I agree with you, EPRP was the most brutal and dictator during the time. I was one of the member and have seen many bad things, when we struggled in the city of Addis we pushed many young generations to die for nothing, Those leaders on the top did many bullsheet, first of all The top leaders dying for power that's why they calculated the durg and killed many for nothing, EPRP was a criminal group lead by criminals, ክፍሉ ታደሰ, ተስፋዬ ደበሳይ and others were very fanatic communities but brutal and criminals, Sad to here today most of them feel that EPRP was Correct, another monster was ዘሩ ክሸን , and many more, during that time the ደርግ ወያኔ ሻእቢያ all killed the poor kids, Sad very Sad until today the goast followed us ,
Quite informative and honest discussion. This is what a true seasoned scholar should do. If you could ask him about his current suggestions for Ethiopia’s complex Political issues.
Its very important to here from an eye witness ( professor Alemante ) on the Meret larashu Rekik. Yet Andargachew Aseged questioned the role of participants on this particular issue. However, Eliyas mentioned the word "wishet" & the importancy of "truth". Since, truth or wishet are a relative words how come Eliyas can't see both (Professor Alemante & Andargachew Aseged ) statement as coreect on the issue. Perhaps Meison in South Ethiopia long before the rekik was relatively active ( Chilga & the role of Abera Yemane ab ). However, while Eliyas's effort must be appreciated, its not free of criticism.
ሰላም ኤልያስ እጅግ በጣም አክባሪህ ነኝ። እኔ የ40 ዓመት ጎልማሳ ነኝ። የደርግ መንግስት ስርዓትን ለፍስ አውቄ አላየሁትም።
ነገር ግን በዚያን ዘመን የተፃፉትን ሁሉም መፅሃፍት አንብቤያለሁ። ከንባቦቼ እንደተረዳሁት ኢህአፓ የተባለው ድርጅት ሰው በላ ሀገር አውዳሚ መሆኑን ነው።
አንተም ብትሆን ለድርጅቱ ወገንተኝነት አለብህ ይሄ ስህተት ነው። ቆሜለታለው ከምትለው እውነት ጋር የተጣላ ነው።
አመሰግናለሁ በጣም🙏🙏🙏
ልክ ልክ ነጋሪ አያሳጣን
ወንድሜ ፥ እኔ የታሪክ ተማሪ ነኝ
እዉነታዉ ይሄ ነዉ።
ምንም አትጠራጠር
እዉነታዉ ላይ በራስህ ተመራምረህ ደርሰህበታል
ኤሊያስ በትላንት ዉስጥ የሚኖር ሰዉ ነዉ
I agree with you, EPRP was the most brutal and dictator during the time.
I was one of the member and have seen many bad things, when we struggled in the city of Addis we pushed many young generations to die for nothing,
Those leaders on the top did many bullsheet, first of all The top leaders dying for power that's why they calculated the durg and killed many for nothing,
EPRP was a criminal group lead by criminals, ክፍሉ ታደሰ, ተስፋዬ ደበሳይ and others were very fanatic communities but brutal and criminals,
Sad to here today most of them feel that EPRP was Correct, another monster was ዘሩ ክሸን , and many more, during that time the ደርግ ወያኔ ሻእቢያ all killed the poor kids,
Sad very Sad until today the goast followed us ,
እጅግ ድንቅ ምሁር በሀቅ ለሀቅ የኖሩ ፕሮፋሰር ዓለም አንተ ገ/ ሥላሴ ታሪክን ለባለ ታሪኩ ለማስረከብ ላደረጉት ጥረት ዘለዓለማዊ ክብር ይገባዎታል ።
We havevto salute him
ኤልያሰ ግሩም መጠይቅ ነው የዓለምአንተነህ ታሪክ የኢትዮጵያ ታሪክ ለጥረት አመሰግንሃለው በርታ አንድቀ ሰለቄርቆሰ እናወራለን
ሁለቱንም ክፍል ተከታትያለሁ፤ በጉጉትና ሳልሰለች ነው የተከታተልኩት። ዶ/ር ዓለምአንተ ጨዋ ሚዛናዊ አስተዋይና እውነቱን የሚናገሩ እንደሆኑ ለመረዳት ችያለሁ። ኤልያስ፥ ለአንተም ለዶ/ሩም ትልቅ ክብር አለኝ። ለእውነት የምታደርገውን ተጋድሎ አደንቃለሁ። እግዜር ይስጥልኝ!
