“በሲና በረሃ ያወረደ መና/ ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ሚካኤል” ለዚህ ያደረሰን እግዚአብሔር ይመስገን

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 6 ก.ย. 2024
  • የምህረት መላክ
    በሲና በረሃ ያወረደዉ መና
    የእስራኤል መሪ በአምደ ደመና
    የመላክት አለቃ ሚካኤል ነዉና
    የምህረት መላክ ቅ/ሚካኤል
    /2/
    ፈጥኖ ይደርሳል ያማልደናል
    በስጋም በነብስ ይታደገናል
    /2/
    አዝ.........
    ዳንኤልን ከአናብስት ባህራንን
    ከሞት
    ቅድስት አፎምያን ከሰይጣን
    ያዳንካት
    እኛንም አድነን መለአከ ምህረት
    አዝ.........
    ክብሩ ታላቅ ነዉ ድንቅ ነዉ ስሙ
    ማን እንደ እግዚያብሔር መላከ ምሩ
    ቅዱስ ሚካኤል ድንቅ ነው ታምሩ
    አዝ......
    ተራዳይነቱ መፅሐፍ መስክረዋል
    ስለ ህዝብ ልጆች ሚካኤል ይቆማል
    ምህረት የሚያሰጥ ኪዳን ተቀብሏል
    አዝ......
    በመታሰቢያዉ ቀን ይነበብ ድርሳኑ
    ዝክሩን እናዘክር ይከበር በአሉ
    ሚካኤል ያድናል ምልጃዉ ቃልኪዳኑ

    ✝️ቅዱስ ሚካኤል✝️
    ቅዱስ ሚካኤል(፫)
    ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
    ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ
    አንተ ስለሆንክ - - - ሚካኤል
    የአምላክ ባለሟል - - - ሚካኤል
    ልመናህ ፈጥኖ - - - ሚካኤል
    ከአምላክ ያቀርባል - - - ሚካኤል
    የዋህ መልአክ ነህ አዛኝ ለሰው(፪)
    ምልጃህ ፈጣን ነው ለምናምነው (፪)
    አዝ=====
    ደዌ የጸናበት - - - ሚካኤል
    ባንተ ይድናል - - - -ሚካኤል
    በአደባባይህ - - - ሚካኤል
    ምስክር ሆኗል - - - ሚካኤል
    ከቤትህ መጥቶ የተማፀነ(፪)
    በቃል ኪዳንህ ህይወቱ ዳነ (፪)
    አዝ=====
    ከአምላክ ተሰጥቶህ - - - ሚካኤል
    ክብርህ ያበራል - - - ሚካኤል
    ለጎስቋላው ሰው - - - ሚካኤል
    መጠጊያ ሆኗል - - - ሚካኤል
    ትንሽ ትልቁ ደሀው ሀብታሙ(፪)
    ለምኖ አግኝቷል ከአምላክ በስሙ(፪)
    አዝ=====
    በብሉይ ኪዳን - - - ሚካኤል
    ከአምላክ ተልከህ - - - ሚካኤል
    ሕዝበ እስራኤልን - - - ሚካኤል
    ነጻ ያወጣህ - - - ሚካኤል
    በአዲስ ኪዳንም ድንቅ ስራ አለህ(፪)
    በተአምራትህ ትፈውሳለህ(፪)
    አዝ=====
    ባለ መድኃኒት - - - ሚካኤል
    ያቃተውን - - - ሚካኤል
    ፈዋሽ ፀበልህ - - - ሚካኤል
    ሆኖኛል ዐይን - - - ሚካኤል
    እንደ መጻጉዕ ድሕነት አገኘው (፪)
    ፈውሰኸኛል በአንተ ተመካው (፪)

ความคิดเห็น • 1

  • @kennaazawude
    @kennaazawude หลายเดือนก่อน +2

    እልልልልልልልልል❤❤❤❤