የዳናው አህመደ ዳንይ ((ኹዝ ቢየዲ ያረሱለሏህ)) ጉድ ነው አል-መወዳ ቲዩብ

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 14 ม.ค. 2025

ความคิดเห็น • 6

  • @WeWee-m9t
    @WeWee-m9t 12 วันที่ผ่านมา

    ❤😢مشاءالله تبارك الله مشاءالله تبارك الله مشاءالله تبارك الله مشاءالله تبارك الله صلى الله عليه وسلم صلى الله عليه وسلم

  • @seadaasefa4266
    @seadaasefa4266 ปีที่แล้ว

    ماشاء الله

  • @ElAb-dy3du
    @ElAb-dy3du 10 หลายเดือนก่อน

    የማን ነው ድምፁስ?

  • @HhHh-l5j1m
    @HhHh-l5j1m 3 หลายเดือนก่อน

    አጀብነው

  • @Al-Meweda_tube
    @Al-Meweda_tube  ปีที่แล้ว

    ‹‹ኹዝ ቢየዲ ያረሱለላህ›› የምትለዋን ዱዓ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዜሙት የዳናው የመጀመሪያ መሪ ሸኽ አህመድ አደም ናቸው። ይህችን ዱዓ ሊቀኙ የቻሉበትን ምክንያት ዕውቁ ዐሊም ሸኽ ዐብደላህ እድሪስ ሲነግሩን በእንባ ታጥበናል።
    ይኼውም ወሌ ጉግሳ ለተበባለ የአአከባቢው አንባገነን ክርስትያን ገዥ ሰዎች ሄደው፦ ሸኽ አህመድ የገሀነም እንደሆንክ እየተናገሩ ነዉ›› ይሉታል። በሰማው ነገር በጣም ይበሳጫል። ሸህ አህመድ ተይዘው ከፊቱ እንዲቀርቡ ያዛል። ታላቁ ዐሊምተይዘው ቀረቡ።
    «የገሀነም እንደሆኩ ትናገራለህ አሉ» ሲል አፈጠጣቸዉ።
    «እኔ እንደዚያ አላልኩም ፣ አምላክ ለገሀነም ያጨዉን ሰው መርጦ ነው የሚያስቀምጠው» ሲሉ በቅኔ መለሱለት። «እርሱ ራሱ መርጦ ይወስናል እንጂ እኔ መዳቢ አይደለሁም» ይመስላል የዚህ ቅኔያዊ መልሳቸው ጥሬ ትርጉም /ሰም/።
    በሌላ በኩል የዚህ አምባገነን ገዥ ቤተ መንገስት ያለበት ከተማ «መርጦ» ትባላለችና የቅኔያቸው ወርቅ «መርጦ ከምትባለው ከተማ ላይ የነገሰው ግፈኛ አምላካዊ ቅጣት አይቀርለትም» ማለት ነዉ።
    ጉግሳ ቅኔው አልገባዉም። በዙሪያው ያሉ ሰዎችም እንደዚሁ። በተናገሩት ተረጋግቶ ሸኹን ወደ መጡበት በሠላም ሸኛቸው።
    ውሎ አድሮ ቅኔው በነገረኞች ሲፍታታታ ፣
    «በዚህ ግፍህና ክህደትህ ከቀጠልክ ጀሀነም አይቀርልህ» ማለታቸው እንደሆነ ተደረሰቀት። ጉግሳ ትርጉሙ ሲገለጥለት በጣም ተበሳጨ። በአስቸኳይ ከፊቱ ይቀርቡ ዘንድ ወደ ሸኽ አህመድ መልዕክት ላከ። «አልመጣም በሉት» ሲሉ መለሱለት። ጉግሳ ጦር ይዞ ወደ ዳና ገሰገሰ።
    ታላቁ ዐሊም የዚህን ካፊር ጸለምተኛ ፊት ከማየት ፣ ዳግም ማየት አልፈለጉምና ጉዞ መጀመሩን ሲሰሙ ፡ አላህ ሞትን እንዲያድላቸው አጥብቀው ዱዓ ጀመሩ። ለወዳጆቻቸው ለመልዕክተኛዉም፦ ‹‹ኹዝ ቢየዲ ያረሱለላህ›› የሚል ማስታወሻ ሌት ከቀን እያዜሙ ላኩ።