Thank you Mr. MESION F
በጣም ተመሥጨ ነው ያዳምጥኩት ፣ ሥለ ኢህአፖ በሚገልፁበት ክፍል እኔ ያደኩበት አካባቢን ሢገልፁት ስለነበር በትግል ሥሙ ዮሐንሥ የሚባል የኢህአፖ አባል የሚያውቁት ይመሥለኛል፤ እዚህ አሜሪካን ሀገር እንደነበርም ሠምቻለሁ። ፕሮፌሠሩ የሚያውቁት ከሆነ ብትጠይቅልኝ ደሥ ይለኛል። ሌላው መፅሐፉን Amazon በኩል ለገቢያ ቢያቀርቡት በቀላሉ ማግኘት ና ማንበብ እንችላለል።
Thanks Sir for your honest well articulated interview.
ለፕሮፌሰሩ ሰፊ እድል ስጥልን ጋዜጤኛው እዬባረክ ጊዜ አትግደልብን
የአንተ ኳሊቲ እኝህን ምርጥና ሀቀኛ ምሁር ማቅረብህ ነው።
በጣም አስተማሪና አይን ከፋች ውይይት ነው።
እባካችሁ መፅሀፉ በአማዞን እንዲሰራጭ አድርጉ።
ሁለታችሁንም ዕድሜና ጤና ይስጥልን🙏
Elias you were great active listener today!
Quite informative and honest discussion. This is what a true seasoned scholar should do. If you could ask him about his current suggestions for Ethiopia’s complex Political issues.
We want to hear from people like this gentleman. We thank him very much!
Thank you professor
የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ።
ማቴዎስ 4:17
እባካችሁ ከዘላለም ሞት አምልጡ!
መጽሐፍ ቅዱስ አንብቡ
እያንዳንዱ ምዕራፍ መፀሐፍ ሊሆን የሚችል፣ በታማኝ መረጃዎች የታጨቀ ሰነድ ነው። በምእራቡ ዓለም በከፍተኛ የስልጣን እርከን ያገለገሉ መሪዎች ለህዝባቸው ከሚያጋሯቸው unclassified የግል ማስታወሻ የአቀራረብ ዘይቤ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
ይህ ትውልድ ሊማርበት የሚገባ ስራ በመሆኑ፤ የቻለ ሁሉ መጽሐፉን ቢያነብ አትራፊ ነው። ፈጣሪ ለፕሮፌሰር ረዥም እድሜን ይስጥልን። ለጋዜጠኛ ኤልያስም እንደዚሁ።
የበጌምድርን ታሪክ ያጫውቱን
ይህን ዝግጅት አሁን እያየሁ ነው። ከማስታውሰው: በየካቲት 25 ቀን 1967 አዋጁ ከመታወጁ አንድ ሶስት ቀናት አስቀድሞ የመሬት ይዞታ ኤክስፐርቶች ወደ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ መጥተው ስለመሬት ለአራሹ አዋጅ መግለጫ በሰጡ ጊዜ ከመጡት ኤክስፐርቶች አንዱ አቶ አነዳርጋቸው አሰግድ ነበር። ኤክስፐርት ሆኖ መጥቶ ነበር ስል ግን አዋጁን በማርቀቅ ላይ ተሳትፏል ማለቴ አይደለም። አላውቅም።
......so what is the point here ?
