ የኔ ጥያቄ ደግሞ ለየት ያለ ነው ፤ለምሳሌ 1997ዓ/ም ተመዝግቤ በ2005ዓ/ም ከባንክ ጋር ውል ተዋዋሉ ሲባል ፡ እንደ አጋጣሚ ሁኖ ችግገጥሞኚ ክፍለሐገር ደርሽ ስመጣ ምዝግባው ቅን አልፏል ብለው እንቢአሉ ይኸው እስከዛሬ በቤት ኪራይ እሰቃያለሁ ፤ግን አሁን ለአዲስ ተመዝጋቢዎች ፤ለሚለው ምን አማራጭ ነው የለን አመሰግን አለሁ። ግን መልስ እፈልጋለሁ
በጣም ጉበዝ ጋዜጠኛ ነኸ የሰዎን ችግር ተቀብለ እስከመጨረሻው እየተከታተልክ ማቅረብ የምትደነቅ ነኸ ይሄ የኮንደሚኒየም ጉዳይ ግን እነሱ የጀመሩት ፕሮጀክት ስላሎነ ቸል ተብሎ ይመስለኛል ይኸው እንደምናየው ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ነው
የኪራይ ቤቶች በአነስተኛ እናቀርባለን የተባለው የኪራይ ቤት በገንዘብ አይደል የሚሰራ የመለሰው መልስ በጣም በጣም ያማል ተስፋ የሌለው ንግግር ነው
አላገኘችም
2005የተመዘገቡ በተስፋ የተቀመጡ አሉ
የተመዘገብነዉ በ1997 ዓ/ም ነዉ ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ ለ 20/80 ገንዘብ እየቆጠብን ብንገኝም ምንም ዓይነት መፍትሄም ተሰፋም የለዉም. ኣንድ ጠባብ ክላስ ለማግኘት ከ 20 ዓመት በላይ መጠበቅ በጣም ያሳዝናል ያሳፍራልም. Anyway ህብረተሰቡ በግልፅ ሊነገረዉ ይገባል የሚመለከተዉ ኣካል ካለ ማለቴ ነዉ
ሽገር የ 7 መቶ ሺ በላይ ተስፈኞችን ጥያቄ በ መጠየቃችሁ እናመስግናለን! ወያኔ ይግደለን ! ወደድህነት ያሽቀነጠረንን ያሽቀንጥር ልን
በቆጣቢ ገንዘብ እየገነባን አይደለም አይባልም ገንዘብ ባንክ እስካለ ድረስ ተገልጋዬ መንግሰት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
ፈጣሪ የስራችሑን ይስጣችሑ??አቤት መፍተሔ መስጠት በጣም ያሳዝናል በልማት የሚነሱ ሰዎች ነበር እንዴ ኮንዶምኔየም የተሰራው እውነት መልካም አስተዳደር በዚሕ መንገድ ይፈታል።
የስልክ ቁጥራችሁ ስንት ነው
ፍትህ ለ1997ኮንዶሚኔም ተመዝጋቢዎች ያሳፍራል20 አመትሙሉ
@@GeaterthanMehmmed ወላሂ አው አላህ በዚህም በቀጣዩም አይመቻቸው 😔
ፍትህ ለ1997 ተመዝጋቢ
ስልክህን እንዴት ማግኘት ይቻላል
ይህ ጥያቄ በእውነት አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ ነው ፤ የኔ ጥያቄ ደግሞ ለየት ያለ ነው ፤ለምሳሌ 1997ዓ/ም ተመዝግቤ በ2005ዓ/ም ከባንክ ጋር ውል ተዋዋሉ ሲባል ፡ እንደ አጋጣሚ ሁኖ ችግገጥሞኚ ክፍለሐገር ደርሽ ስመጣ ምዝግባው ቅን አልፏል ብለው እንቢአሉ ይኸው እስከዛሬ በቤት ኪራይ እሰቃያለሁ ፤ግን አሁን ለአዲስ ተመዝጋቢዎች ፤ለሚለው ምን አማራጭ ነው የለን አመሰግን አለሁ።
ሸገር ባጠቃላይ የስልክ ቁጥር ሲናገር ሰምቼው አላውቅም። ለምን?
