Woooow, unbelievable. All Glory to God my brother. I am just in awe...oh Hallelujah. Am glad God helped u to follow his Spirit. All this times I have been going back home, I have never visited this churches- and I thought something was wrong with me- Thank you Jesus for saving me! 🙏
Eunte new Hanicho seliya new nesa yewotawu keza bohala new bare tekefito keza bohala wode Canada 🇨🇦 wotawu Hanicho sega yechemiri yene wudi nurilgen 😍😍💜
Wow...never expected this. Thank you for bringing it to the light. Our desperation will take us to the darkness...my brothers and sisters Christ is enough ere....nothing else.
Wow Amazing testimony the holy sprit is the only true sprit God bless you my dear sister God bless all we need discerning sprit God is so Good and great
Wow የሚደንቅ መልእክት ። እኔም አንዲት ሴት የታምራት ደምስስ የፀለየበት ዘይት ነው ብላ ሰጥታኝ ነበር ። እኔ ክርስቲያን ነች ብዬ አምኛት እውነት መስሎኝ ተቀብያት ወደ ቤቴ ይዤ ሄድኩኝ ። አንድ ቀን ዘይቱን ልጠቀምበት ፈልጌ ዘይቱን ካስቀመጥኩበት ቦታ ሳነሳው ውስጤ ደገነጠ። ተው የሚልና የሚከለክል የሚቀፍ ስሜት ተሰማኝ። ዘይቱንም ከአስቀመጥኩበት ቦታ መለስኩት። አነድ ቀን ለሊት በህልሜ ዘይቱን ከጓሮዮ በሚገኘው ዛፉ ስር ድፋው የሚል ድምፅ ሰማሁ ። አኔም ይህን ነገር ለባለቤቴ ነገርኳት ። ከዛች ጊዜ ጀምሮ ዘይቱን ድፋው የሚል ስሜት አእምሮዮን ምላው ። ነገር ግን እኔ ያንን ዘይት አልደፋሁትም። ባለቤቴ በድንገት የእሀቷ ልጅ ስለሞተችባት ኢትዮጵያ ላኩሀት ። በሸኘኋት ቀን ያንን ዘይት በዛፍ ዙሪያ ደፋሁትና ቤቴ ገብቼ በዘይት ተመስሎ የገባውን መንፈስ እየገሰፅኩኝ በኋይልና በመንፈስ ፀለይኩኝና በመሽም ጊዜ ተኛሁ። ከረምት ስለነበር በረዶ በዛችው ምሽት በጣም ይጥል ነበር። በዛችው ቀን ሌሊት ሀይለኛ ድምፅና ፍንዳታ በተኛሁበት ሰምቼ በርግጌ ተነሳሁኝ ። ከአልጋዬም ወረጄ ወደ ልጆቼ ክፍል ሰሄድ እነሱም ደንግጠው ተነስተው ወደ እኔ ክፍል ሲመጡ ኮሪደር ላይ ተገናኘን። በጣም ሰለደነገጡ አረጋጋኋቸውና ፀልየን ተኛን። በጠዋት ተነስቼ የቤቴን ዙሪያ ስመለከት ያ ዘይቱን የደፋሁት ዛፍ ስር መኪና በረዶው አንሸራቶት በኃይለኛ ተጋጭቶ የመኪናው ስብረባሪ ከዛፍ ስር አየሁ ። እባካችሁ ኢትዮጵያውያን ተጠንቀቁ የተመተተበት ዘይት ይዛችሁ ወደቤታችሁ አትግቡ ። ያቺው ዘይቱን የሰጠችኝ ልጅ የቤተክርስቲያኑን አገልጋይ አገልግሎቱን አሰቁማው ከቤተክርስቲን አስኮብልላ አጥፍታው ጠቅልላ ወስዳዋለች። ከርስቲያን መስለው ከጓናችሁ ከተቀመጡ እርኩሳን መናፍስት ተጠንቀቁ ።የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች በደጃፋችሁ አንዳይደርሱ ነቁና ተጠበቁ ። ጌታ ይባርካችሁ ።
Woooow, unbelievable. All Glory to God my brother. I am just in awe...oh Hallelujah. Am glad God helped u to follow his Spirit.
All this times I have been going back home, I have never visited this churches- and I thought something was wrong with me- Thank you Jesus for saving me! 🙏
እንኳን ጌታ እረዳህ
betam yemigerm naw geta yisewiren
Wow እንኳን ጌታ ረዳህ ባለቤትህ በሌለችበት ትልቁ ጌታ ተጠነቀቀልህ። ድንቅ ነው
Eunte new Hanicho seliya new nesa yewotawu keza bohala new bare tekefito keza bohala wode Canada 🇨🇦 wotawu Hanicho sega yechemiri yene wudi nurilgen 😍😍💜
ቢጫ የለበሰችው ነብይት የእግዚአብሔር መንፈሰ በሐይል ይታይባታል ሞገሰ በጣም እግዚአብሔር ይባርክሸ በጣም ከዚ የበለጠ ቅባት በውነት ተባረኪ ዘመንሸ ይባረክ
ጌታን ለማምለክ እንጂ ከጌታ ለማግኘት አይደለም የምፈልገው ያለችው እውነት ገርሞኛል ። የብዙዎቻችን ግን የዚህ ግልባጭ ነው ። እህቴ ጌታ ይባርክሽ !!!
ትልቁ ነጥብ ይሄ ነው 99% ፐርሰንት የሚሆኑት አገልጋዮች እራሳቸውን ነው በገንዘብ የሚያገለግሉት፣አጭበርባሪዎች ናቸው አሁንማ አይን ያወጣ የፖለቲካ ሥራ ነው የሚሰሩት። እግዜር ይገስፃቸው።
የጌታ አገልጋይ ትግስት ጌታ ይባርክሽ። በየዋህነት ነቢይ ነቢይ እያሉ በከንቱ ለሚባክኑ ሁሉ ካስተዋሉና ወደ ቃሉ ቢመለሱ ይህ ትልቅ ምስክርነት ነው።
የእነዚህን ነብያት ስም ለምን አትናገርም ይህን የምትመሰክረው ሰዎችን ለማዳን እስከሆነ ድረስ እውነትን ግለጡት እነጂ አትሰውሩት
@Betty7 ትክክል
I agree
ልክ ነሽ Betty እግዚአብሔር ያዳናት ሌሎችንም ለማዳን ነው እንጂ መስክሮ ዝም ለማለት አይደለም!!