የንጉሡ ዘመን የታክስ ስርዓት በጣም ገራሚ ነው በአውነት ያስርዓት አስካሁን ቀጥሎ ቢሆን በታክስ ስርዓት አንቱ በተባልን ነበር ያራሳችንን አስጠለውን የፈርንጅች ኮራጅ ሆንን ::ያ ትውልድ ግን ለኔ የተረገመ ነው ቤተስብን አና አምነቱን ያረከስ ያደሀየ ነው ይባስ ብሎ ያ ክፉ ሥራቸው አሳካሁን ተከትሎን የሚመሩን መሪዎች ቤተክርስቲያን አንደትላት ቆጥረው ባለ በሌለ አይላችው የማዳከም ሰራ አየተሰራ ነው ይህን ችግር የሚያውቁ ጥላቶቻችን የ 100 ዓመት የቤት ሥራ የሰጡን
It was a very nice presentation, I know Alemante or Gebeyehu....
ሲጀመር ጎንደር ጠባብ አሰተሳሰብ ያለው የዘመኑ ወጣት በፍጹም አልነበረም።
What an humble man
ያለ ጨርቆስ መቼም እንግዳ አታቀርብም ጨርቆሴ ናቸው⁉¡ ካልሆኑ ጎብዘሀል ማለት ነው ከከረጢትህ ወጥተሀል ማለት ነው¡‼¡
የሱፍ አበባ በደራሲ ሀብታሙ አለባቸው የተጻፈው መጽሐፍ የትውልዱን ጥንካሬ እና ድክመት በዝርዝር ያቀረበ ሆኖ ይታያል፡፡የፕሮፌሰር ዓለም አንተን መጽሐፍ ተገኝቶ አስኪነበብ በውይይቱ የተነሱ ጉዳዮች በተከታታይ መቅረባቸው መረጃ ይሰጣሉ፡፡በተለይ የወቅቱን የፖለቲካ ትግል ሂደት ለመረዳት ፍላጎት ላለው ዜጋ በወቅቱ ተሳታፊ ሆነው በሕይወት ከሚኖሩ የተለያዩ ሰዎች በመጽሐፍ ወይም በቃለ-መጠይቅ መረጃዎች መቅረባቸው ጠቀሜታው ዘርፈ ብዙ ነው፡፡የፕሮግራሙ አዘጋጅ እና ፕሮፌሰር ዓለም አንተ አመሠግናቸዋለሁ፡፡የዛ ትውልድ የትግል ታሪክ ይመስጠኛል፡፡
የዛገ ትረካ ምፅ ምፅ
Elias where do we find the book? also the other book you showed us "ሸክም ቢቀል" ?
This was the real issue problem posed by the petty bureaucrats of the day. Initiating law and implementing are different as one commentators wrote.
ፕፊሰር የጠለምትን ታሪክ ያጫውቱን
ኤልያስ በእውነቱ ይህን የሀቅ ሚዛን የሆነ ሰውዬ ለኢትዮጵያዊያን በማስተዋወቅህ ምስጋና ይገባሃል።
ፕ/ር ዓለምአንተን በደንብ አውቀዋለሁ፣ በምላሱ ጨው አይማማም የሚባል ሀቀኛ ሰው ነው።
ኢትዮጵያችን ብዙ እንደ ዓለምአንተ ዓይነት ሀቀኛ ሰዎችን መጠቀም ባለመቻላ ነው አሁን ከደረስንበት ውድቀት የደረስነው።
ከቻልህ መቶ አለቃ አያልሰው ደሴን (ከአስመራ አሲምባ ክፕገቡት አየር ወንዶች) አንዱ ነውና ኢንተርቢው ብታደርገው መልካም ነው።
ስለ እኒያ እንቁ አየር ወለድ ሁኔታም ማወቅ ስለምንፈልግ ኢንተርቢው አድርግልን።
የፕ/ር አለምአንተም የቅርብ ጋደኛው ነው።
አመስፕግናለሁ።
😂😂😂ዛሬሞ ትባላላቹ አሸነፈና አቸነፈዋች አረ ለቀቅ አድርገን ይህን ነብሰ በላ ትዉልድ አታቅርብብን ያሳፋራሉ በጠቅላላዋቹ የመገዳደል የመጠላላት ደም ጠጪ ሀገር አዉዳሚ ትዉልድ አታቅርብ ቢቻል ታድነዉ በታሰሩ 🎉🎉🎉🎉😢
አድኖ ማሰር ያልካት ደርግ ደርግ ወይም ወያኔ ወያኔ ትሸታለች ፤ የገዳይና የገራፊ አባቶችህ ደም እንዳለህ ያስረዳል ፤ ካልፈለግህ አትስማው ፤
ኮለኔል እምሩ ወንዴ የመጀ መሪያ የክቡር ዘበኛ ኮርስ ሲሆኑ በመጨረሻም የባሕር ሀይል ምክትል አዛዥ የሪል አድሚራል እክድር ደስታ ምክትል ነበሩ
አቶ አንዳርጋቸዉ በእርጅናም ከዚያ እራስን ከፍ የማድረግ የጉራ በሽታ አልተላቀቁም፡፡
ማርቀቅን በሁለት መንገድ መረዳት አይቻልም?