ግርማን አመሰግናለሁ
እስከ ዛሬ ይኖራል በሚል በተስፋ ስቆጥብ ነበር ።አሁን ከመላሹ እንደተረዳሁት ከዚህ በኃላ የኮንደሚኒየም ዕጣና እየተሰራም ያለ ኮንደሚኒየም ቤት እንደሌለ ነው።ስለዚህ አማራጭ መፈለጉ መፍትሔ ሆኖ እነሱ ያቀረቡ ት ግን አሁንም ዝቀተኛ ገቢ ላለው የማይሆን መሆኑን ሞክሬ ትቼዋለሁ።
ይህ የሁላችንም ጥያቄ ነው እኔም የ 97 ተምዝጋቢ ነኝ ግን ይኸው ምንም አላየንም እኛ ግን እየቆጠብን ነው !
ይሄ የኮንዶሚንም የመኖሪያ ቤት ጉዳይ በራሱ አንዱ የሀገሪቱ የልማት ፕሮጀክት መሆኑ ይታዎቃል ፣ግን መንግስት ልክ እንደ ጫካ ፕሮጄክት እና ኮሪደር እናም ሌሎች ፕሮጄክቶች ከፈተኛ ትኩረት ቢሰጠው መልካም ነው።በርግጥም ከተማው ውብ እንደሆነ ሁላ የሰው ልጅም ውብ መሆን እንዲችል።
ምን ማብራሪያ ሰጠ፤ አይሰጥም ነው መልሱ።
Betaaaaaam yasazenale
መልሱምንምየተለየነገርየለውምያውሁሌማምታታት
ይህ ጥያቄ የኔም ነው ። ከጉሮሮ እየነጠቀ የቆጠበ ብዙ አለን ለሰው ከሚያስፈልገው መሠረታዊ ከሆኑት ውስጥ ውሃ፣ ምግብ፣ መጠለያ፣ ልብስ ወዘተ የግድ ይላል ዋና ዋናው ቢሞላላን
በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 ተመዝግበን እየቆጠብን ያለን ሰዎች ምን ማድረግ ነው ያለብን መፍትሄውስ ምንድነው
በርቱ
የ70/30 ለመመዝገብ ለነባር 20/80ለነበርነዉ ለመክፍል አቅም ካለን ማለት aforaed ማረግ ከቻልን የት ነዉ መመዝገብ ያለብን
SELFISHE
ላም አለኝ በሰማይ...
አስተያየት ሲሰጣችሁ ዝም በላቸው ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ እነደሚባለው ነው ምንያመጣሉ ነገም አንሰጣቸውም እንደምትሉ እናውቃለን::
ይህ የሁላችን ጥያቄ ነው በ 97 የተመዘገብነው ግን ምንም የለም
2005 ተመዝጋቢ ነኝ ላይደርሰኝ ገንዘቡን አወጥቸ የቤት ኪራይ ከፈልኩ አሁን መመለስ ይችል ይሁን😢😢😢
መለሰ ነው ቀልደ የሚባለው😮😮
በ1997 ጀምሮ እየቆጠብኩ እዳውን ዘግቻለሁ ግን እስካሁን አልደረሰኝ ዳግ ኤርኬኖ የእጣ ቋት ውስጥ ገብቼ ነበር
በሙሉ የክፈለስ ????