    «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ፣ መሞቻዬ ደርሷልና በመጪው ዓለም እጄን ይዘው የርሰዎ ሸፈዐ ተጋሪ ያድርጉኝ» ነው መልዕክቱ።
    ረቢዕ ኢብን ከዕብ «በጀነት ከርሰዎ ጋር መሆን እፈልጋለሁ» እንዳላቸዉ ፤ ሙስዐብ አል-አስለሚ ሸፈዐቸውን በቀጥታ እንደጠየቃቸው ወይም የዑትቢ ባለታሪክ ከቀብራቸዉ ተደፍቶ ዱዓ እንደተማፀናቸው ሁሉ ሸኽ አህመድ ዳኒም «ኹዝ ቢየዲ»ን ለዓለማት ዕዝነት አስታወሱ።
    ኢማም አል-ቡኻሪ በወገኖቻቸዉ እንግልት ባገኛቸዉ ጊዜ አላህ እንዲገድላቸዉ ዱዐ ባደረጉ በሳምንታት ዉስጥ እንደሞቱት ሁሉ የሸኽ አህመድን ዱዐም አላህ ፈጥኖ ተቀበላቸዉና የጉግሳ ጦር ከቦታው ከመድረሱ በፊት ፣ ሸኽ አህመድ ይህችን ዓለም በሞት ተሰናበቱ። ጉግሳ ከቦታዉ ደርሶ የርሳቸዉን መሞት ሲሰማ ታላቅ ሰው ማሳደዱ ቆጭቶት በጣም አለቀሰ። እነሆ «ኹዝ ቢየዲ» ዛሬም በደረሶቻቸው እየተዜመች የዚያን ሙጃሂድ ልዕልና ታስተጋባለች። ይህችን ታሪካዊ ክስተትም ታስታዉሳለች።
    (ሐሰን ታጁ መጽሐፍ ‹‹ተወሱል›› 268-279 የተወሰደ ነዉ።)
    ይህ ነበር ለደረሶቻቸው የተላከው። (የመጨረሻዎቹ ስድስቱ የግጥም ቤቶች የደረሳቸው ሸህ በድሬ ነው።)
    خُذ بِيَد يَارَسُول اللَّه؛
    🍀🍀🍀🍀🍀
    يَا مِفْتَاحًا لِكُنِوزِ ﺍلله
    يَا حِجَابًا لِعَذَابِ ﺍلله
    يَا كَعْبَة لِتَجلِّى ﺍلله
    يَا مَجَالًا لِجَمَالِ ﺍلله
    أَيَا عَرْشًا لِاسْتِوَاءِ ﺍلله
    يَا كُرْسيًّا لِتَدَلِّى ﺍلله
    يَا كَرِيْمًا مِنْ كَرَمِ ﺍلله
    أَنْتَ البَابُ لِعَطَاءِ ﺍلله
    يَا مَنْبَعًا لِمِنَّتِ ﺍلله
    يَا حِحِابًا لِجَلَالِ ﺍلله
    يَا سَمَاء لِرَحْمَةِ ﺍلله
    يَا سَحَابًا لِفَيْضَاتِ ﺍلله
    يَا مَهْبِطًا لِكَرَمِ ﺍلله
    يَا مَحَطًّا لِرِجَالِ ﺍلله
    أَنْتَ عَيْنٌ مِنْ عُيُوْنِ ﺍلله
    وَمِيْزَابُ فَيضِ صَلَاةِ ﺍلله
    أَنْتَ السِّرُّ لِإبْدَاعِ الْكَون
    يَا دُرَّةً مِنْ دُرَرِ ﺍلله
    أَنْتَ كَهْفُ مَوْجُودَاتِ ﺍلله
    وَكَنَفُ مِنْ غَضَبِ ﺍلله
    أنْتَ اَنْتَ يَا رَسُوْلُ ﺍلله
    أنْتَ الْمَقَقْصُوْدُ يَاحَبِيْبَ ﺍلله