አንደኛው መርሁንና ድንጋጌዎቹን የመዘርዘሩ ጉዳይ ሲሆን ፡ ሁለተኛው ደግሞ እነዚህን ድንጋጌዎች በሕጋዊ ቋንቋ የመጻፉ ቴክኒካዊ ሥራ ነው ።
የአቶ አንዳርጋቸውን አስተያየት በዚህ መንገድ ብንረዳው ውዝግቡ ይረግባል ።
ተባረክ
የሚገርምህ አቶ አንዳርጋቸዉ አሰግድም የጻፈዉ በዚህ መንፈስ ነዉ።
አብዮታዊ ምሁራን በሙሉ ተሳትፈዉበታል በሚል ነዉ ሁሉንም የዘረዘረዉ
ኤሊያስ parochial የሆነ
ዛሬም ባገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ የመኢሶን ሰዎችን ለማቃለል ሲሞክር የሚቀል ሰዉ ነዉ
What an arrogance from a nonsense EPRP symphatizer
Do you remember Tegegne Desta of Gamo gofa province ? who hired him you or Ato Zegeye?
ፕሮፌሰር ዓለም አንተ ገብረሥላሴ እስካሁን ያቀረቡትን ቃለ ምልልስ ተከታትየዋለሁ እጅግ ድንቅ የማስታወስ ችሎታ ያላቸው የእድሜ ባለፀጋ ናቸው በተለይ ዛሬ ያቀረቡት ኢህአፓ በጎንደር ክፍለ ሃገር ካድሬዎችን በማደራጀት እኒህ ካድሬዎችም በህቡዕና በግልፅ ሕዝብን በማደራጀት ድርጅቱ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ እንዲያገኝና የኢሕአሠ የጀርባ አጥንት እንዲሆን አድርገዋል
እንዲሁም የኢትዮጵያ ሐገር ወዳድ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት / ኢሐወዴድ/ ምስረታንም የተናገሩት ትክክል ነው ይህ ድርጅት የተመሰረተው ታች አርማጭሆ ፉጨና ማሪያም ከተባለ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲሆን እሳቸው እንዳሉት በጎንደር ክፍለሀገር በነበሩ የሰባቱም አውራጃዎች ህዝብየተሰባሰቡበት የድርጅት ምስረታ ነበር እሳቸው እንዳሉትም ኮሎኔል እምሩ ወንዴ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ኮሎኔል አስናቀ እንግዳ ምክትል ሊቀ መንበር ሁነው ተመርጠው ወደ ሱዳን እርዳታ እናሰባስብ ብለው እንደሄዱ ምንም እርዳታ ሳያገኙ በዚያው እንደሄዱ ቀሩ ኢህአፓም በ1972 ዓም በአርማጭሆና በጭልጋ ዳዛ ከፊውታራሪ አየለ አባጏዴ ጋር የነበው የፓርቲው አመራርና ሠራዊቱ የእርማት ንቅናቄ ጉባኤ እናደርጋለን በማለት ከኢትዮጵያና ሱዳን ጠረፍ ቲሃ ከተባለ ቦታ ከተሰባሰበ በኃላ ሠራዊቱ ጉባኤውን እንጀምራለን ብሎ በጉጉት እየጠበቀ የፓርቲው አመራርና የሠራዊቱ አመራር ጉባኤ ለማድረግ ሠራዊቱ ትጥቅ መፍታት አለበት በባዶ እጅ ሁነን ነው ጉባኤ የምናደርገው በማለት ታጋይ ሠራዊቱን