🔴Live

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 10 ม.ค. 2025
  • ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕር ዳር
    +++ በአታ ለማርያም +++
    በአታ ለማርያም ማለት የማርያም ወደ ቤተመቅደስ መግባትዋ ማለት ነው። እግዚአብሔር ብቻ የገባባት ታናሸዋ ቤተመቅደስ ድንግል እናታችን ወደ ቤተመቅደስ የገባችበትን ቀን (በአታ ለማርያም) በዓል አድርገን እናከብራለንና ጥቂት ሐሳብ እናንሣ:-
    ++ ቤተመቅደስ - ምእመናን +++
    ምእመናን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ” ይላል፡፡(1ቆሮ 3÷16) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እስከተመላለስን ድረስ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንሆናለን ፡፡ በተቃራኒው ከፈቃዱ ወጥተን እንደ ሰይጣንና እንደ ሥጋችን እንዲሁም እንደ ዓለም ፈቃድ ብቻ የምንመላለስ ከሆነም የሰይጣን ማደርያዎችም እንደምንሆን መጻሕፍት ያስተምሩናል፡፡(ማቴ 12÷43-44) እንደ ፈቃዱ የሚመላለሱ ሰዎችና ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔር በጸጋ የሚያድርባቸው ቤተ መቅደሶቹ ናቸው፡፡
    +++ ቤተ መቅደስ - ሕንፃ ቤተክርስቲያን +++
    ምእመናን ለአምልኮተ እግዚአብሔር ለውዳሴ ለቅዳሴ ቃሉን ለመማር ንስሐ ለመግባት ለአገልግሎትና ለመሳሰሉት የሚሰበሰቡበት ስፍራም የእግዚአብሔር ቤት ቤተ መቅደሱ ነው፡፡ (ዘጸ25÷8፣ 1ጢሞ3፣15 መዝ5÷7 ማቴ21÷13) ይህ የተቀደሰ ስፍራ ቅዱስ መቅደሱም እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥበት ማደርያው ነው፡፡
    ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕር ዳር, [12/11/2024 10:36 AM]
    የቀጠለ...
    +++ እግዚአብሔር ብቻ የገባባት ቤተ መቅደስ +++
    እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደሱ ናት፡፡ እግዚአብሔር እርሷን ቤተ መቅደሱ ባደረገበት መንገድ ማንንም ምንንም ቤተመቅደሱ አላደረገም!! ከእንግዲህም አያደርግም፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን “እነሆ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፡፡” በማለት የተናገረለትን አምላክ እርሷ በማኅፀኗ ወሰነችው ቤተመቅደሱም ሆነች፡፡ (2ነገ 8:28) ሊቁ ቅዱስ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ በደረሰው የቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ "ገጹ እሳት ልብሱ እሳት መጎናጸፊያው እሳት የሚሆን አምላክ በማኅፀንሽ በተወሰነ ጊዜ እንደ ምን አድርገሽ ቻልሽው? እንደምን አድርገሽ ወሰንሽው? እንደምን አላቃጠለሽም?" በማለት እንደመሰከረውም እመቤታችን የማይወሰነው የተወሰነባት የማይታየው የታየባት ልዩ የእግዚአብሔር ቤተመቅደሱ ናት፡፡ (1ጢሞ 6÷16) እመቤታችን እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸከመችው፤ በሕቱም ድንግልና ጸንሳ በሕቱም ድንግልና ወለደችው፤ ጡቶቿን አጠባችው፤ በጀርባዋ አዝላው ከእስራኤል ተነሥታ በግብጽ በረሃ ተሰደደች፡፡ እመቤታችን ነቢዩ ሕዝቅኤል "ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ ተዘግቶም ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል፡፡" ብሎ በራእዩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተመለከታት ሕቱም ቤተመቅደስ ናት፡፡ (ሕዝ 44:1) ነቢዩ በምሥራቅ የተመለከታት መቅደስ እመቤታችን ናት፡፡ ይህ በር መዘጋቱ እመቤታችን ጌታን ከመውለዷ በፊት ድንግል መሆኗን ያመለክታል፡፡ "እግዚአብሔር ገብቶበታል" አለ እርሱ በማኅፀኗ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተፀንሷልና፡፡ "ተዘግቶ ይኖራል፡፡" አለ እመቤታችን ዘላለማዊት ድንግል ናትና፡፡ በጳጳስ ወንበር ቄስ በንጉሥ ዙፋን ራስ ወይም ወታደር ሊቀመጥ እንደማይቻለው እንደማይገባውም አምላክ ባደረባት ማኅፀንም ፍጡር አያድርም፡፡ ዐውደ ማኅፀንዋ አስቀድሞ በትንቢት ታጥሯል በብፅዓት ተቀጥሯል ተዘግቶ ይኖራል አይከፈትም ሰውም አይገባበትም፡፡ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ ፈጣሬ ፍጡራን ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ መሆኑ የገባው ሁሉ እናቱን ይወዳታል ያከብራታልም፡፡
    ©ቢትወደድ ወርቁ
    ታኅሣስ 03 ቀን 2017 ዓ ም
    🌐ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕርዳር
    🛜በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ያድርሱ...
    👉 Telegram
    t.me/finotehiwotgroup
    👉 Facebook
    / finotehiwotss
    👉Email address
    fenotehiwotmedia@gmail.com
    👉TH-cam
    / @finotehiwet
    👉Tiktok
    www.tiktok.com...
    #አቡነ_ማትያስ #አቡነ_አብርሃም #አቡነ_ጴጥሮስ
    #አቡነ_ኤርምያስ #አቡነ_መርቆሬዎስ #አቡነ_ጎርጎሬዎስ#አቡነ_ፊሊጶስ
    #ቅድስት_ክርስቶስ_ሰምራ#ደብረ_አሚን #አቡነ_ተክለሃይማኖት
    #ቅዱስ_ሚካኤል
    #ቅዱስ_ገብርኤል
    #ቅዱስ_ሩፋኤል
    #ቅዱስ_ራጉኤል
    #ቅዱስ_ፋኑኤል
    #ቅዱስ_ዑራኤል
    #ቅዱስ_ላሊበላ
    #ቅዱስ_ነአኩቶለአብ
    #አቡነ_ተክለሃይማኖት
    #አቡነ_ገብረመንፈስ_ቅዱስ
    #አቡነ_አሮን
    #አቡነ_ይምዐታ
    #ቅዱስ_ቂርቆስ
    #ቅዱስ_ጳውሎስ
    #ቅዱስ_ጴጥሮስ
    #ወረብ
    #መዝሙር
    #ኦርቶዶክስ
    #ቦሌ
    #መድኃኔዓለም
    #ሰዓታት
    #ቅዳሴ
    #ማኅበረ_ቅዱሳን
    #mahbere_kidusan
    #kidasie
    #merkato
    #st_raguel
    #bole
    #medhaniealem
    #ማኅሌተ_ጽጌ
    #መንበረ_ፓትርያርክ
    #teklehaymanot
    #EOTC #EOTC_MK

ความคิดเห็น •