እኔም እሱን ነበር የማስበው ምክኒያቱም እነዚህ ሰዎች የሆነ ቦታ ጋ ካላቆሙ እጅ እየጫኑ የአጋንንትን መንፈስ ነው የሚሞሉት።
በድብቅ ወይም በሌላ ሚዲያ ቢነግሩን ጥሩ ነበር ለመጠንቀቅ
የመጨረሻዉ ዘመን ስለሆነ ከዚህ በላይ ሊሆን ግድ ነዉ ሰለዚህ ወደ ቃሉ እንመለስ በቃሉ ላይ እንድንተከል ይህ ምስክርነት ለእኛ ማንቂያ ነዉ ....እግዚያብሄር ይርዳን
እግዚአብሔር ይመስገን ሕይወታችንን እንድናይ አድርጎናል ተባረኩ
አሜን በቃሉ ያፀናናል
ከ 10 አመት በላይ በጌታ ቤት ቆይቼ ብዙም ቃሉን አላውቅም ነበር ዱባይ በፓስተር ፒተር ማድሪግ ለ 6 አመት ቃሉን ተማርኩ ሁሌም እባርከዋለሁ ሁሌም ቸርች ሊያገለግል ሲቆም መፅሃፍ ቅዱሳችሁን ከፍፍ አርጉ ብሎ በደንብ ያያል ሁሌም ቃሉን እንድናጠና ይመክረናል ስልክ ላይ እንኳን ማንበብ አይፈቅድም እግዚአብሔር ዘመኑን ይባርክ ያለምልም
Peter eko geta yebrkaw naw
ፓስተር ፒተር እንኳን አጠገቡ የተማራችሁት እኔ በyouTube ተከታትየዉ ትምህርቱን ሂወቴ ተለውጦአል ጌታ እየሱስ ዘመኑን ይባርከዉ
@@MT-rg3mt እውነት ነው አሜን ከተማርኩት ቃል የተነሳ ከሃሰተኛ ነቢያቶች (ጠንቋዮች) እግዚአብሔር ጠብቆኛል ጌታ ትውልዱን ይታደግ
@@godisgoodallthetime836 🙏 Amen
አሱም አራሱ አሰንታኝ አሰተማርይ ነዉ ፒተ ር wake up
ቲጂ እባክሽ እንደነዚህ አይነት ነብያቶች በግልፅ መነገር አለባቸው እሷ ጌታ ስለረዳት አመለጠች ሌላውስ ትውልዱስ ብዙዎቻችን በቃሉ የበረታን አደለንም የደረሰባት እውነት ሁላችንም ልናቃቸው ልንጠነቀቃቸው ይገባል ብዬ አስባለው ጥሩ ትምህርት ነው ተባረኩ።
የነብያቶቹን ስም መናገር አለባት ቢቻል እስከ ፎቶአቸው ይሄኔ ብዙ ሰውን እንደዚህ እያደረጉ ነው ስለዚህ ይሄ ነገር መጋለጥ አለበት ጌታ ኢየሱስ የሰላም አምላክ ነው ሰላምን እሰጣችሁአለው ሰላሜን እተውላችሁአለው እኔ የምሰጣችሁ ሰላም አለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም ይላል ቃሉ ኢየሱስ እረፍት ነው ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው ብቻውን ያድናል ጌታ ዘመንሽን ይባርክ እንኳን ጌታ እረዳሽ እንኳን ጌታ ደረሰልሽ
Ewnet new bizu ezib metadeg yichal neber
ለምድ ነው ቲጂ የነቡዩ ሰም መጠራ ያልተፈለገው ቲጂ ጌታ ይጠይቅሻል ሱሙ ተናገሩ ትውልድ እዲጠበቅ ሰሙ ለመጥራት ለምድነው? ??? ሰም ማትገልጪ ከሆነ ኢንተርቪ አታድርጋቸው? ??
Tekikli
፦ትክክል እሷ ከሞት ተረፈች ሌላሰውን ለማትረፍ አልፈለገችም
እባካቹ በጌታ ፍቅር እለምናቹሀለሁ ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ቃል እንመለስ የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል ይላል ትንቢተ ሆሴዕ 4-6 እንወቅ እናውቅም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል ሆሴዕ 6-3 ተባረኩ
God bless you!!!