በማታለል ትጥቁን አስፈታው ትጥቁን ካስፈታ በኃላ ግን ደርግን ታግለን ማቸነፍ አንቺልም የፈለክወደ ሱዳን ተሰደድ የፈለክ ወደ ደርግ ሂደህ እጅ ስጥ በማለት በስንት መስዋእትነት የተገነባውን ሠራዊት አፍርሰው ወደ ሱዳን አሰደዱት የታጋዩን መሳሪያም መሬት ቀብረውት ሄዱ ከዚያ በኃላ ኮሎኔል አስናቀ እንግዳ ሱዳን የነበረውን የኢሕአፓ አመራርን በማነጋር ትጥቁ መሬት ተቀብሮ ከሚቀር አሁን ሕዝቡን እያታገሉ ለሚገኙት ለላይ አርማጭሆ የጦር መሪ ለሻለቃ /ቀኝ አዝማች/ በሪሁን ገብረየስ 2ኛ/ ለታች አርማጭሆ የጦር መሪ ለሻለቃ ዘለቀ ጀንበር 3ኛ/ ለሻለቃ ደሴ አያልነህ የጫቆ አዳኝ አገር የጦር መሪ ቢሰጣቸው ያላቸውን ታጋይ አስታጥቀው ድርግን ይታገሉበታል ካሁን ቀደምም ኢህአፓ ወደ አርማጭሆ ከመግባቱ በፊት ህዝቡን እያስተባበሩ ደርግን የተዋጉ ጀግኖች በመሆናቸው መሳሪያው ለነሱ ቢሰጥ ይሻላል ብለው ሃሳብ አቀረቡ ከፊሉ አመራር መሳሪያው ከተቀበረበት ወጥቶ እንዲሰጥ ቢስማማም ከፊሉ አመራር ግን መሳሪያችን ለአርማጭሆ ሕዝብ አንሰጥም ብሎ አሻፈረኝ በማለቱ ኮሎኔል አስናቀም መሳሪያውን እንሰጣለን ካለው አመራር ጋር ለብቻ በመነጋገር ካስፈቀዱ በኃላ ለሻለቃ /ቀኝአዝማች/በሪሁን ገብረየስና ለሻለቃ ዘለቀ ጀንበር አስቸኳይ ደብዳቤ በመላክ ቲሃ እስከተባለው ቦታ ጠንካራ ታጋዮችን ልካችሁ መሳሪያውን እንድትረከቡ ሲሉ በጥቅምት በ1973ዓም ደብዳቤ ላኩ በደብዳቤውም መሰረት ሻለቃ/ ቀኝአዝማች/ በሪሁን ገብረየስና ሻለቃ ዘለቀ ጀንበር ታጋዮችን አዘጋጅተው ላኩ ታጋዮችም አደገኛውን የጥቅምት ወራት የሳምንት የእግር ጉዙ አድርገው ቲሃ ከተባለው የሱዳን ድንበር ደረሱ ነገር ግን ያልታሰበ ሁኔታ ተፈጠረ ይኸውም ትጥቃችን ለአርማጭሆ አንሰጥም ያለው ቡድን መሳሪያው እንደሚሰጥ ቀድሞ በማወቁ ለሱዳን ሰራዊት የተቀበረበትን ቦታ በማሳየት መሳሪያውን ለሱዳን አስረከበው ኮሎኔል አስናቀና መሳሪያውን የሚያስረክበው ቡድን መሳሪያው ከተቀበረበት ቦታ ሲደርሱ መሳሪያው ተወስዶ ባዶ ጉድጏድ አገኙ እነሱም አዝነው ለተላከውም የአርማጭሆ ታጋይ ሁኔታውን አስረድተው ወደ ሱዳን ተመለሱ የአርማጭሆ ታጋይም ወደ ቦታው ተመለስ
እንግዲህ እንደዚህ አይነት አመራሮች ናቸው ህዝብ መሳሪያውን እንዳይታገልበት ለሱዳን የሸጡት
የሕግ ትምህርት ቤት ጓደኛ አቶ ተሰፋ አያና ያስታውሱታል ወይ እቲ ትንሸ ማብራሪያ ይሠጡበት
መግቢያውን አታንዛዛው።
ኤልያስ ትመሰገናለህ,,, ድንቅ ቆይታ
Editors: ሰው ምስጋናውን ጥንቅቅ አድርጎ ሳይጨርስ አትቁረጡ፥፥ደካማ ኤዲተር አትሁኑ፥፥