ወላሂ አክስቴ 17 አመቷ እስካሁ ምንም በጣም ያሳዝናል እዴት ብላ እደገባች እኔ ነኝ የማቀው ሞትማ መኖሩ ጥሩ ነው ከ አላህ ዘንድ ታገኝዋለች 💔
😢😢😢😢😢😢ጌታን ብንጠብቅ የሻለን ነበር ሆሆሆሆ
2005 በእውነት ተመዝጋቢ ነን ግን እንደገናም በማህበር ብለው አደረጅተውን ነበር ግን ምንም አልተባለ እኛ በማህበር ይሰጣል ተብሎ እየቆጠብን ነው እንዲያው ምንድን ነው
ጥያቄውን አልመለሰም
ቆጣቢ በቆጠበው ቤት ለሌላው መስጠታችሁ በምን አግባብ ነው
Melsu gin algebagnm yegebaw sew yasredagn please ????
አቶ ሺመልስ የመለሱልን መልስ በሰው ቁስል እንጨት እንደመስደድ ይቆጠራል።
ምናለ በተቀመጥንበት የስራ ዘርፍ ለሕሊናችን ብንሰራ ዛሬ በእርሰዎ ባይደርስ በልጀዎ እንደሚደርስበዎ አይጠራጠሩ እኛ እኮ መብላት አናስብም ለቤት ኪራይ ብቻ ነው
ለልማት ተነሺ ሲሉ ትንሺ አያመዎትም???
በጣም የሚገርመው አመራሮች በተለይ በተለይ የን/ላ/ክ/ከ ከቡታጅራ ከአዋሽ ላሉ ቤተሰቦቻቸው የገበሬ ልጅ በሚል ሰበብ ሰጥተው ይዘውታል። ታድያ የኛስ ተስፋ እግዚአብሔር አይደለምን😢😢😢
የኔም ጥያቄ ነው ስደት የሄዲኩት ለሱ ነበር ከፈልኩ ግን የለም ብቻ ያሳዝናል ልጀን ጥየ ስደት የሄድኩት የቤክራይ መሮኝ ነበር ግን የለም አላህ የስራችሁን ይስጣችሁ በቂቃ😢😢😢😢😢😢😢
እኔ አርባ ስልሳ ባለ ሶስት መኝታ ነው
እንድ ሚሊየን ብር አርጌበት አለሁ ግን ወንድሜ ወፍ የለም ይገርማል
ኧረ ተቸግረናል😭😭😭😭😭 ተሰቃየን በቤት ኪራይ😭😭 ወይ የቆጠብነውን አላወጣን
ወይ ቤቱን አልሰጡን😭😭😭
2005እየቆጠብን እየጠበቅን ሰዉ አገር በሰበስን ገና በአዲስ መልክ የምትሉት 97እንካን አልጨረሳችዉም እና እኛም እንክዲ ተሶፋየለንም ማለት ነዉ አረበናታች የሰዉ አገር ደገመኝ 2005 ባለ3መኝታ ምንም ማረፋየለኝም የምጠብቀዉ ቤቱንነዉ😢😢😢😢😢 4:20 ዉ
ግልጽ አሰራር የለም፤ የተደራጀም በፍትሐዊነት አይደለም
በኮንዶምኔየም ቤት ጉዳይ ፍትህ ለኢትዮዽያ
የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተመዝጋቢው መስጠት ቢፈልግ መስጠት ይችላል ምክንያቱም ብዙ ፍላጎቶቹን እያሳካ መሆኑን ማየት ስለቻልን ። የትኩረት እና የእምነት ብሎም የፍላጎት ጉዳይ ነው ባይ ነኝ። መንግስት አሁን አይፈልግም አላመነበትም የሚል ህምነት ነው ያለኝ። እንጂም የአቅም ችግር እና የማድረግ የመስራት ችግር የለበትም መንግስታችን ።
የደረሰንን መቼ ጨርሰው አስረከቡንና ነው
ጎሽ የኔም ጥያቄ ነው ???? የ97 ተመዝጋቢ ነኝ ከኋለዬ የቸመዘገቡ ስንቱ ወሰደ አይይይይ
ኮንደሚኒየም አቅም ለሌላቸው ሰዎች ታስቦ እንደተጀመረ ነበር የምናውቀው። አሁን እየሆነ ያለው ሌላ ነው ያሳዝናል
betam yasazinale egna bekefelinew eko lelaw new eyetetekeme yalew lelawin titenew ahun ley ersu yekefelew sew bekiray eytesekay bet yelem beliw yeneberut lekoriden lemate letenesa hulu bet setachew ena Fatariy Yiylachew Betile 1997 Temezgabiy Tebdiluhal
የ40/60 ባለ2 ምኝታ ሙሉ ክፍያው ስንት ነው
10000000000000000
Me too please
ስልካችሁን ስጡኝ ጥቆማ አለኝ
የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው እውነት መረረን አሁንስ
ሽመልስ የሚባሉ ስሞች ቅፍፍ የሚሉኝ እኔን ብቻ ነው ?