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን 🙏ምን አይነት ግዜ ላይ ነው የደረስነው እባካቹ ከቃሉ ፈቀቅ አንበል ጆሮዬ ጭውውው አለ እግዚኦ! ቲጂዬ ብሩክ ፀጋው ይብዛልሽ🙏
ማንነታቸው መደበቅ ለምን አስፈለጋቹ? እነዚህ ሰዎች ታዋቂ ናቸው አላቹ ያ ማለት ደግሞ የብዙ የዋህ ሰዎችን ህይወት እያበላሹ ይቀጥላሉ ስለዚህ የኔ ምክር ማንነታቸውን በግልፅ ተናገሩና ሊጠፉ ያሉትን ነፍሳት አስመልጡ እውነት ከሆነ ምንም የሚያስፈራቹ ነገር የለም
የወሬ ያለህ
ፀልዪና ድረሺበት
@@felenuna8034 ምነው ይጋለጡ ስንል ተደናገጥክ/ሽ የሀሰተኛ ነቢያቱን እግር እጣቢ ውሃ ከሚሻሙት አንዷ/ዱ ነህ/ሽ መሰለኝ ፀሎት የእናንተ መቀለጃ አይደለም
Probably Esral Dansa
የአጋንንት ነቢያቶችን እባካችሁ ስማቸውን አጋላጡ ።
ዓይን የሚከፍት እና በጣም እንድንጠነቀቅ የሚያደርግ አናፂ ምስክርነት ነው። እህታችን ሜላት ለእግዚአብሔር ክብር እራስሽን ዝቅ አድርገሽ ጌታ ያደረገልሽን በመመስከርሽ እና ለበረከት ስለሆንሽን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክሽ። አገልጋሊት ሃና እና አገልጋሊት ትዕግስት ስለ ትጋታችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
ከጨለማ ጋር አትተባበሩ ግለጡት የሚለውን የከበረውን ቃል ተናግረሻል እህታችን ቲጂ !! እንዚህ ሀሰተኛ ነብያት የተባሉት እነማን እንደሆኑ መገለጥ አለበት ... የተዳፈነ ነገር ነው ... ለምን እነማን እንደሆኑ ተናግራችሁ ሌሎቹን አታስመልጪም እውነት ለትምህርት ነው ሌሎች ያምልጡ ብለሽ የምታቀርቢያቸው ከሆነ !! እውነተኛ አገልግሎት እያገለገልሽ የሚገለጡት ተገልጠው ስለ እውነት ዋጋ ብትከፍይ ይሻላል .. ድብብቆሽ ነው ቤተክርስትያንን እያፈረሰ ያለው
ጌታ ማስተዋል ይሁንሽ ስራሽን በመልካም ጀምረሽ የተደባበሰ ነገር ቃሉም አይደግፍም
Betkikile
ባጭሩ እግዚያብሄር በፊቱ ከሆንኩ እንዱፈቃዱ ከኖርኩ ለእርሱ ክብር በሚሆን ህይወት ከተመላለስኩ ለእኔ ለግሌ ይነግረኛል ብዬ አምናለሁ። እግዚያቤርን በግላችን እንወቀው፣ በቃሉ እውነት ላይ የታነጸ ህብረት ጋር ህብረት እናድርግ። እ/ር ስለኛ ምን እንደሚል ለማወቅ ወደ እ/ር እንጂ ወደ ሰዎች አንደውል። ዘመኑ ከፍቷል።
ቲጂየ በአገልግሎትሺ ሁሉ በጣም እባረካለሁ፡ይህችም እህታችን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካት፡የቀቦት ዘይት ከጥልቁ መናፍስት ጋ ህብረት እዲኖራትና ለትርፋቸዉ መጠቀሚያ ሊያደርጒት ነበር፡ ጌታን ስለምትወድና ቅን ልብ ስላላት ልብና ኩላሊትን የሚያይ ጌታ ደረሰላት፣ እየሱስ ጌታ ነዉ።
ምን አይነት ምስክርነት ነው!!! በእውነት እህቴ እንደዚህ ያሳለፍሽውን ስቃይ በግልፅ ስላካፈልሽን ተባረኪ!!! በጣም የሚያነቃ እና ወደ ቃሉ እንድንመለስ የሚያደርግ ምስክርነት ነው።
ቲጂዬ ላደረግሽው ሁሉ እግዚአብሄር በብዙ ይባርሽ!!! እባካቹ ሁላችንም share አድርገን ሌሎችን ከጥፋት እናስመልጥ!
እህቴ ጌታ ብዙ ምህረት አድርጎልሻል ስሙ ይባረክ ደስ ብሎኛል ቲጂ ነበይት ሀና ተባረኩ
2 ዜና 15፣3-6
እስራኤል ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ ያለ አስተማሪ ካህን ያለ ህግም ይኖሩ ነበር ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው በፈለጉት ጊዜ አገኙት ።
ወገኖቼ ዘመኑ አልቆል ወደ ጌታ እና ወደቃሉ እንመለስ ሀላችሁን እግዚአብሔር ይባርካችሁ
እኔ ግን የገረመኝ እንዴት ጌታ አሳልፎ ይሰጣታል ቃሉን እያነበበች እያመለከች ስሙን እየጠራች ሰይጣን እንዴት በሱዎ ላይ ይሰለጥናል እኔ በማላውቀው የጌታ መንፈስ ነው ብየ ባመንኩት ነብይ ብቀባ በልቤ ደግሞ ኢየሱስን እያመንኩ ከሆነ ከነሱ ጋር ካለው ከኔ ልብ ውሰጥ ያለው ያ ማመልከው የምወደው አምላክ ስላለኝ ሰለሚጠነቀቅልኝ ያ ሰው ነብይ ነኝ ብሎ ቢቀባኝ የሚሰራብኝ አይመሰለኝም ???? አወዛገባችሁኝ ደግሞ እነዚህ አጭበርባሪወች በስም ካልተጠቀሱ አሁንም ትፈሮችሆላችሁ ማለት ነው እኔ የዚህ ምሰክርነት ጥያቄ ብቻ ነው የፈጠረብኝ ለማንኛውም ተባረኩ
የምስክርነቱ ቃል ለሌሎች አስተማሪ ነው፣ እናመሰግናለን።
የአቅራቢዋ ድምጽ ደግም እጅግ ማራኪ የሆነ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
እህቴ እንኳን ጌታ ነጻ አወጣሽ ወገኖቼ ይህ ትልቅ ትምህርት ነው መንፈስን ሁሉ አትመኑ መርምሩ ማንም እኔ አገልጋይ ነኝ ያለው ሁሉ እጅ እንድጭኑላችሁ አትፍቀዱ ። የምአገለግሉአችሁን አገልጋዮች መርምሩ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው ሁሉን ይመረምራል
እነዚህ ሀሰተኛ ነብያት መገለጥ አለባቸው ሌሎች የክርስቶስ ተከታዩችንም እንዳያስቱ ሊገለጡ ይገባል ። እናንተ ግን ተባረኩልን እግዚአብሔር ይባርካችሁ ❤❤❤❤❤❤🙏🙏🙏👍👍
ይህ ምስክርነት ለሰይጣን እጅግ ክስረት ለብዝዎች ደግሞ ነፃ መውጣት ነው
ይህን ፕሮግራም ያየሁት አሁን ነው ግን ለህይወት የሚሆንን ስንቅ ይዤበታለው። ሀናንም ሜላትንም ጌታ ይባርካቸው። አንቺም ትግስት ጌታ ይባርክሽ። ጌታ አንቺን ተተቅሞ ለብዙዎች ደርሷል ብዬ አምናለው። ይህን ለሚያዩ ሁሉ ራሳቸውን በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት እንዲያፀኑ ጌታ ኢየሱስ ይርዳቸው።
ቲጂዬ ማንነታቸውን ለቤተክርስቲያን ማሳወቅ አለብሸ። እግዚያብሔር እድሉን ሰጦሻል። ሌላው አሁንም እየተሰቃየ ነው። ቲጂ ምን ታስቢያለሽ። ተባረኩ
ቲጅዬ ዛሬ ከሌላው ጊዜ ከመታነፅ ይልቅ የሆነ ግራ የሚያጋባ ነገር ሆኖብኛል ። confusion ውስጥ ከተተኝ። ምክንያቱም ስለአገልግሎት ይነሳል ጌታንም ስለመውደድ በሌላ መልኩ ይነሳል ። ነቢይ ወይም ነቢይት ስለሚባሉት ነገሮች እስካሁን ሰውው ለምን እንደ ጠንቋይ ቤት ጉዳዩን ይዞ ወደ እነሱ ለምን እንደሚሮጥ ሌላው ግራ የሚያጋባ ነው ። አሁንም ይህች እህት መላቀቅ እንዳለባት ይሰማኛል ።
እህቴ እንኳን ነጻ ወጣሽ ስለሁሉ ጌታ ይመስገን ። ነገር ግን የነዚህን በሉሲፈር የሚመሩ ነብያትን ማንነት አለመናገር እና አለመግለጥእና ስም ሳይጠሩ እንኳን በደፈናው አለመጠቆም በኢትዮጵያ እና አለም ዙርያ ያሉ የነሱ ቸርች አባል የሆኑትን ብዙ ሺዎች ሲኦል እንዲገቡ መፍቀድ ነው ።
yes that right !!