    يَا سُلَّمًا لِأوْجِ الْكَمَال
    أنْتَ الرَّاقِى قِمَّتَ الْكَمَال
    كَمْ وَضِيْع بِكُمْ تَرَفَّع
    كَمْ ذِى ضَيْقٍ بِكُمْ تَشَفَّع
    يَا رَحِيْقًا لِطُلَّابِ ﺍلله
    مَنْ غَرْقَاء حَضَرَاتِ ﺍلله
    يَا قَامُوْسًا لِأَسْرَارِ ﺍلله
    يَا نَامُوسًا لِنَامُوْسِ ﺍﻟﻠَّﻪ
    أنْتَ الْوَاقِى مِنْ عَذَابِ ﺍلله
    أنْتَ السَّاقِى مِنْ شَرَابِ ﺍلله
    يَا رَيْحَنًا لِمَشَامِ الرُّوْح
    بِكَ النَّصْرُ وَبِكَ الْفُتُوح
    يَا طَلْمَسًا لِأَسْرَارِ ﺍلله
    يَا فَكَاكَا لِرُمُوزِ ﺍلله
    يَا فَاتِحًا لِأَبْوَابِ ﺍلله
    لِأَحْبَابِ حَضَرَاةِ ﺍلله
    مَائِدَةُ جُلَسَاءِ ﺍلله
    وَبُسْتَانُ عُرَفَاءِ ﺍلله
    أنْتَ السَّارِى بِإذْنِ الْبَارِى
    فِى ذَرَّةٍ مَوجُودَات ﺍلله
    يَا مَدِيْنَة لِعُلُومِ ﺍلله
    وَمَرْكَزًا لِشُهُوْدِ ﺍلله
    يَا قَاسِمًا لِعَطَاءِ ﺍلله
    وَسَاقِيًا مِنْ بُحُورِ ﺍﻟﻠَّﻪ
    يَا شُمُوسًا لِأُكْوَانِ ﺍلله
    يَا بَدِيْعًا مِن شُؤُنِ ﺍلله
    أنْتَ السَّاقِى لِأحْبَاب ﺍلله
    وَجَوَّالُ جَبَرُوتِ ﺍلله
    يَا مَظْهَرًا لِصَلَاةِ ﺍلله
    وَيَنْبُوْعًا لِصَلَاتِ ﺍلله
    يَا كَحَّالًا لِعَيْنِ الْأَخْيَار
    وَحُمَيَّا كَأْسِ وُدِّ ﺍلله
    فَأَغِثْنَا يَا رَسُولَ ﺍلله
    بِجَاهِكَ الْوَافِى عِنْدَ ﺍلله
    يَا مَلْحُوظًا بِعَيْنِ الْجَمَال
    يَا مِيْزَابًا لِفَيْضَاتِ ﺍلله
    جَعَلْتُهَا لِيَ رَاتِمَة
    أَرْجُوْبِهَا حُسْنَ الْخَاتِمَةَ
    وَصَلَاةً هُوَ أَهْلُهَا
    مَا غَرَّدَ لُبٌّ أَهْلِ ﺍلله
    وآلِه وَصَحْبِهِ الْكَرَام
    مَا تَوَاتَر غَيْثُ حُبِّ ﺍلله
    خُذ بِيَد يَا رَسُول اللَّه
    🍀🍀🍀🍀🍀

    • @SamsungGalaxy-o6m
      @SamsungGalaxy-o6m ปีที่แล้ว

      ኹዝ ቢየዲ ያ ሸይኽ አህመደ ዳንየ ላኪን ኢኒ ነጃሰቱን ሪድዋኑሏህ😭