Look the government always laying, laying, laying, what the hell?.., What the officer 'Ato Shimelis' said is thumps down. Anyways thank you for asked him even if he said nothing.
ይሄ የሁሉም ሰዉ ጥያቄነዉ
የሁላችንም ጥያቄ ነው እኔማ ደከመኝ በየወሩ አቆርጬ አላቅም በውነት የቤትክራይ ሂወቴን አመሰቃቀለው ተሰርቶ ለቤት ክራይ ደሞ እኳ ወሩ በመቼው እንሚደርስ አንዳዴ ከደሞዜ ቀድሞ የሚደርስ ይመስለኛል
እረ በፈጣሪ ይሁንባችሁ በልልን አባቴ መላ ይበለን
Foto tensto sechares bet lesera yechel yehonal gin feter teru mengest yametalin
የጋራ ቤቶች ምዝገባ በ1997 የተካሄደው ለልማት አገልግሎት ለገበሬ ቤተሰብ ና ለችግረኛ ይሰጣል የሚል በመመሪያ የተደገፈ አልነበረም በዓላማ ና በዕቅድ ተጀመረ የህብረተሰብ የቤት ፊላጎት መሠረት ማዕከል ማድረግ ሲናርበት ቅድሚያ ከፍሎ ያጠናቀቀ ጭራሽ ቅድሚያ አያገኝም መበሉ ትክክል አይደለም የቤት ግንባታ በ1997 ሲጀመር የወጣ መመርያ ተገናዝቦ ለህዝብ ችግር መፍተሔ መፈለግ አለበት ደሀ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ በግል ተደረጅቶ መሠራት የሚችል የለም መንግሥት አፈጻጸሙን መፈተሽአለበት
በኮንዶምኔየም ቤት እደላ ጉዳይ የኢ/ያ ህዝብ ሆይ ተስፋ ቁረጥ ለቆጣቢ አይሰጥም!!
😢አቶ ሽመልስ ሲመልሱ ብራችሁን በራሳችሁ አካውንት ነው የተቀመጠው መውሰድ ትችላችው ብለዋል ዶላር የከፈልን ዶላራችንን መውሰድ እንችላለን?
በጣም የሚያሳፍር መልስ 20/80 ና 40/60 ሳይሰሩ 70/30 ? ሊጠቅሙ ያሰቡት ማህበረሰብ እንዳለ ያሰታወቃል ደሞ ገንዘብ የለም ለኮሪደር ልማት ለ 90 ቀናት 33ቢሊዬን ያወጣችሁ ለመኖሪያ ቤት ሲሆን የላችሁም 😡😡😡ሰውየው ሲያብድ አብሮ የሚያብድ ከንቲባ, መከላከያ ሌሎች ሚንስትሮች ባሉበት ከዚህ በላይ አልጠብቅም!!
በህዝብ ገንዘብ ለወገናቸው እየሰጡ ነው ቤት አለ ግን ባለስልጣኖቹ ለቤተሰብ እየሰጡ😮😮
ተስፋችንን አጨለማቹት የገንዘብ እጥረት እያለብን ለሌሎች ሀገራት አበዳሪ መሆናችንስ እንዴት ይታያል
Me too, waiting since 1997 for 60/40.