ምንም መልፋት አይጠበቅብንም ከመስፍን በሹ በስተቀር ሁሉም በሉሲፈር ነው ሚመሩት ።
wow..... ጌታ ሆይ የሚገርም ነው ተባረኩ እህቶቼ ከምስክርነታቸው የተነሳ ድል ነሱ ተብሎ እንደተፃፈ ውድ እህቴ ድል ነሳሽ ክብር ይሁንለት ለወደደን ከሐጢአታችን በደሙ ላጠበን ሃሌሉያ ኢየሱስ ምን ም ማለት አልቻልኩም ተባረክ አባ!!
ቅዱሳን ወደ እግዚአብሔር ቃል ተመለሱ።
Amen, geta Anchinim Yibark
በጣም የሚያስፈራ ጊዜ ነው ።እግዚአብሔር ምህረት ያድርግልን ።ተባረኪልኝ እህቴ ቲጂ።
እኔን በጣም ነዉ የገረመኝ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም😢😢😢 በተላይ ይባስ የቤተክርስቲያን ፓስተሮች😢😢 የተባሉ ጌታ ሆይይይ እርዳን ዉይይይይ በኢየሱስም እህታችን እግዚአብሔር ኢንኩዋን ከዝይ ሁሉ ማጥ አወጣሽ የእግዚአብሔር ነቢትም ጌታ ይባርክሽ ትጅዬም አንችንም ጌታ ስያስነሳሽ አላማ አለዉ ጌታ ይባርክሽ እግዚአብሔር ከሃገረችን ኢና ወገኖቼ የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑብን
እንኵኣን ጌታ ደረሰልሽ እህቴ! ደሞ ስታምሪ የኔ ደርባባ። ጌታ ኣብዝቶ ይባርክሽ ! በምስክርነትሽ እግዚኣብሄር ብዙ ልጆቹን እንደሚፈውስ ኣልጠራጠርም ያከበርሽው ጌታ ኣሁንም ጨምሮ ጨምሮ ለበረከት ያድርግሽ!
በርቺልን ቲጂዬ ፋይዳ ያላቸው ሰዎች
ስለምታቀርቢልን ጌታ ኣብዝቶ ይባርክሽ
Wow , amazing lesson !! Thanks to the immortal GOD JESEUSE who give you Mersey Amen !!
እጅግ በጣም የሚገርም ምሥክርነት ነው!!!!!
ቲጂ በርቺ!!!?
ወደ እ/ር ቃል መመለስ ምንም ሌላ አማራጭ የሌለው ነው!!!!!!!
ዋዉ የሚገርም አስተምሮት ን የያዘ ትልቅ ምሥክርነት ነዉ ጌታ ፀጋያብዛላችሁም እህቶቼ እባካችሁን ትልቅ ነዉ ያላችሁት አገልጋይ ግለጡት ሌሎችን አድኗቸዉ🙏❤❤❤
እግዚአብሔር ስላስመለጠሽ ደስ ብሎኛል እግዚአብሔር አምላክ ስሙ ይባረክ ።ግን እነዚህን ስወች ካላጋለጣችሁ ትውልድ ይጠፋል እግዚአብሔር የሚጠፋው ስው ደም ከእጃችሁ ይፈልጋል ።
የዚህችን ሴት ምስክርነት ስሰማ ናይጄሪያዊው አማኑኤል አሞፅን አስታወሰኝ። ዲያቢሎስ እንዴት አድርጎ ክርስቲያኖችን እንደሚያጠቃ ነው። ጌታ በእርግጥም አጥብቀው ለጠሩት ደራሽ ነው። እየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው 🙏🏾 ወገኖች ሁሉ ከእግዚአብሔር የሆነና ያልሆነውን ሁሉ ሁሉ ሁሉ መርምሩ። የእግዚአብሔር ጥበቃና ምህረት ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ይሁን። ጌታ እየሱስ ይባረክ። 🙏🏾
እህቴ ትግስት ይህን ጉዳይ ህዝቡን ለማትረፍ ሲባል ስማቸው ወይንም ቤ/ክርስቲያኑ ቢገለፅ ደግሞ ከፈራችሁ ስልክ የናንተን ብትሰጡን እና ብናናግራችሁ ብዙ በየቤቱ የተጎዳ ስለሚኖር ነፃ ቢዎጡ ተባረኩ::
“እኔም ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ በሕይወትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገድ እንዳይመለስ የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና”
- ሕዝቅኤል 13፥22
♥️እግዚአብሔር መልካም አምላክ እና አባት ነው ♥️እህቴ እንኳን ጌታ ረዳሽ እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏
ሰላም እህቴ ጌታ መልካም ነው እንዲህ አይነቱን ሰው ሌባ ስሙን ብትናገሪ ለሌሎች መትረፍ ይሆናል ደግሞም እውነትን ተነጋገሩ ብሏል ቃሉ
ሲጀመር ክርስትያንከሆን እግዚአብሔር የምንፈራ የምንታዘዝ ከሆነ
እራሱ እኮ መንፈሱ ይገለጣል ያስታውቃል
የተስጠን መንፈስ ክፍእና ድግን የምንልይብት ነው
ክፍን በጭራሽ ለለመከተል ቅም ተሰጥቶናል
እግዚአብሔር ይርዳን
ይገርማል ይህንን ያህል ከወጣ አይቀር ለሌላው ትምህርት እንዲሆን የአገልጋይ ነን የሚሉ ሰማቸው መጠቀስ አለበት
I really feel bad for this innocent woman. She is so brave to speak out. God really loves her! Hope people learn from her experience.