Its very important to here from an eye witness ( professor Alemante ) on the Meret larashu Rekik. Yet Andargachew Aseged questioned the role of participants on this particular issue. However, Eliyas mentioned the word "wishet" & the importancy of "truth". Since, truth or wishet are a relative words how come Eliyas can't see both (Professor Alemante & Andargachew Aseged ) statement as coreect on the issue. Perhaps Meison in South Ethiopia long before the rekik was relatively active ( Chilga & the role of Abera Yemane ab ). However, while Eliyas's effort must be appreciated, its not free of criticism.
ኤልያስ :- አንተ የፈለግኸውን እያጣመምክን ለኢህአፓ ወገንተኛ እየሆንክ መለስ ዜናዊና አብይን እየጠላህ ነው የምታቀርበው። እግዜር የለሽ ኢህአፓ ሆነህ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አክራሪ አማኝ በመምሰል እንዲያውም ሌላውን እምነት የምትጠላ መሆንህ ለምንድር ነው ⁉️
ስለቤተ ክርስትያን መሬት ስታስቡ ስለ እስላም መስጊድ ቦታስ አስባችሁ ነበር?
ፐሮፊሰር ሀቀኛ ሰው ነው። ኤልያሰ እንግዳው በፍፁም ያላለውን እንዳለ በጥቅስ በርስትነት መጠቀሙ ወንጀል ነው። ኤልያስ እንግዳው ፖርቲውን አምርሮ እንዲያወግዝለት ጥሯል ግን የተሳካለት አይደለም።
የመሬት አዋጁ የኢትዮጵያን ህዝብ ገበሬውንም ጭምር ከግለሰብ ጭስኝነት ወደ መንግሥት ጭሰኝነት ያደረገና የመሬትን የግል ይዞናነትን ያላረጋገጠና የኢትዮጵያን ህዝብ መንግሥት በየጊዜው ለልማት እያለ ከኖረበት እያፈናቀለ ና ከፊውዳል ወደ ባለሃብት የመሬት ባለቤትነት ያመቻቸ ፣የኢትዮጵያን ህዝብ ያዋረደ አዋጅ ነው።መደረግ የነበረበት ገበሬው የሚያርሰው መሬት የግሉ ሆኖ የማንም ጭስኛ ሳይሆን የመሬቱ ባለቤትና ምሽት መለወጥ ቢፈልግ በግሉ በግዜው ገበያ ዋጋ መሸጥ መቻል ነበረበት።ግለሰብም ቤት ስርቶ የሚኖርበት የግሉ መሬት መሆን አለበት ። የቀረው መሬት በሙል የመንግስት መሬት ተብለው መታወጅ ነበረበት።
አቤት አፍቅሮተ ያ ትዉልድ!!! አቅራቢዉ ሌላ ዘመን ሌላ ትዉልድ ያለ አይመስለዉም።ይገርማል።
Please ask how EPRP was hijacked by ELF and who were its agents?
