በትግራይ ክልል ከጦርነት አስቀድሞ ለተሰጡ ብድሮች “ፖለቲካዊ መፍትሔ” እንዲሰጥ የሚጠይቅ የፊርማ ማሰባሰብ እየተካሄደ ነው | Ethiopia | zena

แชร์
ฝัง
  • เผยแพร่เมื่อ 7 ก.พ. 2025
  • በትግራይ ክልል ከተካሄደው ጦርነት በፊት ለንግዱ ማህበረሰብ ተሰጥተው መመለስ ያልቻሉ ብድሮች እና ወለድን በተመለከተ፤ የፌደራል መንግስት “ፖለቲካዊ መፍትሔ” እንዲሰጥ የሚጠይቅ የፊርማ ማሰባሰብ በክልሉ ባሉ 52 ከተሞች እየተካሄደ ነው። አርብ የተጀመረው የፊርማ ማሰባሰብ በነገው ዕለት ተጠናቅቆ “ወደ ክልሉ ማዕከል ይላካል” ተብሎ እንደሚጠበቅ የትግራይ ክልል የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል።
    በጥቅምት 2013 ዓ.ም. በትግራይ ከተቀሰቀሰው ጦርነት አስቀድሞ፤ በክልሉ የፋይናንስ ተቋማት ተሰጥቶ የነበረው ብድር 31 ቢሊየን ብር እንደነበር ምክር ቤቱ አመልክቷል። ይህ ብድር ወለዱን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት 70 ቢሊዮን ብር ገደማ መድረሱን ምክር ቤቱ አመልክቷል።
    በትግራይ ክልል ከተሞች በሚገኙ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች አማካኝነት እየተካሄደ ያለው የፊርማ ማሰባሰብ፤ የፌደራል መንግስት ወለዱን እንዲሰርዝ አና ለተሰጡት ብድሮች ጦርነቱ እንዳስከተለው ጉዳት መጠን “ተመጣጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥ” የሚጠይቅ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት ተሰጥተው ለነበሩ ብድሮች፤ ባንኮች እስከ ታህሳስ 2017 ዓ.ም. የመክፈያ ጊዜ እንዲያራዝሙላቸው በሰኔ 2015 ዓ.ም. በሰርኩላር ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።
    ብሔራዊ ባንክ የሰጠው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ሁለት ወር በቀረበት ወቅት፤ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ “ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማምጣት ያለመ” መድረክ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በመቐለ ከተማ ተካሄዷል። የትግራይ ክልል የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት እንዲሁም የክልሉ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች በጋራ በካሄዱት በዚህ ስብሰባ ላይ፤ በየከተሞቹ ከሚገኙ ነጋዴዎች የፊርማ ማሰባሰብ እንዲካሄድ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
    (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    🔴 ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    ………………………………………………………………………………………………………………………..
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

ความคิดเห็น •