WOW Wonderful testimony .
ለምን የነብዪቹን ስም አትገልጣቸውም ብዙ ምስኪን ደሀ ና ጌታን አገኘሁ ብለው ፣ ብለን ከዘላለም ህይወት ከምንጠፋ ትግለጣቸው።
ወደ ቃሉ እንመለስ!!!! ኢየሱስ ጌታ ነው !!!!
አሜንንንን
አሜን🙌
እኔ ምስክር ነኝ ኢየሱስ ያድናል ይታደግማል ከእሱ ጋር ተጣብቄ ከሃሰተኛው ከሌባው ከገዳዩ አምልጫለሁ አምላኬ አስመልጦኛል ከቃሉ ጋር ተጣብቄ ብዙዎች ወደ እኔ መተው ነበር ግን ግን ጌታ አስመልጦኛል እኔም ቃሉን አጥብቄ ይዤ ስለነበረ ጌታን እንደ ተቀበልኩ ሰሞን ውር ውር የሚሉ ነብይ ነን ባዬች ነበሩ እኔም አላርፍም ነበር በሰአቱ ትንቢት እፈልግ ነበር አንድ ቀን ጌታ እራሱ ተናገረኝ አቆምኩ አገልጋይ ጋር መሯሯጥ ከዛ ጊዜ ጀምሬ ቃሉን መብላት ስጀምር በቃ ሂወቴ ለመለመ ከጠላቶቼም አዳነኝ ስለኔ የሚመለከተው እንዳለ ገባኝ እኔ አርፌ ቁጭ አንድ ነገር ሲመጣ ይሄ ጉዳይ የእኔ አይደለም አባቴ ያንተ ነው ብዬ እሰጠዋለሁ አሳምሮ ይሰጠኛል እኔ የሰራሁት አያምርም እሱ የሚሰራልን ግን እንዴት ድንቅ እንደሆነ አትጠይቁኝ ወገኖቼ ኢየሱስ ኡፍፍፍፍፍፍፍ አባት ብቻ ሳይሆን ሂወት ነው በቃ ዋው የምትሉለት ምግብ ነው እና ከብዙ ነገር ትጠበቃላችሁ አእምሮአችሁ ይሰፋል እግዚአብሔርን መፍራት ትጨምራላችሁ ልባም ሰው ትሆናላችሁ ነገ ምን እሆናለሁ ብላችሁ አትሰጉም በቃ ምን ብዬ ልንገራችሁ ብቻ ከቃሉ ጋር ተጣበቁ እግዚአብሔር ይርዳን እላለሁ እወዳችሃለሁ ተባረኩልን
Do you mind if I share this
ክብሩን እግዚአብሔር ይውሰድ! ተባረኩ! እህቶች! ጌታ ይርዳን
የኔ እህት ሜላት ሞገስሽ ተፈጥሮአዊ ውበትሽ ደስ ይላል የእግዚአብሔር ሰው መሆንሽን ያሳያል ብዙዎች ከአለም የባስ በተብለጨለጬበት ክርስትና እንዳንቺ ያለ ሴት ማየት ደስ ይላል እንደኔ እንደኔ የነብይነት አገልግሎት የለም ነብይ ነን የሚሉት ስርአት እንኳ የላቸውም አሁንም ተጠንቀቂ ከአምላክሽ ጋር ብቻ ተጣበቂ
በጣም ይገርማል ግን የእነዚህን ሰዎች ስም መደበቅ መልካም ነው ብዬ አላስብም ምክነያቱም ትውልድን ማዳን ነው ምድረ ጠንቋይ መገለጥ ነው ያለባቸው
እህት ትዕግሥት ተባረኪ ይህን መስማት ለብዙ ነገር ይጠቅማል ፕሮግራምሽን ወደድከት።
የሚያደነዝዘን እና ቃሉን እንዳናነብ የሆነዉ በየገስት ሀዉስ መዞራችን ነዉ ማለት ነዉ ይሄስ ያስፈራል። ስማቸዉን ብናዉቅ ጥሩ ነበር ከሄድንባቸዉ አንዱ ሊሆን ይችላል። እንኳን ጌታ ፈወሰሽ።
ያው ሐዋሳ ሱራፌል ነው
እኔ እንኳን አንድም ከእግ/ር የሆነ ያለ አይመስለኝም ምክንያቱም በአንድ ጊዜ ከአንድ ሰፈር ፈሉ ።ከዚያም እጅ እየጫኑና ዘይት እየቀቡ መንፈሱን አስፋፉት።
እህቴ እንኳን የወደድሸው ጌታ ታደገሸ አሰደናቂ ምሰክርነት ነው አገልጋዮቹ ግን ወየውላቸው የእግዚአብሔር ቁጣ በደጅነው!!
You humbled yourself to tell us all the truth. Thank you so much.