አቶ ኤልያስ መኢሶን ላይ ፍትሀዊ አይደለህም፣ በተደጋጋሚ አይቼሀለዉ ይህ ትክክል አይደለም።
መኢሶን የደርግ ቀኝ እጅ ከመፈክር መጻፍ እስከ ለደርግ ፓርቲ አወቃቀር ተግቶ የስራ በመጨረሻም ደርግ የበላቸው
@ahmed-em8nt ቢያንስ የከተማ ትጥቅ ትግል ብሌ ለስልጣን ብሎ ትንታግ የኢትዮጵያን ልጆች አላስፈጀም!!!!!!!
@ahmed-em8nt እራሱ ኢህአፓ ስንቱን የሀገሬን ልጆች ሰለቀጠ
ኢህአፖ ባይኖር ደርግም እዛ ጋር አይደርስም ነበረ።
Of course ወገንተኛ ነህ
አቶ ኤሌያስ ፥ አቶ አንዳርጋቸው አሰግድን ያስተናገደችዋን ልጅ መሰለኝ..
የጋዜጠኝነት ልምድ ልጅቷ ስለሌላት እንጂ.... ስትል በጣም አስገርሞኛል
አንተስ ?
The Sun የሚባል በእንግሊዝኛ የሚሰራጭ ጋዜጣ አዘጋጅ እንደነበርህ አዉቃለሁ
አሁንም ድረስ በ par-time ቢሆን ከጋዜጠኝነት ጋር የተያያዘ ሥራ ትሰራለህ... ቢሆንም
ጋዜጠኛ ግን አይደለህም
መምሰልና መሆን ለየቅል ነዉ
Journalism is more than a profession.
እዉቀትና ክህሎቱን ማደብር ብቻ አይበቃም፤
ሀቀኝነትን ፣ ሚዛናዊነትን ፣ ፍትሃዊነትን
የስብዕና መገለጫ እስኪሆን ድረስ መላበስን ይጠይቃል
ከባዱ ፈተና ተዚህ ላይ ነዉ
ወልደ ሩፋኤል ተወልዴ የአውራ ጎዳና ባለሥልጣን ፕላንኒንግ ዲፓርትሜንት የነበረ ኤርትራዊ፡ ዲሲ የነበረ፡ ካወቃችሁ አደራ አንድ በሉኝ። ስጦታ መኰንንስ?
እዚህ ጋር ደሞ አቶ አለም አንተ ካነሳቸው የአርቃቂ ኮሚሽኑ አባላት ውስጥ አቶ ጣእመ በየነ ሲጠቀስ አቶ ሰለሞን ጋሻው አልተጠቀሰም ዞሮ ዞሮ ሁሉም በግዜ ሂደት ይጠራል ችግር የለውም በዚህ አጋጣሚ የአቶ አለምአንተን የማስታወስ ችሎታ ልበለው ተሰጥዖ ሳላዳንቅ አላልፍም
ለመረጃህ ያህል
ጋንታ 44 አቶ ዓለም አንተ አስምባ በደረሰ ጊዜ active ነበር።
በግንቦት 1969 በእርማት እንቅስቃሴ ጊዜ ነዉ የፈረሰዉ።
ራሱ አቶ ዓለም አንተ አብሮኝ ይተኛ የነበረ አሉላ በጀርባዉ መተኛት እስኪያቅተዉ በጋንታ 44 በጋለ ማጭድ ተጠብሷል ፤
አስማማዉ ኃይሉም በማጭድ ተጠብሷል ብሎ ለርዕዮት ዓለሙ ተናግሯል እኮ።
አሁን ደግሞ በዚህ ጉዳይ አልነበርሁም ፤ አልሰማሁም ይላል...
