ወደ እግዚአብሔር እንመለስ | እህት ቤተልሔም | Sister Betelhem | | EAG 6 kilo | 2025

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 10 ก.พ. 2025
  • ርዕስ፦ወደ እግዚአብሔር እንመለስ
    የመጽ.ቅ.ክ ፦1 ነገስት 12፡25-33
    የእለቱ ሰባኪ፦ እህት ቤተልሔም
    1ኛ ነገሥት 12:25-33
    "ኢዮርብዓምም በተራራማው በኤፍሬም አገር ሴኬምን ሠርቶ በዚያ ተቀመጠ፤ ደግሞም ከዚያ ወጥቶ ጵኒኤልን ሠራ። ኢዮርብዓምም በልቡ፦ አሁን መንግሥቱ ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል። ይህ ሕዝብ በእግዚአብሔር ቤት መሥዋዕትን ያቀርብ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ቢወጣ፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ወደ ጌታቸው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ይመለሳል፥ እኔንም ይገድሉኛል አለ። ንጉሡም ተማከረ፥ ሁለትም የወርቅ ጥጆች አድርጎ፦ እስራኤል ሆይ፥ ወደ ኢየሩሳሌም ትወጡ ዘንድ ይበዛባችኋል ከግብጽ ምድር ያወጡህን አማልክቶችህን እይ አላቸው። አንዱን በቤቴል፥ ሁለተኛውንም በዳን አኖረ። ለአንዱ ጥጃ ይሰግድ ዘንድ ሕዝቡ እስከ ዳን ድረስ ይሄድ ነበርና ይህ ኃጢአት ሆነ። በኮረብቶቹም ላይ መስገጃዎች ሠራ፥ ከሌዊ ልጆች ካይደሉ ከሕዝብ ሁሉ ካህናትን አደረገ። በስምንተኛው ወር በአሥራ አምስተኛውም ቀን በይሁዳ እንደሚደረግ በዓል ያለ በዓል አደረገ፥ በመሠዊያውም ላይ ሠዋ፤ ለሠራቸውም ጥጆች ይሠዋ ዘንድ እንዲሁ በቤቴል አደረገ፤ ለኮረብታ መስገጃዎችም የመረጣቸውን ካህናት በቤቴል አኖራቸው። በስምንተኛውም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን በልቡ ባሰበው ቀን በቤቴል በሠራው መሠዊያ ላይ ሠዋ፤ ለእስራኤልም ልጆች በዓል አደረገላቸው፤ በመሠዊያውም ሠዋ፥ ዕጣንም ዐጠነ።"
    ኢዮርብዓምን የሾመው እግዚአብሔር ነበር
    ንግስናውን አጣለሁ ብሎ ስጋት /ፍርሃት/ ውስጥ ገብቶ ነበር
    ጣኦትን አሰርቶ ለእስራኤልም ልጆች በዓል አደረገላቸው፤ በመሠዊያውም ሠዋ፥ ዕጣንም ዐጠነ።
    እግዚአብሔር እንዲመለስ ነብይ ልኮበት ነበር
    እኛስ ምን እናድርግ?
    1. አንፍራ
    2. እግዚአብሔር አዋቂ መሆኑን እናስብ
    3. በቅድስና እንኑር
    4. ዋጋ ለመክፈል እንተምን
    5. ወደ እግዚአብሔር እንመለስ
    እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

ความคิดเห็น • 2

  • @KUMELEMU
    @KUMELEMU 26 วันที่ผ่านมา

    Be Blessed betishayeee, Amazing message!

  • @edlawitdejene620
    @edlawitdejene620 28 วันที่ผ่านมา

    ቤቲዬ ብርክ በይልን!❤