ደግሜ ደጋግሜ ሰማሁት ከአይምሮ በላይ ነው እንኮንም ጌታ ረዳሽ ነጻ ወጣሽ ክብሩን ሁላ ጌታ ይውሰድ ህዝቤ ሆይ ከሀሰተኞች ተጠበቁ ። ማንም እጁን ጭኖ እንዲጸልይላቹ አትፍቀዱ ማን ምን እንደሚያስተላልፉባቹ አታውቁም እና
ዋው እህታችን እንኳን እግዚአብሔር እረዳሽ እየሱስ ጌታ ነው ጌታ ይባርካቸሁ
Great testimony !!! may God blesses you abanduntly!!!
ሚገርም ነው እረ የት ነው የደረስን ግን የእነኚን ሰዎች ማንነት ቢገለጥ እና ልክ እንደሷም ባለማወቅ የእግዛብሔር መንፈስ ያለባቸው መስሏቸው ሰዎች እንዳይታለሉ
እኮ ካልነገሩን ልንሄድ እንችላለን።ለስማቸው ሲባል ሰው ማለቅ የለበትም፡ ብቻ የሚመረምረውን መንፈስ ጌታ ያብዛልን ማለት ነው እንጂ ከባድ ጊዜ ነው፡ የሚያምኑትን እንኳን እስኪያስቱ ሀሰተኞች እየበዙ ነው።
@@yeneneshmarie1607 የመጨረሻው ዘመን ላይንን በእውነት ፀጋው ይብዛልን ድምፁን ለይተን እንድንስማ እና በእግዚአብሔር ቃል ሁሉን እንድንፈትሽ
የኔ ጌታ ኢየሱስ ይባሬክ ለላ የምለው የለኝም ምስክርነቱ በቃሉ ላይ ብቻ እንድንደገፍ የሚያደርግ ድንቅ ትምህርት የምሰጥ ነው ። እህቶቼ ተባሬኩ ሀንዬ ጌታ በአንች ሥሰራ በመረዳት ደሬጃ አውቅ የነበሬ ብሆንም በዓይኔ በማየቴ እጅግ ደስ ብሎኛል አሁንም አብዝተሽ በጌታ የበሬታሽ ሁኝ !
እባካችሁ የነዚህን ነብያት ስም ግለጡ። ብዙዎች መጠንቀቅ አለብን ።
ስሙ ምን ያረግልሻል ወደቃሉ ዞር እንበል ከነብያቶች ላይ አይናችንን እናሳ
ke tenagerut yitawokal..
Wow wow Egziabher ymesgen tebareki
ዋው እግዚአብሔር አይጥልም አይተውም 🙏🙏ቅዱሳን ልንነቃ ይገባል የእግዚአብሔር ነገር ለማወቅ ከቃሉ ጋር መጣበቅ አለብን!!
እውነት ነው
ይቅርታ ይህ ቅዱሳን የሚል ቃል ለኛ ለሀጢያኞች ይሆን ግን
ጌታ ይባርክሽ እህቴ እንኳን ጌታ ደረሰልሽ ! ዘመኑ እጅግ ክፉ ነው ደግሞም ሐሰተኛ ነብያት የበዙበት ነው።ወደ ቃሉ እንድንመለስ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው ጌታ ማስተዋልን ይስጠን
እጅግ ለማመን የሚከብድ, በእርግጥ ዘመኑ በማለቅ ላይ ነው
መዳናችንን በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ መጠበቅ በቂ ነው::
P09
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ጌታየሱስ ይባርካቹ በጣም ጥሩ ትምህርት ነው
ይህን ታሬክ ስላጋራሺን ጌታ ይባርክሽ በጌታ ስም ይህን የከፋ ስራ የሚሰሩትን ወንጀለኞች ግን ስማቸው መገለጥ የነበረበት ይመለኛል የጌታ ፀጋ ይብዛልሽ😊
ዋው በጣም የሚገርም ምስክርነት ነው የነብያቶችን ስም ብትናገሪ ጡሩ ነበር
ሚገርም ነው !!!!!!!! ጉድ እያልኩ ነው ያየሁት ! ወይ ጌታ !!!! እንደው እግዚአብሔር ኒቆዲሞስ ሾውን ይባርክ !
በጣም አሰተማሪ ነው በዝህ ምስክርነት በዙ ሕይውት የተረፋል በዝህ ዘመን አድንነቃ ነው ተባረኩ ቲጂዬ ጌታ አብዝቱ የባርካሽ 🙌🙏
እነዚህን ሰዎች ማጋለጥ ነዉ ያለባችሁ ምክንያቱም ብዙ ሰዎች በዚህ አይነት እስራት ዉስጥ ስላሉ ስማቸዉ መጋለጥ አለበት
ለምን ነብያቶችን በስም አትናገሪም⁉️
በደፈና ምስክርነት ትምህርት አይሆንም ለሰዎች ‼️
99.9 %ነብያት ነን የሚሉ ጠንቁዋይ ናቸዉ ስንቱን ትዘርዝረዉ?
Geta Eyesus yebarek!!!!