እንዴት በኛ ገዘብ ተስርቶ ለተፋናቃይ ይሰጣል የኞገዘብ ኣቅም የቀነሰ ኣይደለም እንዴት
እግዚአብሔር የሥራችሁን ይስጣችሁ ይህን ህዝብ እንዳስለቀሳችሁ አትቀሩም .... የአዲስ አበባ ሰው ሆይ ንቃና መብትህን አስከብር:: አታላዝን::
ሰላም40/60 ስ መውጣቱ ቀረ
የቤት ልማቱን እየፋጠንን ነው ያሉት ትክክል አይመስለኝም የልቁኑ የሚያፈረሡትና የሚያፈናቅሉት ይበዛል
።።። ሸገር ኤፍ ኤም እባካችሁ።።ቁጠባ ምዝገባ ምዝገባ መቼ ይጀመራል ? ምዝገባ ። በኢሐዲግ ዘመን።።ቁጠባ በየቀበሌ ነበር።።አሁን ምዝገባው ሳይሰማ።።ምዝገባ አለቀ ይባላል።።ለምን በየቀበሌ በር ላይ አይለጠፍም።።።በሚዲያስ ለምን።።አለቀ ሳይሆን ተጀምሯል አይባልም ? እረወን ይሔን ጠይቁልን።።።።
ሁላችንም ተስፋ ቆርጠናል😢😢😢😢ብር ልናውጣ ነው ተስፋ የለንም
ማውጣት ይቻላል እንዴ
ሳይ ጨርሱ ነው ሚያ ድሉት እጥፍ ክፍ ያ በራስ ማሰራት ማለት ነው ። ፎቅ ያለ ሊፍት ውሃ መብራት ምን ይስ ራል ? በውጭ ሲታይ ያለ ቀ ይመስላል ???🤔🤔
2007 ዓ ም የተመዘገብን አድስ ተመዝጋቢወች አልተሰጠም ማህበራት የተባሉት ደግም የሌባ ማህበራት ናቸው ጤና ቢሮ ዳሸን ባንክ አለበት ተብሎ ነገር ግን ምንም የሰሩት የለም አንድ ዓመት 5ወር ምን እንደሰሩበት አይታወቅም !
የአዲስ አበባ ላዳ ተክሲወችን ጉዳይ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ብታቀርቡልን
ብሩን ቢመልሱልን ለመመለስም እኮ ወረፋ ነው ወይ ኢትዮጲያ የማፌያ ሀገር
አስቡት 1997ተመዝግበን በ2005 ጀምሮ ቆጥበን ይህን መመለስ አይከብድም ? ያሳዝናል ። ተመዝጋቢዎች በተመዘገቡበት መስተናገድ አለባቸው ምክንያቱም መንግስትን አምነን ?
በህገወጥ ና በኮሪደር ልማት ሰም የዜጎቹን ቤት በማፍረሰ እሰከ አሁን ከሶስት መቶ ሺህ ቤቶችን ካፈረስ ስርዓት ኮንዶሚኒየም ሰርቶ ይሰጠኛል ብሎ መጠበቅ ጅልነት ነው
20/80 ቅድማ ክፍያ ስንት ነው
ከኢትዮጵያ ውጭ በዶላር ከፍለው ጨርሰው ቤት ያላገኙ አሉ።
፨ ኢየሩሳሌም አረጉ ስመኝ የተባለች ዘመዴ ክፌያ ጨርሳ ቤት አላገኘችም። ከአረብ አገረ መጥታለች። የት ታመልክት?
እሽሩሩ እያለ ራቴን ሳያበላ እንደራበኝ የሚያስተኛ ምላሽ 😜... አይ ዘመን
40/60 Temezgabiwochis min Adis Ale kezik befit Derson yeteserezbns
😢are yenem endeza new aldersenm
አዲስ ምዝገባ አለ?