- 3
- 9 425
Essey Yohannes Official
เข้าร่วมเมื่อ 4 ก.ค. 2023
ሰላም! እሰይ ዮሐንስ እባላለሁ፡በመዝሙር አገልግሎት የማገለግል ሲሆን:ያደኩባት እና አገልግሎት ሀ ብዬ የጀመርኩባት አንጋጫ ቁጥር 1 ቃለህይወት ቤተክርስቲያን ስትሆን አሁን ደግሞ አዲስ አበባ ሲ.ኤም.ሲ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን ታቅፌ እያገለገልኩ እገኛለሁ፡ለህዝብ የደረሱ “መልካም እረኛ” እና “ምስክር” የተሰኙ መዝሙሮች ያሉኝ ሲሆን በነዚህ መዝሙሮች እንደተባረካችሁ እምነት አለኝ:ካልሰማችኋቸውም ቻነሌ ላይ ስላሉ እንድትሰሙ እጋብዛችኋለሁ:ይህ ቻነል የራሴን መዝሙሮች የምለቅበት ስለሆነ Subscribe በማድረግ አገልግሎቴን እንድትደግፉ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ:ተባረኩ::
ESSEY YOHANNES /መልካም እረኛ/ "MELKAM EREGNA" Ethiopian Gospel Song
“እግሮቼ ተሰናከሉ ባልሁ ጊዜ፥ አቤቱ፥ ምሕረትህ ረዳኝ።” - መዝሙር 94፥18
እያንዳንዱ እርምጃዬ፣
ተጠብቋል በጌታዬ፣
እግሬም እንዳይሰናከል፣
እርሱ ነው የሚከላከል፣
የሚጠብቀኝ አያንቀላፋም፣
ደክሞ ዝሎ ከጎኔ አይጠፋም፣
ተጨንቄ ስጠራ ስሙን፣
ይተውልኛል ሰላሙን::
መልካም እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ
ታማኝ እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ::
፩, ሁሌም ተስፋዬ እግዚአብሄር ነው፣
ምታመንበት ከእርሱ ውጪ ማነው፣
ቀን እና ለሊት ዘብ እየሆነ፣
ነፍሴን ከሞት ዐይኔን ከዕንባ ያዳነ::
መልካም እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ
ታማኝ እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ::
፪,ከእኔ ጋር ባይሆን እግዚአብሄር፣
በነፍሴ ላይ ጎርፍ ባለፈ ነበር፣
ስለከለለኝ ሆኖ እንደ ጋሻ፣
ተረፍኩ ከጠላቴ የጥርስ ንክሻ::
መልካም እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ
ታማኝ እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ::
፫,ሆድ ይፍጀው አልልም ሳዝን ሲከፋኝ፣
ጌታ እያለልኝ ገመና ሸፋኝ፣
የውስጥን የሚያውቅ ወዳጅ ነው የልብ፣
ከእስትንፋስም ይልቅ የሚቀርብ::
መልካም እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ
ታማኝ እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ::
እያንዳንዱ እርምጃዬ፣
ተጠብቋል በጌታዬ፣
እግሬም እንዳይሰናከል፣
እርሱ ነው የሚከላከል፣
የሚጠብቀኝ አያንቀላፋም፣
ደክሞ ዝሎ ከጎኔ አይጠፋም፣
ተጨንቄ ስጠራ ስሙን፣
ይተውልኛል ሰላሙን::
መልካም እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ
ታማኝ እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ::
፩, ሁሌም ተስፋዬ እግዚአብሄር ነው፣
ምታመንበት ከእርሱ ውጪ ማነው፣
ቀን እና ለሊት ዘብ እየሆነ፣
ነፍሴን ከሞት ዐይኔን ከዕንባ ያዳነ::
መልካም እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ
ታማኝ እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ::
፪,ከእኔ ጋር ባይሆን እግዚአብሄር፣
በነፍሴ ላይ ጎርፍ ባለፈ ነበር፣
ስለከለለኝ ሆኖ እንደ ጋሻ፣
ተረፍኩ ከጠላቴ የጥርስ ንክሻ::
መልካም እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ
ታማኝ እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ::
፫,ሆድ ይፍጀው አልልም ሳዝን ሲከፋኝ፣
ጌታ እያለልኝ ገመና ሸፋኝ፣
የውስጥን የሚያውቅ ወዳጅ ነው የልብ፣
ከእስትንፋስም ይልቅ የሚቀርብ::
መልካም እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ
ታማኝ እረኛ ነው ያለኝ፣
አልጥልሽም አልተውሽም ያለኝ::
มุมมอง: 1 576
วีดีโอ
ESSEY YOHANNES /ምስክር/ "MESEKER" New Ethiopian Gospel Song /2024
มุมมอง 7K28 วันที่ผ่านมา
“ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ!” - 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥13 በኩራት ላንቀላፉት ትንሣኤ፣ ህይወት እንዲቀጥል ሆነሃል መንስኤ፣ ብንሞት እንደማንቀር በምድር፣ ተነሥተህ ያሳየሀን ምስክር። ፩, የሚጠፋው የማይጠፋውን፣ የሚሞተው የማይሞተውን፣ ሊነሣ ለብሶ፣ ዳግም ታድሶ፣ ከሞት በኋላ፣ ከዚህኛው ሌላ፣ ህይወት ለመኖሩ፣ አንተው ምስክሩ። ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ፣ ባንተ በኩል ትንሣኤ ተሰጠ ፣ ከሙታን የተነሣህ ፊተኛ፣ ኢየሱስ ተስፋችን ነህ ለኛ። ፪,ልዑል ነህ ለኛ መጠጊያ፣ የረታህ የሞትን መውጊያ ፣ ሙታን እንዲነሡ ማረጋገጫ፣ በእምነት የምታስሮጠን የያዝነዉን ሩጫ። ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ፣ ባንተ በኩል ትንሣኤ ተ...