እባካችሁ የነዚህን ነብያት ስም ንገሩን ቲጂየ እወድሻለሁ
ስማቸዉ ምን ያርጋል ተጠንቀአቁ ወደቃሉ እንዙር ከነብያቶች ላይ አይናችንን እናንሳ
ኧረ የእግዚአብሔር ቃል የሚለው መንፈስን ሁሉ አትመኑ ከእግዚአብሔር መሆኑን መርምሩ ይላል ቃሉን በማንበብና በመፀለይ መመርመር አለብን እንጂ ሰዎች የሰው ስም እንዲነግሩን መጠበቅ የለብንም እኛም መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር ነው
መንፈስ ቅዱስ ጥሎ አያፈራግጥም ሰላም ና እርጋታ ነው የሚሰጠው ።በመንፈስ ቅዱስ ተሞለተን ነው የምንወድቀው የሚሉት በሀሰት አሰራር ያሉ ናቸወ።እግዘብሔርን አይናቸውን ያብራ
የሚገርም ምስክርነት ነው... ዝም ብዬ ስጠረጥር እስራኤል ዳንሳ እና ጓደኞቹ ይሆናሉ። ካልሆኑ ግን እራሳቸው አይደለንም ይበሉ። እነሱ ናቸው ቃሉ የሌለበትን አገልግሎት የሚያገለግሉት። እናንተን ግን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቹ። አሜን
😂😂😂😂
Me too
Ene rasu gemchalew
ሁላችሁም ያላችሁትን ብላችኋል እኔ ግን ይህ ምስክርነት በራሱ የሚጋጩ ሃሳቦችን የያዘና የጠራ አይደለም ሰው ጌታን እየጠራ ቃሉን እያነበበ እየፆመና እየፀለየ እንዴት እንዲሁ ይሆናል? እንዲህማ ከሆነ መፆም መፀለይ በራሱ ችግርን ያመጣል እደማለት ይመስላል
በአንድ ሳይድ ጌታ ሲያርግ የሚመስለውን ጌታን አየሁት ቤቴ በብርሃን ተሞላ የብርሃን መላእክትን በቤቴ አየሁ ብላ ልዩልዩ የሰዎች ራሶችን አየሁ እነዚህ እራሶች ከእይታ ወደግርግዳ ላይ ከግርግዳ ላይ ወደልብስ ከልብስ ወደ ገላ(ሰውነት ላይ) መገለጥና በህይወት ላይ ችግር መፍጠር የመሳሰሉትን ነገሮች ከመጀመሪያው የሚገሰፀውን በማባረር እና የብርሃን የሆነውን በእግዚአብሐር ቃል በመለየት ከጌታ ጋር መቀጠል ሲቻል ተጠያቂዋ እንግዳ ይዛው የመጣችው ምስክርነት በራሱ መፈተሽ ያለበትና መጥራት ያለበት ጉዳይ ነው እላለህ
ሌላው በብርሃን የሚመላለሱ መንፈስ ቅዱስን እየተለማመዱ ያሉትን እንዲጠራጠሩና የመንፈስ ቅዱስን ሃይል እንዳይቀበሉ እንዲፈሩ እንዲሸሹ ያደርጋል
በሌላ እምነት ውስጥ ላሉና ህፀፅ በመፈለግ እውነትን በውሸት ለመበረዝ ለሚተጉ በር መክፈት ይሆናል
ባጠቃላይ ትጂ ከቃለመጠይቅሽ ስርጭት በፊት ትምህርት አዘል የሆኑና የጠሩ በዚህ አጋጣሚ ጠላት የራሱን መልእክተኞች ተጠቅሞ ኮንፊውዥን እንዳይዘራ ብትመረምሪው እላለሁ
ጌታ ስላስተረፋት ጌታ ይባረክ እነዚያን የቀቡዋትን ሰዎች ብትናገርና ወደሾው መጥተው ቢናዘዙም መልካም ነበር
በተረፈ ዩትብሽን ከሚከታተሉትና ከተጠቃሚዎች አንዱ ነኝ በርች
የኔም እይታ ነው !! በዛ ላይ ሁሉም ነቢያት ሐሰተኛ አደሉም ለይታ ብታወራ ቆንጆ ነበር!! እንኩአን ጌታ ነጽ አወጣሽ!!
Tegi and our sisters bless you more. ምስኪኑን ሕዝብ ኣድናችሁዋል። ስግብግብ ራስወዳድ የሉሲፈር ኣገልጋዪች በየሱስ ስም ኣሁንም የጋለጡ ይዋረዱ ! በቃሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንተከል ኣምልጠን እናስመልጥ
Amazing Testimony, praise Lord, Tgi stay blessed in Christ forever!
እናቴ አይዞሽ ተባረኪ ከዚህ የሚበልጥ የልኡልን ክብር ታያለሽ
የተወደዳችሁ ጌታ የረዳቹ እህቶቼ የክፉን ስራ በመግለጣችሁ ምክንያት እንዳይበቀላችሁ ጌታ ኢየሱስ በደሙ ይሸፍናችሁ
God bless you.
Blessed testimony.
የሚገርም ነው እግዚአብሔር የቃሉን እውነት ያብራልን
እህቴ እንኳን የምታመልኪው ጌታ ደረሰልሽ፣ ምን ያክል ሰይጣን ክፉ ውሸታምና አስመሳይ እንደሆነ እግዚዓብሄር ህዝቡን ሊታደግ አንቺን ተጠቅሞዓል ፤ ክብር ለአምላካችን ለእግዚዓብሄር ይሁን፡፡ አሜን
ወይ ጉድ ይገርማል እህቴ ያለፈችበት ወገኖች ልንጠነቀቅ ይገባል የምንሄድበትን ቦታ ማወቅ ከማን ጋር እንደምንፀልይ በተለይ እህቶቼ ጌታ ይርዳን እህቴ እንካን እግዚአብሔር ከዚህ ክፊ ገላገለሽ
በብዙ ተገርሚያለሁ።እናንተን ጌታ ይባረክ!!!እግዚአብሔር ከክፉ ሠራተኞች በደሙ ይሰውረን
ለትምህርት ከሆነ የነብያቱን(የሀሰተኞቹን) ስም ለምን አትናገሩም ትውልድ ይዳን ለስማችሁ ሳትጨነቁ የጨለማውን ስራ ግለጡ እኛም እከሌ ይሆን እያልን እንድንጠረጥር አታድርጉን።
እኔም ይህን ልል ነበር የገባሁት
They do something bad to her
ስም ብትጠቅስ ምናልባት ሚድያውን ሊያስከስስ ይችላል ይሄ የኔ ግምት ነው
Me too uffffff
በጣም ትልቅ እና አስተማሪ የሆነ ምስክርነት ነው ደግሞም ሰይጣን በምን ያህል በረቀቀ መንገድ ስራውን እየሰራ እንዳለ በጌታ በመሆን ዳግም ውልደትን ያገኘን እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙሮች ደግም በብዙ ጥንቃቄና ቃሉ ላይ በመመስረት መኖር እንደሚገባን ማወቅና የምናስተምር ደግሞ ከትንቢትም በላይ የጸናውና ህያው የሆነው ቃሉ ላይ ትኩረት ብናደርግ,# ዋናውና በደንብ ሊታሰብበት የሚገባው ጉዳይ ግን በዚህ ምስክርነት ይህንን በክርስቶስ ስም የተጭበረበረ ሠይጣናዊ ስራን የሚሰሩ ውሸታሞች በስምና በአድራሻ ተለይተው ቢታወቁ ሌሎችም ከጥፋት እንዲተርፉ መልካም ነው,ይህ በመሆኑ አንደኛ እውነተኛው የነቢያት አገልግሎትና ቢሮ ይጠበቃል ደግሞም ሌሎች ወደዚህ አይነት የሒወት ልምምድ ውስጥ ሊገቡ ያሉ ከጥፋታቸው ይመለሳሉ...
