ከቃል እስከ ባህል | From Pledge to Practice | አብይ አህመድ | Abiy Ahmed

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 10 ก.พ. 2025
  • ከቃል እስከ ባህል | From Pledge to Practice | አብይ አህመድ | Abiy Ahmed
    Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
    Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ
    “ቀጣዮቹ ወራት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብሥራት የምናደርስባቸው ይሆናሉ”
    የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
    +++++++++++++++++++++
    ጥር 24/2017 (ጋዜጣ+)፡- አሁን የማንሰራራት ዘመን በመሆኑ ቀጣዮቹ
    ወራት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብሥራት የምናደርስበት ይሆናል ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የመክፈቻ ሥነሥርዓት ትናንት ሲካሄድ ባደረጉት ንግግር፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተጓዝንበት መንገድ ከጥልቅ እንቅልፍ እና ከብዙ ዕዳ የተነሳንበት ምዕራፍ ነው ብለዋል፡፡
    በዚህ ምዕራፍ የታሰረ ይፈታ፣ የተሰደደ ይመለስ፣ ያኮረፈ ይታረቅ፣ የተባረረ ይመለስ፣ የተከፋፈለ ይደመር፣ ቶርቸር ይብቃ፣ አቧራ ይራገፍ፣ ፀጋ ይገለጥ ብለን በተግባር ይሄንኑ አሳይተናል ብለዋል።
    አሁን ይሄን ሁሉ የፈጸምንበት የመነሳት ምዕራፍ አብቅቶ የማንሰራራት ዘመን ተተክቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህም በቀጣዮቹ ወራት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብሥራት የምናደርስበት ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።
    የማንሰራራት ዘመን ሲባል የቁልቁለትና የጎንዮሽ ጉዞ የሚያበቃበት መሆኑንም አመላክተዋል።
    ከጉባኤው በኋላ ያሉት ወራት ፕሮጀክቶችን የምናስመርቅበት፣ ሪባን የምንቆርጥበት እና ዐሻራ የምናስቀምጥበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሥራት የምናደርስባቸው ናቸው ሲሉ አመልክተዋል።
    ለውጥ መፍጠር ብቻውን ለውጥን መምራት የሚያስችል ብቃት እስካልፈጠረ ድረስ የተሟላ የፓርቲ ሕልውና እንደማይኖረው ጠቁመው፤ ለውጥ መፍጠር ሲባል ስላለ ችግር ድካምና ውድቀት አብዝቶ መናገር ብቻ ሳይሆን መፍትሔም ማፍለቅ የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።
    ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል የነበሩ ኋላ ቀር አሠራርና ልምምዶችን በማፍረስ በአዲስ እሳቤና የለውጥ ሥራዎችን አልቆ አስቀጥሏል ብለዋል።
    ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገር በቀል እሳቤ ነድፎ የተገበረ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፓርቲው ለኢትዮጵያ ፍቱን መድኃኒት የሆነውን ሀገር በቀል የመደመር እሳቤ ቢያመጣም፤ ላለፉት ስድስት ዓመታት አሁንም ከሳሽ እንጂ አማራጭ ሃሳብ ይዞ የመጣ ግለሰብ፣ ቡድንና ፓርቲ አላየንም ሲሉ ገልጸዋል።
    አያይዘውም የኢትዮጵያ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አማራጭ ሀገር በቀል ሃሳብ ይዘው ቢመጡ ብልፅግና ለመማር ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
    በጌትነት ምሕረቴ
    ++++++++++++++++++++
    #prosperity #adanechabebi #ethiopia #ኢትዮጵያ #addisababa #ባህል #ብልጽግና #culture

ความคิดเห็น •