ጠያቂ ይመርጣል እንዴ?
ፕሮፌሰር ዓለም አንተን አውቀዋለሁ። የሚታማው እውነት እና መክንያታዊነት ያበዛል የሚል ነው።
አንዳርጋቸው አሰግድንም አውቀዋለሁ። እውነተኛነው በሚል ጠባይ አይታማም ።
ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዳአርጋቸው ጋር የተዋወቅነው በርሊን ሲሆን ታዮ ከሚባለው ጓደኛው ቤት ተገናኝተን ስለ አፄ ኃይለሥላሴ መንግሥትሁኔታ ተወያይተናል። በዚህ የቢራ ውይይት የአንዳርጋቸው አሰግድ ፋከራ ጣራውን ሰንጥቆ መውጣቱ ትዝ ይለኛል። በዚህ ፋከራው አነዳርጋቸው አሰግድ “ የኃይለ ሥላሴ ን ባለሥልጣኖች ሆድ ሆዱን በሳንጃ ማለት ነው ሲል፣ እኔ በቁጣ ኢትዮጵያን የሚአጠፋት እንዳንተ ያለ ሰው ነው ማለቴ ትዝ ይለኛል።
እንዳርጋቸው በመግድል የሚአምን አክራሪ ሰው እንደነበር ተገንዝቤአለሁ።
የሚገርመው ግን እንዳርጋቸው የአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመድ እና ከሀብታም ቤተሰብ ከመሆኑበተጨማሪ እሱ እንዳሰበው ብዙዎቹ የአፄ ኃየለ ሥላሴ በለሥልጣኖች አጎቱ የሀረሩ እንደራሴ ደጃዝማች ወርቅነሀ ጭምር በደርግ ተረሸነዋል።
ጋዜጠኛው ኢሕአፓን ለማራከስ አትሩጥ። ቀፋፊ
Much ado about nothing. Besides, once you say that Andargachew was "deceitful" what kind of clarification are you looking for?
አቶ ዓለም አንተ ፥ በሰሚ ሰሚ እነ አቶ ኃይሌ ፊዳ ዘንድ ስለተደበቀ አንድ ግለሰብ በመጽሐፉ ላይ ጽፎ ስለ ኢሕአፓ የቶርቸር ጥፋትና ስለ 14 ታጋዮች ግድያ አለመጻፉ ይገርማል
bozene
.......please show some civility towards educational activities !
አሁን ገና ውይይቱ ትርጉም እየሰጠ መጣ!!! የአብይትና የጦርነት ( WR) አንድነትና ልዩነት እየተገለጠ ነው። Unfolding the real Eway Ethiopian Revolution is happening right now. አቶ አልያስም ጎንደረ ነህ መሰልኝ ከሆንክም እሰየው ትንሽ ስለ ጎንደር ላክልበት። ጠዛ የሃይለ ገሪማ ፊልም ካየሁ በሃላ ስለ ጎንደርና አብየተኞት አወቅሁ እሱም 44 ከ ዘንዶ ጋር አነፃፀርኩ። ፕ/ሮ አለም አንተ 44 ታቦት በጎንደር አልነበርም እያለ መሰለኝ? እውነት ነው ካልሆነ ክፍሉ ስለ አለማንተ ሲናገር ወይ ሲመሰክር ስልጣን ይወዳል ይላል። ስለማንኛውም ከጎንደር በግል ጀግና የነበረ የለም። አለም አንተ ከዮናስ አድማሱ ጋር እናነፃፅረው
Alem already was a minister : how can he be after power 😢
አቶ ኧልያስ ብዙ ስሞችን እየጠቃቀስ ምሁር ወይም አብዮተኛ ለመሆን ባትሞክር ጥሩ ነበር፥
ኧረ አታቆራርጠው
ጋዜጠኛው አንዳርጋቸውን በተመለከተ በጣም ባያዝድ ሆኖል
አቃጣሪ ግም