ቲጂዬ ሰላም ለናንተ ይሁን ዛሬ ብዙዎች እየተታለልን ያለንበት ጉዳይ ስለሆነ እባካችሁ እውነት አርነት ያወጣልና እነዚህን ግለጡልን ነጩን ነጭ ጥቁሩን ጥቁር ነው በሉን
ይህ ሾው አሁን ወደ ዋናው ነጥብ ይመጣ መጥተሻል።የዚህች ሴትዮ አይነት መንገድ ያለፉ ብዙዎች ይመጣሉ በሩን ክፈች።ጌታ ኢየሱስ ይክበርበት።
መጀመሪያ ፎቶውን እኮ አይታ ጨለማ ነው የማየው ብላለች ግን አቤት የኔ እህት እንኩዋን ጌታ ረዳሽ እንኔ እንደዚህ ታሞ ከቤተ ክርስቲያን የቀረ አውቃለሁ ጌታ ለልጆችሽና ለአንቺ ለቤትሽ እራራ 😭 እኔ ሁሌ ጉባኤ ኢትዮጵያ ስሄድ ፀልያለሁ ያልፈቀድከው እጁን እንዳጭንብኝ ብዬ ፀልያለው የት ውለው እንደሚመጡ የማይታወቁ ወረበላ ሁላ አሁንም አስተውሉ እረ እኔ ያለሁበት አገር እንዴት እንደሚሆኑ ነብይ ሲባል ጌታ ምህረት ያርግልን ስንቱ አብዱዋል ,TG ጌታ ይባርክሽ እንድናስተውል ስላረክሽን 🙏
A great lesson! May Lord help you to reveal more.
Wow...never expected this. Thank you for bringing it to the light. Our desperation will take us to the darkness...my brothers and sisters Christ is enough ere....nothing else.
Wow Amazing testimony the holy sprit is the only true sprit God bless you my dear sister God bless all we need discerning sprit God is so Good and great
ነብያቶቹ ሳይሆን ጂኒዎቹ ነው የሚባሉት ። ማንነታቸው መታወቅና መገለጥ አለባቸው ህዝቡ መንቃት አለበት ጂኒዎቹ በእግዚአብሔር ስም ሲነግዱ ሲያጭበረብሩ ከደፈሩ እኛ ደግሞ እነሱን ደፍረን በስምና በአድራሻ ማጋለጥ አለብን !!! plz ቅዱሳን እንንቃ
እንኳንም ጌታ አስመለጠሽ እህቴ
የጌታ ስም ይባረክ ግን እንደዚ የሚሰሩ ሰዎችን ስማቸውን ብትናገር እና ብታጋልጡአቸው አሪፍ ነው ምክንያቱም ብዙ ተከታይ ይኖራቸዋል ባአንቺ አልፎ የተናገረን ጌታ ስሙ ይባረክ ወደ ቃሉ እድንመለስ እሱ ይርዳን ቲጂዬ ተባረኪ
ዋው ክብር ሁሉ ለጌታ ይሁን አሜን።
እግዚአብሔር መልካም ነው።
ዘመናችሁ ይባረክ ።
ትጅዬ ከፍ በይ ፀጋ ይበዛልሽ።
በጣም አደንቅሻለሁ ወጥተሽ በመናገርሽ እህቴ እግዚአብሔር ይባርክሽ፣ ለብዙዎች የማንቅያ ደወል ነው ። ነገር ግን ስማቸው መናገር አለብሽ የነዚህ የሀሰተኛ ነብያቶች፣ የሰይጣን አገልጋዮች ፣የዘሩትን ያጭዳሉ አቤት ጌታ ሆይ እባክህን ጠብቀን በእውነት ያስፈራል
እንኳን ጌታ ደረሰልሽ እህቴ: የኛ አገር በተለይ ባሁኑ ሰአት ነብይ ነን ከሚሉ ሌቦች አስመሳይ እግዚአብሔር ይጠብቀን❤
ማምለጫ መፈወሻ ከዚህ ሁሉ መዳኛ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው እንደገና በቃሉ መሰረት ላይ መታነጽ ይሁንልን❤❤❤❤❤
እህታችን ትዕግስት ጌታ እየባረከ ይባርክሽ። ለመባረክ ካለን ጉጉት የተነሳ ያለእውቀት እንዴት ለአደጋ እንደምንጋለጥ ትልቅ ትምህርት ሰጪ ዝግጅት ነው።ዝም ብሎ ዘይት መቀባት ለካስ እንዲህም አለ ያስብላል።ቅዱሳን ጌታ የመለየትን ፀጋ ያብዛልን እላለሁ።
ቲጂ ጌታ ይባርክሽ ይህ ምስክርነት ብዙዎችን ስለሚታደግ እባክሽ ጌታ ግለጡት ስለሚል ሰዎችን ስማቸውን ትግለጥ ካለዚያ እውነት ነው ብሎ ለመቀበል ያዳግታል
እረ ሚገርም ነው መንፈስ ቅዱስ አይኖቻችንን አብራልን በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ ተብሎ ተፅፏል አቤቱ ድምፅህን ለይተህ አሰማን እኔ በጣም ገርሞኛል
ህይወት ብርቱ ሰልፍ አለበት የራስን አካሄድ ማስተዋል ግድ ነው። ቃሉን ማስተዋል ጌታንም በተፃፈው እውነት ብቻ መከተል ግድ ያለበት ወቅት ነው። ሶስታችሁም ተባረኩ !!
እግዚአብሔር ድንቅ ነው ምህረቱ ብዙ ነው፣ የረዳሽ ጌታ ይባረክ ❤❤
ይህ ኪሳራ ነው የላከው ለጌታ አይደለም ተበልተሻል እንኳን ጌታ ነፃ አወጣሸ ❤❤❤❤